ANRS ICT Agency - ANRS ICT Agency

የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሐምሌ 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም 1 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስትር መልዕክት የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሐምሌ 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ 2 ኢትዮጵያ ካላት ሀብት ሁሉ ትልቁ የሰው ሃይሏ ነው፡፡ ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዟችንም በዚህ ላይ ይመሰረታል፡፡ ይህን ታሳቢ በማድረግ የክህሎት ልማት የዘርፋ የሪፎርም አጀንዳዎቻችን የትኩረት አቅጣጫና የስበት ማዕከል፣ የሥራ ገበያው ደግሞ የተግባሮቻችን ሁሉ መነሻ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ የቴክኒክና ሙያና ስልጠና ዘርፉ ለሀገር ዘላቂ ልማትና እድገት ሚናው የላቀ ቢሆንም ትኩረት ተነፍጎት ቆይቷል፡፡ በዚህም ብቁና ተወዳዳሪ ዜጎችን በማፍራት ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አኳያ ውጤት ቀያሪ ሚና መጫወት አልቻለም፡፡ ለሙያና ሙያተኛ ይሰጠው የነበረው ግምት የተዛነፈ ሆኖ በመቆየቱም ዘርፉ ለወጣቶቻችን ሳቢ እንዳይሆን አድርጎታል፡፡ የዘርፉ የሪፎርም አጀንዳዎች ሲቀረፁ ይህንን ችግር ከመሰረቱ ለመፍታት እና ዘርፉ ለሀገራችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ጎዟችን አስቻይ ሚና እንዲጫወት ታሳቢ ተደርጓል፡፡ በዚህም የክህሎት ልማት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ስብራቶቻችንን ለመጠገን በሚያስችሉ አዳዲስ እሳቤዎች እንዲቃኝ ተደርጓል፡፡ የክህሎት ልማት አዲሱ እሳቤ “ከስልጠና በላይ” የሚል አጠቃላይ ማዕቀፍ አለው፡፡ በዚህም የስልጠና ተቋማት ሥልጠና ከመስጠት የተሻገረ ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ይህ ተልዕኳቸውም የዘርፉን ችግር የመፍታት፣ መፍትሄ የማመንጨት እና ሀብት የመፍጠር እምቅ አቅማቸውን መጠቀም የሚያስችል ነው፡፡ ይህን ግዙፍ ተልዕኮ ለማሳካት ነባራዊ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታውን ባገናዘበ መልኩ የዘርፉን አዲስ እሳቤን በመቅረጽ ወደ ሥራ አስገብተናል፡፡ የእሳቤው ዘረ-መሎች ከሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያው ጋር የተሰናሰሉና ለሁለንተናዊ ብልጽግና ጉዟችን አስቻይ ሚና የሚጫወቱ ናቸው፡፡ ፈጠራ ከፍጥነት፤ ፍጥነትንም ከዘግይቶ መድረስ በረከት ጋር አሰናስሎ እምርታዊ እድገትን ለማምጣት እንዲያስችል ተደርጎ የተቃኘ ነው፡፡ የሥራ ገበያው የማይፈልገው ሙያ ማሰልጠን ሥራ አጥ ከማብዛት ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም፡፡ ስለሆነም የዘርፉ አዲስ እሳቤ ስልጠናው ገበያ መር እንዲሆን ያስገድዳል፡፡ የእሴት ሰንሰለትን እና የሥራ ገበያውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ አጫጭር ስልጠና ላይ በማተኮር በአጭር ጊዜ በርካቶችን ለመድረስ የሚያስችል ነው፡፡ አዲሱ የዘርፉ እሳቤ የመልማት ፀጋን መሰረት ያደረገ የተቋማት አደረጃጀትን በመተግበር አካባቢያዊና ሀገራዊውን ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፉን የሥራ ገበያ ፍላጎት ታሳቢ እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው፡፡ ይህም በሥራ ገበያው የማይፈለጉ ሙያዎችን በማሰልጠን የሚባክነውን የሰው ኃይል፣ ጊዜ እና የሀብት ብክነትን በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ ተቋማትን በማዘመን የስልጠና ስርዓታችን ጊዜውን የዋጀ መሆን ይኖርበታል፡፡ በዚህም የዘርፉ አዲስ እሳቤ ለፋብሪኬሽን ኢንጂነሪንግና ለቴክኖሎጂ ሽግግር ልዩ ትኩረት ሰጥቷል፡፡ ይህም ኢኮኖሚያዊ ነፃነትን ለመጎናፀፍ የሚያስችሉ ተኪ ምርት ላይ ሀገራዊ አቅም ይፈጥራል፡፡ 3 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስትር መልዕክት ለሥራ ገበያው ፍላጎት አጥጋቢ ምላሽ መስጠት ካለ ግሉዘርፍ ተሳትፎ የሚታሰብ አይደለም፡፡ ስለሆነም የግሉ ዘርፍ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ስርዓት ውስጥ ተሳታፊ ብቻ ሳይሆን የስርዓቱ ባለቤት ማድረግ የዘርፉ አዲሱ እሳቤ መሰረቶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በዚህም የግሉ ዘርፍ ከትብብር ስልጠና በሻገር በሙያ ደረጃ እና በስርዓተ ስልጠና ዝግጁቱ ላይ ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ያስችላል፡፡ የዘግይቶ ደራሽ አውንታዊ ትሩፋትን በአግባቡ ለመጠቀም፣ ጊዜንና ጉልበትን የሚቆጥብ እና ሀገራዊ የፈጠራ ሥራን የሚያበረታቱ ስርዓቶችንም አዲሱ የዘርፉ እሳቤ ታሳቢ አድርጓል፡፡ በዚህም የክህሎትና ቴክኖሎጂ ባንክን ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል፡፡ ይህም አካባቢያዊ ችግሮችን ወደ መልካም አጋጣሚዎች መቀየር የሚችሉ ወጣቶችን ድካምና ውጣውረድ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ በቀድሞ የዘርፉ አሰራር ብቁ፣ በቂና ተወዳዳሪ ዜጎችን ማፍራት የስልጠና ተቋሞቻችን ተልዕኮ መሰረት ነው፡፡ በአዲሱ የዘርፉ እሳቤ በሙያ ብቻ ሳይሆን በስነ-ምግባር የታነፀ ሥራና ሀገር ወዳድ ትውልድ መቅረጽ የተልዕኳቸው ሌላኛው መሰረት እንዲሆን ተደርጓል፡፡ በዚህም ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው የዘመኑ አርበኝነት የሚፈልገውን እውቀትና ልል ክህሎትን ጨምሮ የሙያ ስነ-ምግባር እንዲላበሱ የሚያደርግ የሙያ ደረጃና ስርዓተ ስልጠና ተቀርፆ ወደ ሥራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ እነዚህ እሳቤዎች ወደ መሬት ወርደው ተግባራዊ መሆን ጀምረዋል፡፡ አዳጊ እና ተስፋ ሰጪ ብቻ ሳሆን ተጨባጭ ውጤቶችንም ማየት ተችሏል፡፡ ጥቂት የማይባሉና እሳቤውን ሳያጓድሉ መተግበር የቻሉ ተቋማት ደግሞ አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ዘርፉን ለወጣቶች ምቹና ሳቢ ለማድረግ በተጀማመሩ ጥረቶች ዘርፉን በምርጫ የሚቀላቀሉ ወጣቶች ቁጥር አንፃራዊ እድገት አሳቷል፡፡ በመደበኛ እና አጫጭር ስልጠና የሚያልፉ ዜጎች ቁጥርም ሪፎርሙ ከጀመረበት ዓመት አንፃር ከእጥፍ በላይ ማደግ ችሏል፡፡ ተኪ ምርቶችን ለማምረት በተጀመሩ ጥረቶች በክህሎት ኢትዮጵያ መርሃ ግብር ብቻ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ እና አሰራሮችን የሚያቀላጥፉ ከአንድ መቶ ሀምሳ በላይ ቴክኖሎጂዎችን መስራት ተችሏል፡፡ አካባቢያዊ ችግሮችን የሚፈቱ ብቻ ሳይሆን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታችንን የሚጨምሩ ትላልቅ የፈጠራ ሥራዎች በሀገራችን ወጣቶች እውን ተደርገዋል፡፡ ይህ ስትራቴጂ የዘርፉን አዲስ እሳቤ ትግበራ እና ውጤታማነትን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር የሚያስችል ነው፡፡ ስለሆነም ስትራቴጂው የፖሊሲ ሰነድ ብቻ ሳይሆን የሀገራችንን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፍኖተ ካርታ ነው ማለት ይቻላል። ስትራቴጂው የታለመለትን ግብ እንዲመታ የሁሉንም አካላት የጋራ ጥረትና የተቀናጀ ርብርብን ይጠይቃል፡፡ ስለሆነም ወላጆች፣ ሰልጣኞች እና አሰልጣኞችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ሁሉም አስፈፃሚ፣ ባለድርሻ እና በክህሎት ልማት ሥራው ላይ ሚና ያላችሁ አካላት በሙሉ ለስትራቴጂው ትግበራ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡ አመሰግናለሁ። ሙፈሪያት ካሚል አህመድ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መልዕክት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017፣ የፖሊሲ ማስፈጸሚያ ሠነድ ብቻ ሰይሆን የሰለጠነ፣ ሀገር ወዳድ እና ከወቅቱ ጋራ መላመድ የሚችል የሰው ሃይል ለማፍራት ያለንን ሀገራዊ ቁርጠኝነትን የሚያሳይ ነው። ይህ ስትራቴጂ ከጊዜያዊ ተግዳሮቶች የዘለለ፣ የነገን ፍላጎት ለመተንበይ የሚያስችል አካሄድ የቀየሰና ቀጣይነት ያለው የመማርን፣ የፈጠራን እና የአካታችነትን ባህል አጣምሮ የተዘጋጀ ፍኖተ ካርታ ነው። ይህ ሪዕይ እንደ አመራርም ሆነ እንደ ዜጋ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ለኢትዮጵያ ኢንደስትሪያላይዜሽን እና ለማህበራዊ ለውጥ የማዕዘን ድንጋይ በመሆን የሚያገለግል ይሆናል። ይህንን ስትራቴጂ ወደ ተጨባጭ ውጤቶች ለመተርጎም የዘርፉ ቁልፍ ባለ ድርሻ አካላት የተቀናጀ ርብርብ እጅግ ወሳኝ ነው። በዚህም የፖሊሲ አውጪዎች እና የክልል ባለሥልጣናት ማሻሻያዎችን መደገፍ እና አስፈላጊውን የገንዘብ ድጋፍ እና ቁጥጥር ማረጋገጥ፣ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት እና የሴክተር አካላት ጥራት እና የፈጠራን ባህል ማዳበር፣ እንዲሁም ቀጣሪዎች እና የግል ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ለተግባር ልምምድ በራችሁን ክፍት በማድረግ በፍላጎት ላይ የተመሠረተ የሥልጠና መርሓ ግብሮችን በጋራ በመንደፍ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቃል። የልማት አጋሮች ሀብታችሁንና ዕውቀታችሁን ለቴክኖሎጂ ሽግግር እና ለምርምር ሥራ መጎልበት ማዋል ይገባል። እንዲሁም ሕዝባችን የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን እንደ መልካም የብልጽግና ጎዳና መቀበል ይኖርበታል። ከዚህም ባሻገር ወላጆች፣ ሠልጣኞች እና አሠልጣኞች ደግሞ የሀገር ፍቅር እና የልህቀት ዕሴቶችን ማስጠበቅ አለብን። ይህ ስትራቴጂ ብቁ ባለሙያዎችን እና ሥራ ፈጣሪ ዜጎችን ለማፍራት ግልጽ መንገድን ከማስቀመጡም ባሻገራ የሥራ-ተኮር ሥልጠና፣ የሙያን ዕድገት ምክር አገልግሎት አሰጣጥን እና ውጤታማ የሥራ ሥምሪት ያበረታታል። ነገር ግን ወሳኙ ኃይላችን ቆራጥ ተግባራችን መሆኑን በጽኑ እናምናለን። በጋራ ፈጠራን የሚያጎለብት፣ ሀገራዊ ኩራትን የሚያጎናጽፍ እና የኢትዮጵያን ተወዳደሪነት የሚያረጋግጥ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት መገንባት እንችላለን። ይህን ሪዕይ ወደ ተግባር ለመቀየር እያንዳንዳችን የበኩላችንን እንድንወጣ በአክብሮት እጠይቃለሁ። አመሰግናለሁ። ተሻለ በሬቻ ያዴሳ (ዶክተር) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ 4 5 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም ምኅጻረ ቃላትና ትርጓሜ ምኅጻረ ቃላት ቴ/ሙ/ሥ - ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኅ/ተ/ም/እ - ኅላፊነት፣ ተጠያቂነት፣ ምክር የሚሰጥ እና እንዲያውቀው መረጃ የሚሰጠው አካል ሥ/ክ/ሚ - የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ትርጓሜ የአፕረንትስሽፕ ሥልጠና ማለት ሙያን ለማለማመድ ዕውቅና በተሰጠው የማምረቻ ወይም የአገልግሎት ሰጪ ተቋም ወይም ባለሙያ አማካይነት የሙያ ልምምድ ውልን መሠረት በማድረግ የሚሰጥ የሥልጠና ዓይነት ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ የቴ/ሙያ ሥልጠናን ተቋማት የንድፈ-ሐሳብ ሥልጠናው በመስጠት ሊሳተፉ ይችላሉ። የትብብር ሥልጠና ማለት የቴ/ሙያ ሥልጠና ተቋማት ከምርትና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋራ በመተባበር ቴ/ሙያ ሠልጣኞችን በጋራ የሚያበቁበት የሥልጠና አይነት ሆኖ ሠልጣኞች አብዛኛውን የተግባር ሥልጠናቸውን በኢንዱስትሪ ውስጥ የሚያደርጉ ይሆናል። ኢንተርንሺፕ ማለት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚሠለጥኑ ሠልጣኞች በኢንዱስትሪ ውስጥ ተግባራዊ የሥራ ልምድ የሚያገኙበት፣ በአሠልጣኝ የሚመራ የአጭር ጊዜ የልምምድ ፕሮግራም ነው። ኤክስተርንሺፕ ማለት የቴክኒክና ሙያ አሠልጣኞች የማሠልጠን ብቃታቸውንና የቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸውን ለማሻሻል በኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሚወስዱት የዐጭር ጊዜ የተግባር ልምምድ ነው። ገቬርናንስ ማለት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት አስተዳደርን የሚመሩ የፖሊሲዎች፣ የደንቦች እና የአሠራር ሥርዓቶች ማዕቀፍ የሙያ ደረጃዎችን፣ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ሥርዓቶችን እና የዕውቅና አሰጣጥ ሂደቶችን በማዘጋጀት የሥልጠና ጥራት እና አስፈላጊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥርዓት ነው። የልህቀት ማዕከል ማለት አንድን የኢንዱስትሪ ዘርፍ ትኩረት በማድረግ ከኢንዱስትሪው ተዋናዮች ጋራ ጥብቅ ቁርኝትን በመፍጠር ከኢንዱስትሪ ዘርፉ ጋራ ተያያዥነት ባላቸው ሙያዎች ላይ የዘርፉን የክህሎት ልማትና የኢኖቬሽን ፍላጎትን የሚያሟላ ተቋም ነው። ሀገር-በቀልና ባህላዊ ሙያ ማለት ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገሩና ባህላዊ ዘዴዎችን የሚጠቀሙ የሀገር-በቀል የእጅ ሙያ ሥራዎች ሲሆኑ፣ ለማንነት፣ ለኑሮና ለቅርስ አጠባበቅ የሚያገለግሉ ናቸው። የሀገር-በቀልና ባህላዊ ሙያ ማኅበር ማለት የሀገር-በቀልና ባህላዊ ሙያ ባለቤቶች ሙያቸውን ለማዳበርና ለማስፋፋት እንዲያስቸላቸው የሚያቋቁሙት የሙያ ማህበር ወይም አደረጃጀት ነው። የኢ-መደበኛ ዘርፍ ሠራተኛ ማለት በሕግ ወይም በመንግሥት ያልተመዘገበ ወይም ቁጥጥር የማይደረግበት፣ እንዲሁም እንደ ኮንትራት፣ ጥቅማጥቅሞች እና የማኅበራዊ ዋስትና ያሉ የሕግ እና የማኅበራዊ ጥበቃዎች የሌሉት ግለሰብ ነው። የኢንዱስትሪ የብቃት ምዘና ማዕከል ማለት የሙያ ብቃት ምዘና ለመስጠት ዕውቅና የተሰጠው እና ለዚሁ ተግባር መስፈርቶችን ያሟላ ተቋም ነው። የኢንዱስትሪ መዛኝ ማለት የሙያ ብቃትን በምዘና ለመለካት የሚያስችል ሥልጠና የወሰደና ፈቃድ ያለው የኢንዱስትሪ ባለሙያ ነው። የሴክተር ክህሎት አስፈጻሚ አካል ማለት የኢንዱስትሪውን ተሳትፎ በማሳደግ፣ የሚያስፈልጉትን ክህሎቶች በመለየትና በመከታተል የክህሎት ሥልጠናን የሚያሳልጥና እና የሚያስተባብር አካል ነው። አረንጓዴ ክህሎት ማለት የአካባቢን ዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስፈልጉ ዕውቀቶች፣ ክህሎቶች እና ዕሴቶች ሲሆኑ፣ የአካባቢን ብክለት የሚቀንሱ እና ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችንና ሂደቶችን የመጠቀምን ብቃት ያጠቃልላል። አረንጓዴ ቴ/ሙያ ማለት የአካባቢን ዘላቂነት መርሆዎችን በተግባርና በትምህርት የሚያሳይ ኅላፊነት የተሞላበት የትምህርትና ሥልጠና ተግባር ነው። የቀደመ ትምህርት ዕውቅና ማለት አንድ ግለሰብ ከሥራ ልምድ፣ ከመደበኛ ትምህርት ውጪ ወይም ከሌሎች የመማሪያ መንገዶች ያገኘ/ችውን ዕውቀት እና ክህሎት ዕውቅና የሚሰጥበትና የሚያረጋግጥበት ሂደት ነው። የክህሎት ባንክ ማለት የሰዎች ክህሎቶች እና ብቃቶች የተመዘገቡበት፣ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የሰውን ኃይል ፍላጎት ለማሟላት የሚያገለግል የመረጃ ቋት ነው። የማኅበረሰብ አገልግሎት ማለት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት፣ ሠልጣኞች ወይም ሠራተኞች ለኅብረተሰቡና ለኢንዱስትሪው የሚሰጡት የተቀናጀና የታቀደ ድጋፍ ነው። የክህሎት ልማት አስተዋፅኦ ማለት በኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሚደረግ የክህሎት ልማትና የኢኖቬሽን ሥራዎችን ለመደገፍ ከግል ዘርፍ ኩባንያዎች የሚሰበሰብ ሀብት ሲሆን በአፕሬንትሽፕና በትብብር ሥልጠና የሚሳተፉ ኩባኒያዎች የሚያበርክቱት አስተዋፅኦ እየታየ ነጻ እንዲሆኑ በማድረግ የሚፈጸም ይሆናል። የፌንድ ቅርጫት ማለት የልማት አጋሮች በአንድ የገንዘብ ድጋፍ ማዕቀፍ ወይም ጥላ ስር ሆነው ተቀናጅተውና ተናበው ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ሀብትን በውጤታማነት መጠቀም እንዲያስችል በሚኒስቴሩ የተቋቋመ የሀብት ቋት ነው። የቴክኒክና ሙያ ምርምር ማለት በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ዕውቀትን እና ግንዛቤን ለመፍጠር የሚደረግ ስልታዊ ጥናት ሲሆን፣ ፖሊሲ ለማውጣት፣ ለሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት እና ለሥልጠና አሰጣጥ ዘዴዎች መሻሻል ጠቃሚ መረጃ ይሰጣል። የሙያ ማማከር ማለት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለሠልጣኞቻቸው ስለ ሥራ ፍለጋ፣ የሙያ ምርጫ እና ቀጣይ የሙያ ዕድገት የሚሰጡት ድጋፍ ነው። የቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማለት አዲስ ለሚቋቋሙ ወይም ለጀማሪ ንግዶች ዕድገትና ስኬት እንዲያገኙ የሙያና የፋይናንስ ድጋፍ የሚሰጥበት የአሠራር ሥርዓት ነው። 6 7 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም ጨመቅ የቢዝነስ ኢንኩቤሽን ማለት አዲስ ለሚቋቋሙ ወይም ለጀማሪ ንግዶች ዕድገትና ስኬት እንዲያገኙ የሙያና የፋይናንስ ድጋፍ የሚሰጥበት የአሠራር ሥርዓት ነው። የቴክኖሎጂ ኢንኩቤሽን ማዕከል ማለት ጀማሪ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችና ፈጣሪዎች የቴክኖሎጂ ውጤቶቻቸውን ወደ ተግባር እንዲለውጡ የሚያግዝ የገንዘብ፣ የሙያና የሥራ ቦታ ድጋፍ የሚሰጥ ተቋም ነው። ዲጂታል ክህሎት ማለት የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ዲጂታል መረጃዎችን ለማግኘት፣ ለመረዳት፣ ለመገምገም፣ ለመፍጠር እና ለማስተላለፍ የሚያስችል ዕውቀትና ብቃት ነው። የጥራት ፍተሻ ማለት የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሥልጠና አሰጣጣቸውና አጠቃላይ አሠራራቸው የተቀመጠውን ሀገራዊ ደረጃና የጥራት መመሪያ የሚያሟላ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚደረግ ስልታዊና ገለልተኛ ግምገማ ነው። የጊግ ሠራተኛ መድረክ ማለት ራሳቸውን የሚያንቀሳቀሱ ባለሙያዎችን ለዐጭር ጊዜ አገልግሎቶች ከደንበኞች ጋራ የሚያገናኝ ዲጂታል የገበያ ቦታ ነው። ዓጫጭር ሥልጠና ማለት በአንድ የተወሰነ የሥራ ዘርፍ ላይ የሚያተኩር፣ ተማሪዎችን በቀላሉ በሥራው ዓለም ተቀባይነት እንዲያገኙ የሚያስችል የተለየ የሙያ ክህሎት የሚያስጨብጥና በብቃት ምዘና የሚጠናቀቅ የሥልጠና ፕሮግራም ነው። 8 የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ብልጽግና ለማሳካት፣ ተፈላጊውን ብቃት (ዕውቀት፣ ክህሎት እና አመለካከት) የተላበሰ፣ ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋራ የሚላመድና የፈጠራ ችሎታ ያዳበረ የሰው ኃይል ማፍራት ወሳኝ ነው። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዐሥርት ዓመታት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና (ቴ/ሙ/ሥ) ተደራሽነትን በማስፋፋትና በውጤት ላይ የተመሠረተ ሥልጠና በመተግበር ጉልሕ ዕድገት ብታስመዘግብም፣ አሁንም የሥልጠና ፕሮግራሞች ከሥራ ገበያ ፍላጎት ጋራ አለመጣጣም፣ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ ውስንነት፣ የሥልጠና ጥራት ችግር ያለበት መሆን፣ የፋይናነስ ዕጥረት፣ በኅብረተሰቡ ዘንድ የቴ/ሙ/ሥ ተመራጭ አለመሆን፣ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ሠልጣኞች የመሳብ ዓቅም ውስንነ እና ልዩ ትኩረት ለሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽነት አናሳ መሆን የመሳሰሉ ተግዳሮቶች ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው። ይህ የ2017 ዓ.ም. የቴ/ሙ/ሥ ስትራቴጂ ከላይ የተዘረዘሩ ተግዳሮቶቸን በመቅረፍ የሀገራዊ ልማት ሪዕይን እውን ለማድረግ ያለመ ሲሆን፣ ተፈላጊውን ብቃት የተላበሰ፣ ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋራ የሚላመድ እና የላቀ የፈጠራ ችሎታ የዳበረ የሰው ኃይል ማፍራት ላይ ያተኩራል። ስትራቴጂው ከ2000 ዓ.ም. የቴ/ሙ/ሥ ስትራቴጂ ትግበራ ከተገኙት መልካም ተሞክሮዎች በመነሣት፣ በ2015 ዓ.ም. ከጸደቀው ትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ ጋራ እንዲጣጣም ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ሀገራዊ የልማት አጀንዳዎች እና ዓለም ዓቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን አካቷል። ዋናው ግቡም ከፍተኛ ጥራት ያለው፣ በሥራ ገበያው ተፈላጊ የሆነ ብቃት ያለው የሰው ኃይል ማፍራት የሚያስችል ሥልጠና የሚሰጥ፣ የሥራ ፈጠራንና የሕይወት ዘመን ክህሎትን የሚያበረታታ፣ ተለዋዋጭ፣ አካታች እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የቴ/ሙ/ሥ ምኅዳር መፍጠር ነው። የ2017 ዓም የኢትዮጵያ የቴ/ሙ/ሥ ስትራቴጂ የሀገሪቱን የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት ከሥር መሠረቱ ለመለወጥ ታስቦ የተዘጋጀ ማዕቀፍ ነው። ይህ ስትራቴጂ በፍጥነት እየተለዋወጠ ካለው የሥራ ገበያ ፍላጎት ጋራ ለመጣጣምና የሀገሪቱን ከፍተኛ የወጣት ቁጥር ዓቅም አሟጦ ለመጠቀም ካለው አጣዳፊ ፍላጎት በመነሣት፣ የ2000 ዓም ስትራቴጂ ትግበራ የተመዘገቡ ተሞክሮዎችን በመጠቀምና ከሀገራዊ የልማት ቅድሚያዎች ጋራ በማጣመር ተዘጋጅቷል። ይህ ስትራቴጂ እንደ አሉታዊ የሕዝብ ግንዛቤ፣ የክህሎት ክፍተት እና የተቋማት ጥገኝነት የመሳሰሉትን ለረጅም ጊዜ የቆዩ ተግዳሮቶች በቀጥታ የሚፈቱ ጠቃሚ ሐሳቦች ላይ የተመሠረተ ነው። ከዋና ዋናዎቹ ተነሣሽነቶች መካከል ተቋማትን በፋይናንስ ራሳቻውን የሚያስችል የደረጃ በደረጃ የራስ ገዝ አስተዳደር ሞዴል፣ ቴ/ሙ/ሥን እንደ “ቀዳሚ ምርጫ” የሙያ መሥመር ዳግም ለመገንባት የሚያስችል ሀገራዊ አገልግሎት እና የሰዎችን ተሰጥዎ ከተስማሚ ሙያ ጋራ የሚያዛምድ ተሰጥዎ ተኮር የሥልጠና ሥርዓት መገንባት ይገኙበታል። ከዚህም በተጨማሪ፣ ሀገራዊ የክህሎት ባንክ መመሥረት ክህሎቶች በየትኛውም መንገድ ቢገኙ ዋጋ እንዲኖራቸው በማድረግ የበለጠ ፈጣንና ቀልጣፋ የሥራ ገበያ ይፈጥራል። ይህ ስትራቴጂ በአራት የስትራቴጂ ትኩረቶች ማለትም፡- የቴ/ሙ/ሥ ገቨርናንስን በማጎልበት፣ የሥልጠና አግባብነትንና ጥራትን በማሻሻልና በማረጋገጥ፣ ለሥራ ዝግጁ የሚያደርጉ ክህሎቶችን በማዳበር እና የምርምርና ኢኖቬሽን ሥነ-ምኅዳርን ማሳደግ ላይ የተዋቀረ ነው፡፡ ስትራቴጂው ከሀገራዊ ፖሊሲዎች ጋራ ያለው ተናባቢነት፣ የሥልጠና ፍትሐዊ ተደራሽነት እና የባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎን እና ቅንጅታዊ አሠራር ሥርዓት እንዲዳብር ልዩ ትኩረት ይሰጣል። እንዲሁም የቴ/ ሙ/ሥ ሥርዓቱ የሥራ ገበያውን ፍላጎት መሠረት ማድረግ እንዲቻል፣ ሥርዓተ-ሥልጠናዎችን፣ የሙያ ደረጃ ምደባዎችን እና የሥልጠና ዘዴዎችን በማዘመን በሥልጠና ተቋማት በሚሰጠው ሥልጠና እና በሥራ ቦታ በሚፈለጉት ብቃቶች መካከል ያለውን ልዩነት ለማጥበብ እና ሠልጣኞችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ለሚመራ ኢኮኖሚ በብቃት ለማዘጋጀት በሚያስችሉ ፈጠራና ዲጂታል ሽግግር ላይም ትኩረት ይሰጣል። የቴ/ሙ/ሥ ስትራቴጂው ለአዳዲስና ክሡት ኢንዱስትሪዎች የሚያስፈልጉ ክህሎቶች ላይ ዜጎችን ለዕውቀትና ልስኬት ለማብቃት፣ አረንጓዴ ክህሎትንና ዲጂታላይዜሽንን ማስተዋወቅና ሁሉን ዓቀፍ በሆነው የክትትል፣ ግምገማ፣ ተጠያቂነት ማረጋገጥ እና ተሞክሮ ቅመራ ማዕቀፍ አማካይነት በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ አሰጣጥን የመሳሰሉ የወደፊት ወሳኝና ባለድርሻ አካላትን በማካተት፣ የቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት የዛሬን ችግሮች ከመፍታት ባሻገር ለነገው ዕድገትም ዋንኛ አንቀሳቃሽ መሆኑን ያረጋግጣል። 9 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም 11 10 ማውጫ ቁልፍ ጉዳይ 7፡ ለሀገር ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የኢኮኖሚ ዘርፎች ልዩ የልህቀት ማዕከሎችን ለመመሥረት ስትራቴጂያዊ ዞን አከፋፈልና ልዩ ልዩነትን መተግበር 35 ቁልፍ ጉዳይ 8፡ በኢ-መደበኛ ዘርፍ የተሠማራውን የሰው ኃይል ብቃትን ማሳደግ 36 ቁልፍ ጉዳይ 9፡ የቴ/ሙ/ሥ/ ዓለም ዓቀፋዊነትን እና የክልላዊ ትስስር ማሳደግ 36 ቁልፍ ጉዳይ 10፡ ዲጂታላይዜሽንን በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ውስጥ ማሳደግ 37 ቁልፍ ጉዳይ 11፡ አረንጓዴ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ፕሮግራምን ማሳደግ 37 ቁልፍ ጉዳይ 12፡ የሀገር-በቀል ዕውቀቶችንና ክህሎቶችን በቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት ውስጥ ማዋሓድና መጠቀም 38 ቁልፍ ጉዳይ 13፡ ተጽዕኖ መቋቋም የሚችል እና ተለማጭ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት መገንባት 38 3.3. ትኩረት ሦስት፡ ለሥራ ዝግጁ የሚያደርጉ ክህሎቶችን ማሳደግ 39 ቁልፍ ጉዳይ 1፡ ሥራ ፈጠራን እና የንግድ ሥራን ማጎልበት 39 ቁልፍ ጉዳይ 2፡ የሙያ ማማከር ድጋፍ እና አገልግሎቶችን ማሻሻል 40 ቁልፍ ጉዳይ 3፡ ማኅበረሰቡን መሠረት የደረጉ የሥራ ልምምድ (Apprenticeships) እና የትብብር ሥልጠና (Cooperative Training) ማስፋፋት 40 ቁልፍ ጉዳይ 4፡ ሀገራዊ የክህሎት ባንክ በማቋቋም የክህሎት ክምችትና ዝውውር ማጎልበት 41 ቁልፍ ጉዳይ 5፡ ለቀደመ ትምህርት ዕውቅና መስጠት (RPL) 41 ቁልፍ ጉዳይ 6፡ በሀገር ውስጥ እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚገኙ የሥራ ገበያ ዕድሎችን ማሳደግ 43 3.4 ትኩረት አራት፡ የምርምር እና ፈጠራን ሥነ-ምኅዳር ማበልጸግ 44 ቁልፍ ጉዳይ 1፡ የቴ/ሙ/ሥ ጥናትና ምርምር ምኅዳርን ማበልጸግ 44 ቁልፍ ጉዳይ 2፡ በዜጎች የሚመራ ፈጠራ እና ማኅበራዊ የፈጠራ ማዕከሎች (Social Innovation Labs) 44 ቁልፍ ጉዳይ 3፡ የቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደቱን ለመጠቀም ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ መተግበር 45 ቁልፍ ጉዳይ 4፡ የማኅበረሰብ አገልግሎትን ማሳደግ 45 ቁልፍ ጉዳይ 5፡ በተሰጥኦ ላይ የተመሠረተ ሥልጠናና ምደባ ሥርዓት በመተግበር ተሰጥኦን መፈለግና ማዳበር 46 ክፍል አራት፡ የስትራቴጂው ትግበራ ስትራቴጂካዊ ማዕቀፎች 47 4.1. የሀብት ማሰባሰብ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ 48 4.2. የስትራቴጂ ትግበራ ሥጋት እና የሥጋት ቅነሳ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ ማጠቃለያ 49 4.3. የክትትል፣ ግምገማ፣ ተጠያቂነት እና ተሞክሮ ቅመራ (MEAL) ማዕቀፍ ማጠቃለያ 49 4.4. ተቋማዊ የአሠራር ሞዴል፣ የአፈጻጸም ልህቀት፣ ተቋሟዊ ዓላማን ማስተማርና ማስተዋወቅ፣ የማኅበረሰብን ግንዛቤን ማሳደግ እና ተደራሽነት የማረጋገጥ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ ማጠቃለያ 50 4.4.1. ተቋማዊ የአሠራር ሞዴል እና የአፈጻጸም ልህቀት ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ 51 4.4.2. የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ማርኬቲንግ እና ማስተዋወቅ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ 51 4.4.3. የማኅበረሰብ ግንዛቤን ማሳደግ እና ተደራሽነትን የማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ ማዕቀፍ 51 4.5. የቲክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ ትግበራ የኃላፊነት፣ ተጠያቂነት፣ ምክር የሚሰጥ እና እንዲያውቀው መረጃ የሚሰጠው አካል ማትሪክስ (ኃተምእ) ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ ማጠቃለያ 52 ማውጫ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር መልዕክት 3 የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መልዕክት 5 ምኅጻረ ቃላትና ትርጓሜ 6 ጨመቅ 9 ክፍል አንድ፡ መግቢያ እና ዳራ 12 1.1. መግቢያ 13 1.1.1. አጠቃላይ ዕይታ 13 1.1.2. የስትራቴጂው ዳራ 13 1.1.3. የስትራቴጂው አስፈላጊነት 14 1.1.4. የስትራቴጂው ዓላማዎች 15 1.2 የነባራዊ ሁኔታ ትንተና 15 1.2.1 ገቨርናንስ እና ቅንጅታዊ አሠራር 15 1.2.2 የሥልጠና አግባብነትና ጥራት 16 1.2.3 ለሥራ ብቁ የሚያደርጉ ክህሎቶችን ማዳበር 17 1.2.4 ምርምር ፈጠራ እና የማኅበረሰብ አገልግሎት 17 ክፍል ሁለት፡ ርዕይ፣ ተልዕኮ እና ዓላማዎች 18 2.1. ርዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዋና ዋና ዕሴቶች እና መርሖች 19 2.2 የስትራቴጂው ትኩረቶች እና ዓላማዎቻቸው 19 2.2.1 የስትራቴጂው ትኩረቶች 21 2.2.2 የስትራቴጂው ዓላማዎች 22 ክፍል ሦስት፡ ቁልፍ ጉዳዮች፣ ስትራቴጂዎች እና የሚጠበቁ ውጤቶች 25 3.1 ትኩረት አንድ፡ የቴ/ሙ/ሥ ገቨርናንስን ማጎልበት 26 ቁልፍ ጉዳይ 1፡ የቴ/ሙ/ሥ ሕጋዊና ተቋማዊ አደረጃጀትን ማጣጣም 26 ቁልፍ ጉዳይ 2፡ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ፣ ትብብር እና ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር 26 ቁልፍ ጉዳይ 3፡ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ 26 ቁልፍ ጉዳይ 4፡ በቴ/ሙ/ሥ አመራር ሥርዓት ውስጥ የዜጎችን እና የማኅበረሰብ ተሳትፎን ተቋማዊ ማድረግ 27 ቁልፍ ጉዳይ 5፡ ተቋማዊ ራስን መቻልን ለማሳካት የሀብት ማሰባሰብንና አጠቃቀምን ማሳደግ 27 ቁልፍ ጉዳይ 6፡ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና መሠረተ ልማትን ማሻሻል 28 ቁልፍ ጉዳይ 7፡ የጥራት ማረጋገጫ ሥርዓትን ማሻሻል 28 ቁልፍ ጉዳይ 8፡ ተደራሽነትን እና ፍትሓዊነትን ማሻሻል 29 ቁልፍ ጉዳይ 9፡ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ገጽታ ግንባታን ማሻሻል 29 ቁልፍ ጉዳይ 10፡ የመረጃ አያያዝ፣ ፍሰት እና አጠቃቀምን ማሻሻል 30 ቁልፍ ጉዳይ 11፡ ክትትል፣ ግምገማ፣ ተጠያቂነት እና ልምድ ቅመራን (MEAL) ሥርዓትን ማሻሻል 30 3.2. ትኩረት ሁለት፡ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና አግባብነት እና ጥራትን ማሻሻል 30 ቁልፍ ጉዳይ 1፡ የሙያ ደረጃ ምደባ እና የሥርዓተ ሥልጠና ጥራትን ማሻሻል 30 ቁልፍ ጉዳይ 2፡ የማኅበረሰብን የሥልጠና ፍላጎትና የክህሎት ክፍተቶችን የሚለይ እና ሥርዓተ ሥልጠና የሚያዘጋጅ ሥርዓት በጋራ መፍጠር 31 ቁልፍ ጉዳይ 3፡ የሥልጠና አቅርቦትን ማሻሻል 31 ቁልፍ ጉዳይ 4፡ የብቃት ምዘና እና የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ሥርዓትን ማዘመን 32 ቁልፍ ጉዳይ 5፡ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና አሠልጣኞች እና አመራሮች ብቃት ማሻሻያ ሥርዓት ማጠናከር 34 ቁልፍ ጉዳይ 6፡ በሠልጣኞ ዘንድ ጠንካራ የሥራ ሥነ-ምግባርና የሀገር ወዳድነት ስሜትን ማጎልበት 34 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም ክፍል አንድ መግቢያ እና ዳራ ክፍል አንድ 12 1.1. መግቢያ 1.1.1. አጠቃላይ ዕይታ ይህ ስትራቴጂ በትግበራ ላይ ያለውን የ2000 ዓ.ም. የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና (ቴ/ሙ/ሥ) ስትራቴጂ ትግበራ መልካም ተሞክሮዎችን በማጎልበትና ክፍተቶችን በመሙላት የሥልጠና ሥርዓቱን ለማሻሻል ያለመ ነው። በመሆኑም ስትራቴጂው ራሱን ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋራ በማስማማት፣ የገቨርናንስ ሥርዓትን በማሻሻል፣ ከፍተኛ ጥራትና ተደራሽነት ያላቸውን የሥልጠና ፕሮግራሞችን በማቅረብ እንዲሁም ጠንካራ የሆነ የምርምርና የፈጠራ ሥርዓትን ማጎልበት ላይ ያተኮረ ነው። ይህንም ለማሳካት በመንግሥት፣ በግል ዘርፉ፣ በሥልጠና ተቋማት እና በኢንዱስትሪዎች መካከል ጠንካራ ቅንጅት መፍጠር፣ ተከታታይነት ያለው የሥራ ገበያ መረጃ ዳሰሳ እና ትንተና ማካሄድ፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የሥልጠና ፕሮጋራሞችን መለየት እና ተግባር ላይ የተመሠረተ የሥልጠና ዘዴዎችን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል። በተጨማሪም ልዩ ትኩረት የሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሥልጠና ፕሮግራሙ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አካታችነትና ተደራሽነትን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። በዚህ ስትራቴጂ ትኩረት የተሰጠው በቴ/ሙ/ሥ/ ሥርዓት ውስጥ የሚያልፉና ብቃታቸው በሀገር ዓቀፍ የሙያ ብቃት ምዘና የተረጋገጠ ዜጎችን ስኬታማ ሥራ ሥምሪት እንዲኖራቸው ማስቻል ነው፡ ፡ ይህም የሥራ ፈጣሪነትን በማበረታታት፣ በሙያቸው የማደግ ዕድል በማመቻቸት እና ከሥልጠና ወደ ሥራ የሚደረግ ሽግግርን ማፋጠንን ያካተተ ነው። ሰለሆነም በሕይወት ዘመን ክህሎት ሥልጠና ላይ የሚሳተፉ ዜጎች በፍጥነት ከሚለዋወጠው የሥራ ገበያ ፍላጎት ጋራ መላመድ እንዲችሉ ዝግጁ ማድረግ ይገባል። በተጨማሪም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፉ ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም የሚያስችል ብቃትን ማስታጠቅ፣ አዳዲስ የሥልጠና ዘዴዎችን በማዳበር እና የጥናትና ምርምር የፈጠራ ባህል ማስፈን ላይ ትኩረት ያደርጋል። 1.1.2. የስትራቴጂው ዳራ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና በሥራ ገበያ ውስጥ የሚያስፈልግ ብቃትን በማስታጠቅ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለመደገፍ፣ ለኢንዱስትሪና ከተሞች መስፋፋት፣ ለግብርና መዘመን፣ የሥራ ፈላጊዎችን ብቃት ለማሳደግ እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን ቁልፍ ሚና ይጫወታል። እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ አዝማሚያዎች እየተለወጡ በመጡ ቁጥር ዘላቂነት ያለው፣ የሕይወት ዘመን ክህሎትን በመደገፍ ራስን ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋራ በማላመድ ችግርን መቋቋም የሚያስችል ኢኮኖሚ ለመገንባት ያስችላል። ሀገራት ብቃትን መሠረት ያደረገ የሥልጠና ሥርዓትን በመዘርጋት ዘላቂነት ያላቸውን የሥልጠና ሞዴሎችን በመተግበር በፍጥነት እየተለዋወጠ የሚገኘውን የኢንዱስትሪ ውስጥ የሠለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎትን ለማሟላት እየሠሩ ይገኛሉ። ከዚህ አንጻር በትግበራ ላይ ያለው የ2000 ዓ.ም. ሀገር ዓቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ ዘርፉ በተበታተነ መልኩ በተለያየ ተቋማት የነበረው የሥልጠና አካሄድ እና አቅርቦት-መር የነበረውን የሥልጠና ሥርዓት ወደ ፍላጎት-መር እና ውጤት ላይ የተመሠረተ ሥርዓተ ሥልጠና መዘርጋት ችሏል፡፡ በዚህም የሥልጠና ጥራትን፣ አግባብነትን፣ ፍትሓዊ ተደራሽነትን እና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሳደግ ተሞክሯል። ሆኖም ግን ፍላጎት-መር የሥልጠና ሥርዓቱ በሥልጠና መሠረተ ልማት አለመሟላትና የነበሩትም ጊዜ ያለፈባቸው መሆን፣ የአግባብነትና ጥራት ችግር ያለበት የሙያ ደረጃና ሥርዓተ ሥልጠና ዝግጅትና ትግበራ፣ በንድፈ ሓሳብ እና በተግባር ሥልጠና መካከል ሰፊ የምጥጥን ልዩነት፣ ለተግባር-ተኮር ሥልጠና ብቁ የሆኑ አሠልጣኞች አለመኖር፣ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆን እና የጥራትና ብቃት ማረጋገጫ ሥርዓት ክፍተት ያለበት መሆኑ አሁንም ተጠቃሽ ተግዳሮቶች ናቸው። 13 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም በሀገሪቱ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የሥልጠና ፍላጎትን ለማወቅ እና ለመረዳት የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት በመዘርጋት፣ ለቀደመ ትምህርት ዕውቅና በመስጠት፣ ቅይጥ (Blended Learn ing) የሥልጠና አቀራረቦችን በመከተል፣ የተለያዩ የብቃት ማሳደጊያ አመራጮችን በማስተዋወቅ የሕይወት ዘመን ክህሎት ለማሳደግ የሚረዱ ጥረቶች እየተደረጉ ናቸው። እንዲሁም የዘርፉን ገቨርናንስ ሥርዓት ከማጎልበት አንጻርም የዘርፍ ክህሎት ካውንስል መመሥረት እና ቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ጥራትና ብቃት ያለው ሥልጠና መስጠት እንዲያስችላቸው ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ላይ ልዩና የላቀ ጥራት ያለው ሥልጠና የሚሰጡ የልህቀት ማዕከላትን በመመስረት በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ውስጥ ተከታታይነት ያለው የለውጥ እና ዕድገትን ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል። ሀገራዊ የቴክኒክና ሙያ ሥርዓቱን ከዓለም ዓቀፋዊ አዝማሚያዎች፣ ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶች እና ዘላቂ ልማት ግቦች ጋራ ለማጣጣም ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ይህ ስትራቴጂ የኢንዱስትሪ እና ሥልጠና ተቋማትን ትስስር ማጠናከር፣ የጥራት ማረጋገጫ ሥርዓትን ማሻሻል፣ የምዘና ሥርዓቱን ከሕጸጾች የነጻ ማድረግ እና የገበያ ፍላጎትን መሠረት ያደረጉ ሥልጠና ዕድሎችን ማስፋት ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። 1.1.3. የስትራቴጂው አስፈላጊነት የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ በአዲስ መልክ እንዲዘጋጅ አስፈላጊ ካደረጉት ምክንያቶች መካከል የሥልጠና ሥርዓቱ በፍጥነት ከሚለዋወጠው የሀገር ውስጥና ዓለም ዓቀፍ የሥራ ገበያ ፍላጎት ጋራ ለማጣጣም አስፈላጊ በመሆኑ፣ እየጨመረ ባለው የሕዝብ ቁጥር ዕድገት እና ጫና ምክንያት ለሥራ ገበያው ፍላጎት በአግባቡ ምላሽ ለመስጠት፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ምኅዳሩ ላይ በፍጥነት እየመጣ ያለው ለውጥ በተለይም ኢኮኖሚው ወደ ዲጂታልና አረንጓዴ ኢኮኖሚ በፈጣን ሽግግር ላይ መሆኑ እና ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን የሰው ኃይል በዲጂታልና አረንጓዴ ክህሎት ብቁ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡ ስለሆነም የ2000ዓ.ም. ስትራቴጂ ትግበራ ላይ የተገኙ ተሞክሮዎችን በማካተት እንዲሁም በ2015ዓ.ም. የጸደቀውን የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ እና በ2017ዓ.ም. የወጣውን የኢትዮጵያ ትምህርትና ሥልጠና የብቃት ማዕቀፍ ባሉ የቅርብ ጊዜ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን መሠረት በማድረግ፣ ሥርዓተ ሥልጠናዎችን ከወቅቱ የሥራ ገበያ ፍላጎት ጋራ በማጣጣም፣ የቴክኒክና ሙያ ገቨርናንስ ሥርዓትን በማጎልበትና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ፣ የሥልጠና ፕሮግራሞች ለኢንዱስትሪው ተለዋዋጭ ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ በማድረግ፣ ከቴክኖሎጂ ዕድገት ጋራ የተጣጣመ እና ሥራ ፈላጊ ወጣቶችን ብቁ የሚያደረግ መሆናቸውን ማረጋገጥን ያለመ ነው። በተጨማሪም የሥልጠና መሠረተ ልማትን በማሻሻልና በማዘመን እና የጥራትና የብቃት ማረጋገጫ ሥርዓት ክፍተቶችን ለመሙላት ያለውን አስፈላጊነት መሠረት ያደረገ ሲሆን፣ እንዲሁም ለኢኮኖሚያዊ ለውጥና ለዘላቂ ልማት ግቦች መጠቀም የሚያስችል ይሆናል። በተጫማሪም ስትራቴጂው አዳዲስ የማሻሻያ ተነሣሽነቶችንም ተግባራዊ ማድረግ ላይ ትኩረት ይሰጣል። እነዚህም በዋናነት ተቋማትን አንደ አዲስ የጥቃቅንና አነሰተኛ ኢንትርፕራይዞች/ ኩባንያዎች የሚፈለፈሉባቸው ማዕከሎች በማድረግ፣ በሥራ ገበያ ፍላጎት የሚመራና ሥራ ፈጣሪነትን የሚያበረታታ ሞዴል በመፍጠር እንዲሁም ዕሴት-ሰንሰለት ተኮር ሥልጠናዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ይከናወናሉ። ስትራቴጂው አካባቢያዊ እና የዘርፍ ልየታ (Zoning and Dif ferentiation ) ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ በመተግበር በክልል የልማት ዓቅም ላይ አጽንዖት ይሰጣል፣ ሀገር ወዳድነትንና የሙያ ሥነ-ምግባርን በሰው-ተኮር ሥርዓተ ሥልጠና ጋራ በማቀናጀት ፣ እና በተለይም በፋብሪኬሽን ኢንጂነሪንግ መስክ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ቅድሚያ ይሰጣል። ከዚህም በላይ፣ ስትራቴጂው ለዘመናዊነት የሚያግዙ ጠንካራ የግል እና መንግሥት ትብብሮችን በንቃት ያስተዋውቃል፣ እንዲሁም ቀጣይነት ያለው መላመድንና የሀብት አቅርቦትን ለማረጋገጥ ሁሉን ዓቀፍ የሆነ የክህሎትና የቴክኖሎጂ ባንክ መመሥረት ላይ ትኩረት ያደርጋል። በተጨማሪም አዲሱ ስትራቴጂ ውስን የሆነ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ፣ በቂ ያልሆነ መሠረተ ልማትና የጥራት ማረጋገጫ 14 ክፍተቶችን የመሳሰሉ ለረጅም ጊዜ የቆዩ ሥርዓታዊ ተግዳሮቶችን ይፈታል፣ በተመሳሳይ ጊዜም የኢኮኖሚ ለውጥና ዘላቂ ልማት ዕድሎችን ይጠቀማል። ስትራቴጂው ተለዋዋጭ፣ ሥራ ፈጣሪና የኢንዱስትሪ ዕድገትን ሊያነሳሳ የሚችል የሰው ኃይል ለማፍራት የፈጠራ ልምዶችን፣ ዲጂታል ክህሎቶችንና ብቃት ላይ የተመሠረተ ሥልጠናን በማዋሐድ ላይ ያተኩራል። በአጠቃላይ ጠንካራ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎን እና ቅንጅታዊ አሠራርን በማጎልበት፣ ሥልጠናዎች ቅድሚያ ትኩረት ከሚሰጣቸው የልማት አጀንዳዎች ጋራ በማጣጣም፣ የሥልጠና ሥርዓቱን ለማኅበራዊ ተሳትፎ፣ ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ወሳኝ አንቀሳቃሽ ሞተር ለማድረግ ታሳቢ ያደረገ ነው። 1.1.4. የስትራቴጂው ዓላማዎች የዚህ ስትራቴጂ ዋነኛ ዓላማ የኢትዮጵያን የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት ወደ ከፍተኛ ጥራትና የሥራ ገበያ ፍላጎት ተኮር እንዲሆን ማሸጋገር ነው። ይህም ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለማኅበራዊ ልማት እንደ ዋና አንቀሳቃሽ ኃይል ሆኖ እንዲያገለግል ያስችለዋል። ስትራቴጂው በዘመናዊ ክህሎቶች (እንደ አረንጓዴና ዲጂታል ክህሎቶች) የተካነ፣ በፈጠራ ከህሎት የተካነ ሥራ ፈጣሪና ሀገር-ወዳድ የሆነ ትውልድ ለመፍጠር ያለመ ነው። ይህ የሚሳካው የቴ/ሙ/ሥ ተቋማት የራስ ገዝ አስተዳደርና የፋይናንስ አቅም እንዲኖራቸው በማድረግ፣ ለሁሉም ዜጎችም እኩል ዕድል በማረጋገጥ ነው። በተጨማሪም፣ ከግሉ ዘርፍና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋራ የሚደረጉ ስትራቴጂካዊ ሽርክናዎች የቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት ከሥራ ገበያው ፍላጎት ጋራ በቋሚነት እንዲጣጣም ያደርጋሉ። በመጨረሻም፣ ይህ ሥርዓት ለተፈጥሮኣዊም ሆነ ሰው-ሠራሽ ተግዳሮቶች የማይበገር ጠንካራና ተቋቋሚ (resil ient) እንዲሆን ያለመ ሲሆን፣ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትና ዓለም ዓቀፍ ተወዳዳሪነት ቁልፍ ሚና እንዲጫወት ያጠናክራል። 1.2 የነባራዊ ሁኔታ ትንተና የኢትዮጵያ የቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት ነባራዊ ሁኔታ ትንተና አኃዛዊና ገላጭ መረጃዎችን በመጠቀም፣ ከባለድርሻ አካላት ጋራ የተካሄዱ ዐውደ ጥናቶች (ጥንካሬዎች፣ ድክመቶች፣ ዕድሎች እና ስጋቶች/ SWOT/PESTEL)፣ በተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የተካሄዱ ሴሚናሮች፣ ከባለሙያዎች ጋራ የተካሄዱ ወርክሾፖች፣ ሪፖርቶችና ነባር የምርምር ውጤቶች ላይ የተካሄዱ ፍተሻዎች ጥራት ያለው ግንዛቤን አስጨብጧል። ይህ ትንተና የቴ/ሙ/ሥ ሥርዓቱን ጥንካሬ፣ ተግዳሮቶች እና ዕድሎች ይዳስሳል፣ መሻሻል የሚገባቸውን ርዕሰ ጉዳዮች ለይቶ የሥርዓቱን አጠቃላይ ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ መንገዶችን ይጠቁማል። ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች የተገኙ መረጃዎችን ለመተንተን ባለ ሦስት ማዕዘን የንጽጽርና ትንተና አካሄድ በመጠቀም የኢትዮጵያን የቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት ወቅታዊ ሁኔታ አጠቃላይ ምስል ማሳየት ተችሏል። እንደ ወጥነት የጎደለው ሥርዓት፣ የበጀት ድልድል (5% የትምህርት ፈንድ)፣ የሥልጠና አግባብነትና ጥራት ጉድለት፣ የጥናትና ምርምር ክፍተቶች፣ ደካማ የኢንዱስትሪ ተሳትፎ ያላቸው የቴ/ሙ/ሥ ሥርዓታዊ ተግዳሮቶች ተለይተው እንዲታወቁ አስችሏል። ሥልጠናውን ከሥራ ገበያ ፍላጎቶች ጋራ ለማጣጣም በቅንጅታዊ አሠራር፣ በመሠረተ ልማት ማሟላት እና በፖሊሲ ላይ ለሚደረጉ ማሻሻያዎች የሚኖሩትን ዕድሎች አጉልቶ አሳይቷል። 1.2.1 ገቨርናንስ እና ቅንጅታዊ አሠራር መንግሥት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት ለሀገራዊ ልማት ወሳኝ ሚና እንዳለው ስለሚገነዘብ ሥርዓቱን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑን በተለያዩ ተግባራት ሲገለጽ ቆይቷል። በመሆኑም በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ እና በተለያዩ ዘርፎች መካከል የሚኖር የተቀናጀ አስተዳደርን የሚያጎሉ ሁሉን ዓቀፍ ፖሊሲዎች በማዘጋጀት ሥርዓቱን ለማዘመን ጥረት መደረጉ አንዱ ማሳያ ነው። በዚህም መሠረት የሥልጠና ፕሮግራሞችን ውጤታማነት ለማሳደግ በመንግሥት አካላት፣ በሥልጠና ተቋማት፣ በኢንዱስትሪዎች እና በአካባቢው ማኅበረሰብ መካከል የትብብር አጋርነቶች እየተጠናከሩ መሄዳቸው መልካም መሆኑ ታይቷል። 15 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም ነገር ግን አሁንም ቢሆን ተቀናጅቶ ለጋራ ዓላማ ከመሥራት አኳያ በተለይም በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችና ዘርፎች፣ በሥልጠና ተቋማት እና በኢንዱስትሪ ባለድርሻ አካላት መካከል ያለው ቅንጅት ውስንነት ያለበት ነው። ቅንጅታዊ አሠራር ሥርዓት አለመጠናከር፣ የሥልጠና ተቋማት የአሠራር ብቃት ማነስ፣ የውሳኔ መዘግየት እና ለተለዋዋጭ የሥራ ገበያ ፍላጎቶች ምላሽ ለመስጠት አለመቻል ጎልተው የሚታዩ ክፍተቶች ናቸው። በተጨማሪም ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና በኅበረተሰቡ ቀዳሚ ተመራጭ አለመሆን፣ መጠነ ሰፊ የሆነ ዘላቂ ፋይናንስ ምንጭ መፍጠር አለመቻል፣ ገቨርናንስ ሥርዓቱ ግልጽነት እና ተጠያቂነት የጎደለው በመሆኑ፣ በባለድርሻ አካላት መካከል አለመተማመንን የሚፈጥር እና ሁሉን ዓቀፍ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶችን የሚያደናቅፍ ሆኖ ተገኝቷል። ለአብነትም ከ2014 ዓ.ም. እስከ 2016 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተሳትፎ በ47.5 በመቶ(47.5%) የጨመረ ቢሆንም ከአጠቃላይ ለትምህርት ከሚበጀተው በጀት አንጻር 5 በመቶውን(5%) ብቻ የሚመደብለት መሆኑ እድገቱን ገቶታል። በተመሳሳይም በ2016 ዓ.ም. 1,011 የግል የሥልጠና ተቋማት የነበሩ ሲሆን ተቋማቱ በሥርዓተ ሥልጠና ቀረጻ እና ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ ያለቸው ግንዛቤና ተሳትፎ ውስንነት አለበት፡፡ አርባ ከመቶ (40%) በላይ የአገሪቷ ወረዳዎች የሥልጠና ተቋም ተደራሽ ያልሆኑ በመሆናቸው የገጠር ነዋሪዎችን የቴ/ሙ/ሥ ፍትሓዊ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ አድርጓቸዋል። በተመሳሳይ በክልሎች ያለው የሥልጠና ተቋማት ሥርጭትና ተደራሽነት ምጣኔ የተዛባ ነው፡፡ 1.2.2 የሥልጠና አግባብነትና ጥራት ኢትዮጵያ በብቃት ላይ የተመሠረተ ሥልጠናን በማቅረብ ክህሎትን በማዳበርና የሥልጠና ፕሮግራሞችን ከኢንዱስትሪ ፍላጎቶች ጋራ በማጣጣም ረገድ ዕድገት አሳይታለች። በሙያ ደረጃና ሥርዓተ ሥልጠና ዝግጅት ሂደት የኢንዱስትሪውን ተሳትፎ በማሳደግ የሥራ ገበያ ፍላጎት የሚያሟላ ሥልጠናን ተገቢነትን ለማሻሻል ጥረት ቢደረግም አሁንም ቢሆን ሠልጣኞች ከሥልጠና ተቋማት ይዘውት በሚወጡት እና ኢንዱስትሪው በሚፈልገው ብቃት መካከል ጉልሕ ልዩነት አለ። የሥልጠና ተቋማት ተለዋዋጩን የሥራ ገበያ ፍላጎት ለመሟላት በቂ በሆነ መልኩ ያልተደራጁ በመሆናቸው ለሥራ ዝግጁ የማያደርግ ብቃት ያላቸው ምሩቃን እንዲፈሩ በማድረግ ሥራ ዐጥነት ከሠልጠኑበት የሙያ መስክ ውጭ እና ከደረጃ በታች የተሠማሩ ባለሙያዎች ምጣኔ ከፍ እንዲል አድርጎታል። በተጨማሪም የሥልጠና ተቋማት እና የኢንዱስትሪ አጋርነትና ቅንጅት ውስንነት ያለበት በመሆኑ፣ የሥልጠና መሠረተ ልማቶች ጊዜ ያለፈባቸው እና በበቂ ሁኔታ አለመሟላት፣ የሥልጠና ፕሮግራሞች ዝግጅት በአግባቡ የኢንዱስትሪውን የበቃ የሰው ኃይል ፍላጎት ምላሽ የማይሰጡ በመሆኑ ችግሩ ይበልጥ እንዲባባስ እና የሥልጠናው ውጤታማነት ጎድሎታል። አሠልጣኞች የተግባር-ተኮር የማሠልጠን ዘዴ እና ኢንዱስትሪ-ተኮር ልምድ ስለሚጎድላቸው በተጨባጭ ውጤት ማምጣት ትልቅ ፈተና ሆኗል። ይህም በመሆኑ በተቋማት ውስጥ የሚሰጠው ሥልጠና ጥራት የለውም ተብሎ በመታመኑ ተቋማት ሰልጣኞቻቸውን ለሥራ ገበያው በማዘጋጀት ረገድ ባላቸው ውጤታማነት ላይ ጉልህሕ የሆነ ተጽዕኖ እያሳደረባቸው ይገኛል። በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ 70% ተግባር ተኮር ከኢንዱስትሪው ጋራ በትብብር የሚሰጥ ሥልጠና ስልት ተግባራዊ ለማድረግ ታቅዶ እየተሠራ ቢሆንም የሥልጠና መሠረተ ልማቶች በበቂ ሁኔታ ባለመሟላታቸው ምክንያት ብቃት ላይ የተመሠረተ ሥልጠና ሞዴልን (CBT model) በመተግበር ረገድ ተግዳሮቶች ገጥመውት ቆይቷል። የዲጂታል ክህሎት እና የአረንጓዴ ክህሎት በቴክኒክና ሙያ ሥርዓተ ሥልጠና ውስጥ በበቂ ሁኔታ ተካተው ሲሰጡ ያልነበረ በመሆኑ ሥርዓተ ሥልጠናው የነበረበትን ችግር፣ አግባብነትና ጥራት የማረም እና የማስተካከል ሥራ ይጠይቃል፡፡ 16 1.2.3 ለሥራ ብቁ የሚያደርጉ ክህሎቶችን ማዳበር የቴ/ሙያ ሥልጠና አጠናቃቂዎችን ወደ ሥራ የመሠማራት ዕድላቸውን ከፍ ለማድረግ ኢንተርንሺፕ፣ አፓረንትሺፕ እና የሥራ ላይ ልምምድ ዕድሎችን ማስፋት ያስፈልጋል። የሥልጠና አጠናቃቂዎች የገሓዱን ዓለም የሥራ ሁኔታ በበቂ ሁኔታ የሚላመዱበትን ዕድል ለመፍጠር ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ወሳኝ ነው። የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና አጠናቃቂዎች በያዙት ክህሎትና በአሠሪዎች ፍላጎት መካከል እስካሁን ድረስ ያልተፈታ ችግር አለ። እንደ እንዱስትሪው ግምገማ ከሆነ ከቴክኒካል ብቃት ባሻገር እንደ ውጤታማ ተግባቦት፣ ችግር ፈችነት፣ በሳል አስተሳሰብ፣ ፈጠራ እና ሥነ-ባሕሪያዊ ክህሎቶች ጉድለት እንደሚታይባቸው ይገልጻሉ። ሀገሪቷ የሥራ ዕድል አማራጮችን ለማስፋት የሥራ ላይ ልምምድ ዕድሎችን ማስፋት፣ የአሠልጣኞችን አቅም ማጎልበት፣ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓትን ማጠናከር እና በአጠቃላይ የሥራ ፈጠራ ዕድል ማሳደግና ማበረታታት ቢገባትም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ከኢንዱስትሪ ጋራ ጠንካራ የትስስር፣ የትብብር እና አጠቃላይ የጋራ የሥራ ፈጠራ ሥልጠና ማዕቀፎች ስለሌላቸው ሠልጣኞቹ የሥራ ፈጠራ ዓቅማቸውን ማጎልበት እንዳይችሉ አድርጓቸዋል። 1.2.4 ምርምር ፈጠራ እና የማኅበረሰብ አገልግሎት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ከምርምር ተቋማት፣ ኢንዱስትሪዎች እና የአካዳሚክ ተመራማሪዎች ጋራ የትብብርና ቅንጅታዊ አሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ኢንዱስትሪ-ተኮር ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የሥልጠና ዘዴዎችን ለማሻሻል ትብብር እንዲያደርጉ ቢጠበቅም የዘርፉ የምርምር እና የፈጠራ ዓቅም በቂ ባልሆነ የፋይናንስ ድጋፍ እና የሙያዊ ብቃት ማነስ ምክንያት አገልግሎቱ ውስንነት ያለበት ሆኗል። በሥልጠና ተቋማት ውስጥ ለምርምር ተግባር የተቋቋሙ ማዕከላት አለመኖር እንደ ግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ እና ታዳሽ ኃይል ባሉ ወሳኝ ዘርፎች ውስጥ ፈጠራን ለማጎልበት የሚያስችል የኢንዱስትሪ ትብብር ሥርዓት እንዳይኖር አድርጎታል። በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ኢንዱስትሪዎች እና ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች መካከል ውጤታማ የዕውቀት ሽግግር አለመኖር ተቋማቱ ለዓለም ዓቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎች እና የቴክኖሎጂ እድገቶች ያላቸውን ተደራሽነት ከመገደቡም በላይ ቅድሚያ የተሰጣቸውን ዘርፎች ከጊዜው ጋራ አብሮ የመዘመንን ዕድል አናሳ አድርጎታል። የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን ተመራጭነት የሚያስተዋውቁ የውጭ ግንኙነት ሥራዎች በሚገባው ልክ ባለመሆናቸው በኅብረተሰቡ ዘንድ ስለ ሙያ ሥልጠና ያለውን አመለካከት ለመቀየር አስቸጋሪ አድርጎት ቆይቷል። በመሆኑም ዘርፉን በሁሉም መልኩ ለማሻሻል የምርምር እና የፈጠራ ማዕከላትን ማቋቋም፣ በግሉ ዘርፍ የሚደገፍ ምርምርን ማበረታታት እና የቴ/ሙ/ሥን ቅቡልነት ለማሳደግ የግንዛቤ ማስጨበጫ የንቅናቄ ሥራዎችን መሥራት አስፈላጊ ነው። 17 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም ክፍል ሁለት 18 ክፍል ሁለት: ርዕይ ተልዕኮ እና ዓላማዎች 2.1. ርዕይ፣ ተልዕኮ፣ ዋና ዋና ዕሴቶች እና መርሖች ርዕይ በ2027 ዓም፣ የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ዋና አንቀሳቃሽ የሚሆን፣ ለወደፊቱ አረንጓዴና ዲጂታል ኢኮኖሚዎች ዝግጁ የሆነ በክህሎት የበለጸገ፣ ሀገር ወዳድ፣ ሥራ ፈጣሪና ከፍተኛ ፈጠራ ችሎታን የተላበስ የሰው ኃይልን የሚያፈራ ሆኖ ማየት። ተልዕኮ ከፍተኛ ጥራት ያለውና በሥራ ገበያ ፍላጎት የሚመራ ሥልጠና በመስጠት፣ በክህሎት የበለጸገ፣ ሀገር ወዳድና ሥራ ፈጣሪ፣ ችግር ፈቺ የሆነ እና የፈጠራ ችሎታ የተላበስ የሰው ኃይል እና ቴክኖሎጂ በማፍራት የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዕድገትና ዘላቂ ልማት ማረጋገጥ ነው። ዋና ዋና ዕሴቶች አካታች፡ ማኅበራዊም ሆነ ኢኮኖሚያዊ፣ አካላዊም ሆነ ሌሎች መሰናክሎች ሳይገድባቸው ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ለሥልጠና እኩል ዕድል ማግኘታቸውን ማረጋገጥ፤ ልህቀት፡ የሥራ ገበያን ደረጃዎች የሚያሟላና ዓለም ዓቀፍ የጥራት ደረጃ ያለው ሥልጠና ለመስጠት ጽኑ ቁርጠኝነት ማሳየ፤ ፈጠራ፡ ከሀገር ውስጥም ሆን ከዓለም ዓቀፍ የሥራ ገበያ ፍላጎቶች ጋራ የሚጣጣሙ አርቆ አሳቢ የሆኑ የፈጠራ መፍትሔዎችን ማፍለቅ፤ ለስኬት ማብቃት፡ ግለሰቦች ከሀገር ውስጥም ሆን ከዓለም ዓቀፍ በሥራ ገበያ ላይ ተወዳዳሪና ስኬታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ብቃት (ዕውቀት፣ ክህሎት እና ዝንባሌ) ማስታጠቅ፤ ሀገር ወዳድነት፡ ለእያንዳንዱ ሠልጣኝ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት አስተዋጽኦ እንዲያደርግ የሚያነሳሳ ጥልቅ ቁርጠኝነት መፍጠር፤ 19 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም 21 20 2.2 የስትራቴጂው ትኩረቶች እና ዓላማዎቻቸው 2.2.1 የስትራቴጂው ትኩረቶች ይህ ስትራቴጂ በጥልቅ ትንተና ላይ ተመሥርቶ በአራት ዋና ዋና ትኩረቶች ዙሪያ የተዋቀረ ሲሆን፣ የሥልጠና ሥርዓቱን ወደ ምላሽ ሰጭነት፣ ጥራት ያለውና አካታች የሆነ የክህሎት ልማትና የሥራ ሥምሪት ማስፋፊያ መንገድ ለመለወጥ ያለመ ነው። ትኩረት 1 የቴ/ሙ/ሥ ገቨርናንስ ሥርዓትን ማጎልበት፤ ለትብብር፣ ለፖሊሲ አቅጣጫ እና ለተጠያቂነት አስፈላጊ የሆኑ ማዕቀፎችን ማጠናከር፣ ባለድርሻ አካላትን ማሳተፍ፣ ሀብትን ማሰባሰብ፣ የግል ዘርፍን ተሳትፎ ማሳደግ እና የሥርዓቱን ገጽታ መገንባት ላይ ያተኩራል። ትኩረት 2 የቴ/ሙ/ሥ አግባብነት እና ጥራትን ማሻሻል: የሥራ ገበያ ፍላጎት ዳሰሳ፣ የሙያ ደረጃ ምደባ፣ ሥርዓተ-ሥልጠና ዝግጅት፣ የማሠልጠኛ መሣሪያዎች ዝግጅት፣ ምዘናና የምስክር ወረቀት አሰጣጥ፣ የአሠልጣኞች ሥልጠና እና የዲጂታል ሽግግርን በማካተት የሥልጠናውን ጥራትና አግባብነት ማረጋገጥ። ትኩረት 3 ለሥራ ዝግጁ የሚያደርጉ ክህሎቶችን ማዳበር: ሥልጠና አጠናቃቂዎች ለሥራ ገበያ በበቂ ሁኔታ ዝግጁ እንዲሆኑ ኢንተርንሺፕ፣ አፓረንትሺፕ፣ የሥራ ላይ ልምምድ፣ የሥራ ፈጠራ ዕድገት፣ የሙያ ማማከርንና የመደገፍን አገልግሎት እና ለቀደመ ትምህርት ዕውቅና መስጠትን በማበረታታት ከሥልጠና ወደ ሥራ ቀጥተኛ ሽግግርን፤ ልል ክህሎትን (Soft skills) ኢንተርፕረነርሽፕ እና መሰል ክህሎቶችን ማስታጠቅ። ትኩረት 4 የምርምር እና የፈጠራን ሥነ-ምኅዳር ማጠናከር: ቴ/ሙ/ሥ በምርምርና ቴክኖሎጂ በመደገፍ ወደ ኢኮኖሚ ዕድገት አቀጣጣይ ኃይልነት እንዲሸጋገር ማድረግ ይገባል። ምርምርን በማሳደግ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማካሄድ፣ የማኅበረሰብ አገልግሎትን በማጠናከር እና የተሰጥኦ ዕድገትን በማጎልበት የኢንዱስትሪውን ክፍተት መሙላት ተገቢ ይሆናል። መርሖዎች የተሰጥዎ ልማት: ከግለሰቦች ተሰጥዎና ዝንባሌ ጋራ በሚጣጣም መልኩ ለግል የተበጀና ውጤታማ የክህሎት ልማት መስጠት፤ ስልታዊ ትብብር: በተባባሪነትና መሠረተ ሰፊ ትብብር ላይ ያተኮረ የብዝኅ ተሳትፎን በማረጋገጥ ለሥራ ገበያው ፍላጎት ምላሽ የሚሰጡ የሥልጠና መርሓ ግብሮችን ለመንደፍ ከባለድርሻ አካላት ጋራ በንቃት መሥራት፤ ወደፊት ተኮር ክህሎቶች: ለአረንጓዴና ለዲጂታል ኢኮኖሚዎች የሚያዘጋጁ ክህሎቶችን ቅድሚያ በመስጠት፣ የቴክኖሎጂንና የሀገር-በቀል ዕውቀትን ማዋሐድ፤ ሥራ ገበያ ተኮር/ ዕሴት ሰንሰለት መሠረት ያደረገ የቴ/ሙ/ሥ በማረጋገጥ የሥራ ገበያውን አሟጦ በመጠቀም የሥራ ገበያ ጉድለትን መሙላት፤ የሥራ ዕድልን ማስፋት: ግለሰቦች ለቅጥርም ሆነ ለራስ ሥራ ለመፍጠር የሚያስችላቸውን የሥራ ፈጠራ አስተሳሰብና ክህሎት ማስታጠቅ፤ ቀጣይነት ያለው ሥልጠና: በሥራ ዘመናቸው ሁሉ ሠራተኞች ከሚለዋወጡ የሥራ ፍላጎቶች ጋራ እንዲላመዱ የሚያስችል የሕይወት ዘመን ክህሎት ሥልጠና ሥርዓት መፍጠር፤ የዲጂታል ቴክኖሎጂን መጠቀም: የሥልጠና አቅርቦትን፣ አመራርንና አጠቃላይ ሥርዓቱን ለማሻሻል ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ መጠቀም፤ ከሀገራዊና አካባቢያዊ ቅኝት ጋራ ማጣጣም፡ የሥልጠና ፕሮግራሞቻችን ሀገራዊና ከአካባቢያዊ የኢንዱስትሪና የልማት ግቦች ጋራ በቀጥታ የተጣጣሙ መሆናቸውን ማረጋገጥ፤ ተለማጭነት: በሥራ ገበያ እና በቴክኖሎጂ ላይ ያለውን ተለዋዋጭነት እና የተጠቃሚውን ፍላጎት መሠረት በማድረግ ብቁ እና ተፈላጊ የሆነ የሰው ኃይልና ቴክኖሎጂ ማቅረብ፤ ለኢ-መደበኛ ዘርፍ ትኩረት መስጠት፡ ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት በኢ-መደበኛ (informal) ዘርፍ የተሠማሩ ዜጎችን ብቃት በማሳደግ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ወደ መደበኛ ሥርዓት ማሸጋገር፣ ዘላቂነት: የቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት የረጅም ጊዜ ዘላቂ ልማትና ማኅበራዊ ዕድገትን የሚደግፍ መሆኑን ማረጋገጥ፤ ኢንተርፕርናል ኦረንቴሽን፡ ቴ/ሙ/ሥ ተቋማት በተጨባጭ አዳዲስ የንግድ ሥራዎችን ለመፍጠርና ለማሳደግ፤ እንዲሁም የቴክኖሎጂ መፈልፈያ እና ማምረቻ ማዕከል እንዲሆኑ ማስቻል:: የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም 23 22 የትኩረት መስክ ዓላማዎች የቴ/ሙ/ሥ አግባብነት እና ጥራትን ማሻሻል • የሙያ ደረጃ ምደባና ሥርዓተ ሥልጠናን ማሻሻል (ለሥራ ገበያ ፍላጎት ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት)፤ • በማኅበረሰብ የሥልጠና ፍላጎቶች እና የክህሎት ክፍተቶች ላይ ተመሥርቶ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት የሚመራበት ሥርዓት መዘርጋት፤ • የቴ/ሙ/ሥ አተገባበር ሥርዓትን ማሻሻል (የተግባር ተኮር ሥልጠናን ለማዳበር)፤ • የብቃት ምዘናና የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ሥርዓቱን ማዘመን (ሚዛናዊ ዕውቅና ለማረጋገጥ)፤ • የአሠልጣኞችና አመራሮች ብቃት ማሻሻያ ሥርዓት ማጠናከር (የማሠልጠን ጥራትን ለማሳደግ)፤ • በሠልጣኞች ዘንድ ጠንካራ የሥራ ሥነ-ምግባርና የሀገር ወዳድነት ስሜትን ማጎልበት፤• ስትራቴጂያዊ የሙያ ሥልጠና አካባቢ ልየታ (Zon ing and Differentiation) ሥርዓት በመተግበር ተቋማት በአካባቢያቸው የኢኮኖሚ ጸጋ ላይ ቅድሚያ የሚሰጥ የሥልጠና ፕሮግራሞችና ሙያዎች ላይ እንድያተኩሩ ማድረግ፤ • መደበኛ ባልሆኑ ዘርፎች የክህሎት ማሻሻያ ሥርዓትን ተደራሽ ማድረግ (የክህሎት ክፍተት ለመቅረፍ)፤ • የቴ/ሙ/ሥ ዓለም አቀፋዊነትንና ክልላዊ ቅንጅትን ማፋጠን (የሠለጠነውን የሰው ኃይል ተዟዙሮ የመሥራት ዕድል ለማመቻቸት)፤ • በቴ/ሙ/ሥ/ ተቋማት ዲጂታላይዜሽንን ማሳደግ (ጥራትና ውጤታማነትን ለማሳደግ) አረንጓዴ የቴ/ሙ/ሥ ፕሮግራምን ማፋጠን (ዘላቂ ልማትን ለማምጣት)፤ • የሀገር-በቀል ዕውቀቶችንና ክህሎቶችን በቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት ውስጥ በማዋሃድና በመጠቀም (የዕደ ጥብብ ባለሙያዎችን ለማሳደግ እና ለማቆየት)፤ እና • ችግርን መቋቋም የሚችል የቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት መገንባት (ዘርፉ ለአደጋ ምላሽ ሰጪ መሆኑን ለማረጋገጥ) ናቸው፡፡ 2.2.2 የስትራቴጂው ዓላማዎች እያንዳንዱ የቴ/ሙ/ሥ ስትራቴጂ ትኩረቶች ዝርዝር ዓላማ የሚከተሉትን ጉዳዮች ያካትታል:: የትኩረት መስክ ዓላማዎች የቴ/ሙ/ሥ ገቨርናንስ ማጠናከር • የቴ/ሙ/ሥ ሕጋዊና ተቋማዊ አደረጃጀትን ማጣጣም (ግልጸኝነት እንዲኖረው እና ያሉ ድግግሞሾችን ለማስቀረት)፤ • የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ትብብር ማጠናከር (የጋራ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ)፤ • የኢንዱስትሪ አግባብነትን ለማረጋገጥ በሀገር ዓቀፍ የቴክኒክና ሙያ ገቨርናንስ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማጠናከር፤ • በቴ/ሙ/ሥ አመራር ሥርዓት ውስጥ የዜጎችን እና የማኅበረሰብ ተሳትፎን ተቋማዊ ማድረግ፤ • የተቋማዊ ራስን የመቻል ዓቅምን ለማጎልበት የሀብት ማሰባሰብና አጠቃቀምን ማሳደግ፤ • መሠረተ ልማትን ማሻሻልና ማሳደግ (ምቹ የሥልጠና ከባቢን ለማረጋገጥ)፤ • የጥራት ማረጋገጫ ሥርዓቱን ማሳደግ (የሥልጠና ወጥነትን ለማረጋገጥ)፤ • ተደራሽነትንና ፍትሐዊነትን ማስፋፋት (አካቶነትንና እኩል ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ)፤ • የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን ገጽታ ማሻሻል (ዕሴቱንና ሳቢነቱን ለማሳደግ)፤ • የመረጃ አያያዝ እና አጠቃቀም ሥርዓትን ማዘመን (በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ አሰጣጥን ለማጠናከር፤ እና • የክትትል፣ የግምገማ፣ የተጠያቂነትን እና ተሞክሮ ቅመራ (MEAL) ሥርዓትን ማጠናከር (ቀጣይነት ያለው መሻሻል ለማረጋገጥ) ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም 25 24 ክፍል ሦስት የትኩረት መስክ ዓላማዎች ለሥራ ዝግጁ የሚያደርጉ ክህሎቶችን ማዳበር • ሥራ ፈጣሪነትንና በሥራ ለይ ምርታማነትን የሚጨምሩ እና የሥልጠና አጠናቃቂዎችን ተለማጭነት እና ተላማጅነት(Adaptability) የሚያሳድጉ ልል ክህሎቶችንና የንግድ ሥራ ፈጠራ ክህሎቶችን ማስፋፋት፤ • የሙያ ማማከርና ድጋፍ አገልግሎትን ማሻሻል (ሠልጣኞች የሙያ ምርጫ ውሳኔያቸው በመረጃ የተደገፈ መሆኑን ለማረጋገጥ)፣ • ማኅበረሰቡን መሠረት ያደረጉ የሥራ ላይ ልምምድ (communi ty-based apprenticeships) እና የትብብር ሥልጠና (Cooperative Training) ማስፋፋት ፤ • ሀገራዊ የክህሎት ባንክ በማቋቋም፣ የክህሎት ክምችትና ዝውውር ማጎልበት፤ • ቀድሞ ለተገኘ ዕውቀት (RPL) ዕውቅና የሚሰጥና ቀጣይነት ያለው የሙያ ዕድገትን የሚያሳልጥ ጠንካራ ሥርዓት መዘርጋትና መተግበር፤ እና • ዓለም ዓቀፍ የሥራ ገበያ ዕድሎችን ማሳደግ (ለሠለጠኑ ሠራተኞች የውጭ ሀገር የቅጥር ዕድሎችን ለማስፋፋት) ናችው፡፡ የምርምር፣ የፈጠራና የማኅበረሰብ አገልግሎት ሥነ-ምኅዳር ማበልጸግ • የቴ/ሙ/ሥ የምርምር ሥርዓተ-ምኅዳርን ማሳደግ (አዳዲስ የፈጠራና ዕውቀት አመንጭነትን ለማስፋፋት)፤ • በዜጎች የሚመሩ ፈጠራዎችንና የማኅበራዊ ፈጠራ ማዕከላትን ማበረታታትና መደገፍ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደትን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ መተግበር፤ • የማኅበረሰብ አገልግሎቶችን ማስፋፋትና ማጠናከር (በኢንዱስትሪና በቴ/ሙ/ሥ መካከል ያለውን ክፍተት ለማጥበብ)፤ እና • በተሰጥኦ ላይ የተመሠረተ ሥልጠናና ምደባ ሥርዓት በመተግበር ተሰጥኦን መለየትና ማዳበር ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም ክፍል ሦስት ቁልፍ ጉዳዮች፣ ስትራቴጂዎች እና የሚጠበቁ ውጤቶች ይህ ክፍል የኢትዮጵያ ቴ/ሙ/ሥ ስትራቴጂክ ግቦችን ለማሳካት በአራቱ ስትራቴጂክ የትኩረት መስኮች ሥር ቁልፍ ጉዳዮችን፣ ስልታዊ አካሄዶችን እንዲሁም ሊተገበሩ የሚችሉ እርምጃዎችን እና በመካከለኛ ጊዜ ገደብ የሚጠበቁ ውጤቶችን በዝርዝር ያስቀምጣል። 3.1 ትኩረት አንድ፡ የቴ/ሙ/ሥ ገቨርናንስን ማጎልበት ቁልፍ ጉዳይ 1፡ የቴ/ሙ/ሥ ሕጋዊና ተቋማዊ አደረጃጀትን ማጣጣም የቴ/ሙ/ሥ ዘርፍ ከፌደራል እስከ ታችኛው ዕርከን በተዋረድ ያለው አደረጃጀትና ተቋማዊ ስያሜ ተናባቢ ባለመሆኑ በመረጃ ፍሰት፣ በድጋፍና ክትትል ሥርዓት ትግበራ ላይ ውስንነት ያለበት ነው፡፡ በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡ ስትራቴጂዎች ከፌደራል እስከ ታችኛው እርከን ያለው አደረጃጀት ተናባቢነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል የአሠራር ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ይተገበራል፣ በሁሉም እርከን ያሉትን የዘርፉን አደረጃጀቶች አቅም የሚገነባበት የአሠራር ሥርዓት ይዘረጋል፣ ሀገራዊ የቴ/ሙያ ተቋማት አደረጃጅቶች የሚመሩበት የአሠራር ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ይተገበራል፡፡ የሚጠበቁ ውጤቶች ከፌደራል እስከ ታችኛው ዕርከን የአደረጃጅቶችን ተናባቢነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የህግና የአሠራር ማዕቀፎች መተግበር፣ በሁሉም እርከን የአደረጃጅቶች አቅም መገንባት፤ የቴ/ሙያ ተቋማት አሠራርና አስተዳደር ወጥነት ባለው መልኩ መተግበር ይኖርበታል። ቁልፍ ጉዳይ 2፡ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ፣ ትብብር እና ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር በባለድርሻ አካላት መካከል ውጤታማ የትብብርና ቅንጅታዊ አሠራር ሥርዓት ባለመኖሩ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ውጤት እንዳያመጡ አድርጓል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች/ የክልል ሴክተር ቢሮዎች መካከል ቅንጅትን ለማሳደግ የሚያስችል የሚኒስትሮች/ የቢሮ ኃላፊዎች ፎረም/ሞች ይቋቋማል/ሉ፤ በሁሉም ደረጃ ባለብዙ ባለድርሻ አካላት የትብብር ፎረሞች ይዘጋጃሉ፤ የሴክተር የክህሎት አካላት ይቋቋማሉ፤ የልማት አጋሮች ፎረም ይደራጃል፤ ሀገራዊ የባለድርሻ አካላት ስትራቴጂካዊ የግንኙነት ማዕቀፍ ይዘጋጃል። የሚጠበቁ ውጤቶች ተቋቁመው ወደ ሥራ የገቡ የሚኒስትሮች/የቢሮ ኃላፊዎች ማስተባበሪያ ፎረም/ሞች፤ ተቋቁመው ወደ ሥራ የገቡ ሀገራዊ፣ ክልላዊ እና አካባቢያዊ ባለብዙ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት መድረኮች፤ ተደራጅተው ወደ ሥራ የገቡ የሴክተር የክህሎት አካላትም፤ ተደራጅተው ወደ ሥራ የገቡ የልማት አጋሮች ማስተባበሪያ ፎረም፤ ተዘጋጅቶ የተተግበረ ሀገራዊ የባለድርሻ አካላት ስትራቴጂካዊ የግንኙነት ማዕቀፍ ናቸው። ቁልፍ ጉዳይ 3፡ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ የግሉ ዘርፍ በቴክኒክና ሙያ ሥርዓት ውስጥ ያለው ተሳትፎ እጅግ አነስተኛ ነው። ይህም የሆነው በግንዛቤ ማነስ፣ ግልጽ ሚናዎች ባለመቀመጣቸውና ማበረታቻዎች ባለመኖራቸው ነው። በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል የምክክር መድረኮች ይመቻቻሉ፤ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ የሚያበረታታ ሁሉን ዓቀፍ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ይተገበራል፤ በአፓረንትሺፕና በኢንዱስትሪ ውስጥ በሚሰጥ ሥልጠና ለሚሳተፉ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የቴክኒክ ድጋፍ ይሰጣል፤ በሥልጠና ተቋማት የአስተዳደርና የኢንዱስትሪ አማካሪ ቦርዶች ውስጥ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ እንዲያድግ ይደረጋል። የሚጠበቁ ውጤቶች በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል የተመቻቸ የምክክር መድረክ፣ በአፓረንትሺፕና በኢንዱስትሪ ውስጥ ሥልጠና የጨመረ የግል ዘርፍ ተሳትፎ፤ በሥልጠና ተቋማትና ኢንዱስትሪው ትብብር የተዘጋጁ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና ፕሮግራሞች፤ የግል ዘርፍ ተዋናዮች በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት አስተዳደር ቦርዶች ውስጥ የጨመረ ተሳትፎዎች ይጠበቃሉ። ቁልፍ ጉዳይ 4፡ በቴ/ሙ/ሥ አመራር ሥርዓት ውስጥ የዜጎችን እና የማኅበረሰብ ተሳትፎን ተቋማዊ ማድረግ የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት ዜጎች፣ ወላጆች፣ ወጣቶችና የማኅበረሰብ አደረጃጀቶች በአመራርና ውሳኔ አሰጣጥ ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ የሚያስችል የተዋቀረ አሠራር የለውም። ይህ ክፍተት ለሥርዓቱ ተጠያቂነትን፣ ምላሽ ሰጪነትንና የሕዝብ ባለቤትነትን ይገድባል። ስትራቴጂዎች ማኅበረሰቦችን ከቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ጋራ በይፋ ለማገናኘት በወረዳና በክልል ደረጃ የማኅበረሰብ ቴ/ሙ/ሥ ምክር ቤቶችን ማቋቋም፤ ለአካባቢ ቴ/ሙ/ሥ መሠረተ ልማትና ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍ የተሳትፎ በጀት አሠራር ማስጀመር፤ የቴ/ሙ/ሥ አገልግሎት አሰጣጥን ለመከታተል የዜጎች ሪፖርት ካርዶችንና የማኅበረሰብ ውጤት መመዝገቢያዎችን ማዘጋጀት። የሚጠበቁ ውጤቶች በወረዳ/ክልል ደረጃ የሚሠሩ የማኅበረሰብ-ቴ/ሙ/ሥ ምክርቤቶች ቁጥር መጨመር፤ ከአካባቢው ማኅበረሰብ በተሳትፎ ድጋፍ የሚጠቀሙ የቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ቁጥር መጨመር፤ የታተሙና ሥራ ላይ የዋሉ ዓመታዊ የዜጎች ውጤት መመዝገቢያዎች ቁጥር መጨመር የሚጠበቁ ናቸው። ቁልፍ ጉዳይ 5፡ ተቋማዊ ራስን መቻልን ለማሳካት የሀብት ማሰባሰብንና አጠቃቀምን ማሳደግ ቀጣይነት ያለው ዘላቂ ዕድገት ለማስመዝገብ፣ ለመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት፣ የፈጠራ ፕሮግራሞችንና የፍትሓዊ ሥልጠና ተደራሽነትን ለመደገፍ ዘላቂነት ያለው የቴ/ሙ/ሥ የፋይናንስ ድጋፍ መኖር አስፈላጊ ነው። ከጊዜ ወደ ጊዜ ለቴ/ሙ/ሥ የሚሰጠው የፋይናንስ ድጋፍ እያደገ ቢመጣም፣ ከመንግሥት የሚደረገው ድጋፍ በቂ አለመሆን፣ በልማት ዕርዳታ ላይ መተማመን እና ደካማ የውስጥ ገቢ ማስገኛ ሥርዓቶች በዋናነት የሚጠቀሱ ክፍተቶች ናቸው። ይህን የሀብት አሰባሰብና የአጠቃቀም ሥርዓትን ለማሻሻል የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ተተልመዋል። ስትራቴጂዎች የቴ/ሙ/ሥ የፋይናንስ ምንጭ ዘርፈ ብዙ አማራጮች እንዲኖረው ይደረጋል፣ መንግሥት ለቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት የሚሰጠውን የበጀት ድጋፍ እንዲያድግ ይደረጋል፤ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ፈንድ (basket fund) ይቋቋማል፤ ወጪ ቆጣቢ የፕሮግራም አቅርቦት ሞዴሎች ይተገበራሉ፤ በአፈጻጸም ውጤት ላይ የተመሠረተ የበጀት ድልድል ተግባራዊ ይሆናል፤ በአፈጻጸም ላይ ተመሥርቶ በሚሰጥ የደረጃ በደረጃ የአስተዳደር፣ የአሠራርና የፋይናንስ ራስ ገዝ አስተዳደር አማካይነት የሀብት ማሰባሰብንና አጠቃቀምን በማሳደግ ተቋማዊ ራስን መቻልን ማምጣት፤ የገቢ ምንጮችን በማስፋፋትና ትብብሮችን በማጠናከር ተቋማዊ ራስን ለመቻል የሚያስችል ማዕቀፍ ማቋቋም አስፈላጊ ነው። 26 27 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የሚጠበቁ ውጤቶች ያደገ ከዘርፈ ብዙ ምንጭ የተገኘ የቴ/ሙ/ሥ ፋይናንስ፣ ያደገ ከመንግሥት የሚመደብ ፋይናንስ፤ በአፈጻጸም ውጤት ላይ ተመሥርቶ የተተገበረ የበጀት ድልድል ሥርዓትና ወጪ ቆጣቢ የፕሮግራም አቅርቦት ሞዴል፣ በልማት አጋሮችና ሌሎች ባለድርሻዎች የፋይናንስ ድጋፍ ለማረጋገጥ የሚያስችል የተቋቋመ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ፋይናንስ ቋት (basket fund)፤ ተቋማት የአስተዳደር፣ የአሠራርና የፋይናንስ ነጻነትን ለማሳካት ግልጽ የሆኑ ቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያዎች (KPIs) ባሏቸው የደረጃ በደረጃ የራስ-ገዝ አስተዳደር ሞዴል መተግበር፤ ገቢን የማስፋፋትና ትብብሮችን የማጠናከር ፖሊሲዎችን ጨምሮ ለተቋማዊ ራስን መቻል የሚያስችል ግልጽ ማዕቀፍና የአሠራር መመሪያዎች ተዘጋጅተው መተግበር አለባቸው፡፡ ቁልፍ ጉዳይ 6፡ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና መሠረተ ልማትን ማሻሻል የሥልጠና መሠረተ ልማት ደረጃዎች/Training facility standard/ አለመኖር፣ ጊዜ ያለፈባቸው የሥልጠና መሠረተ ልማቶች፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማላመድ የሚደረገው ጥረት ውስንነት ያለበት መሆኑ የሥልጠናውን ውጤታማነት ጎድቶታል። በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች የሥልጠና መሠረተ ልማት ደረጃዎች/Training facility standard/ ማዘጋጀትና መተግበር፣ በልዩ የሥልጠና ሙያዎች ላይ ያተኮሩ የልህቀት ማዕከላትን ማቋቋም፤ ስትራቴጂያዊ የኢንቨስትመንት ዕቅድ አውጥቶ ተግባራዊ ማድረግ፤ በሥልጠና ተቋማትና በኢንዱስትሪ መካከል የሥልጠና ሀብትን በጋራ መጠቀም የሚያስችል ማዕቀፍ ማዘጋጀት። የሚጠበቁ ውጤቶች ዝቅተኛውን የመሠረተ ልማትና የሀብት ደረጃ የሚያሟሉ የቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ቁጥር መጨመር፤ ሀገራዊ የጥራት ደረጃዎች ያሟሉ የልህቀት ማዕከላት ቁጥር መጨመር፤ በISO ደረጃ/Standard/ የምስክር ወረቀት ያገኙ የሥልጠና ተቋማት ቁጥር መጨመር፤ ከኢንዱስትሪዎች ጋራ የሥልጠና ሀብቶችን የሚጋሩ የቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ቁጥር መጨመር የሚጠበቁ ናቸው። ቁልፍ ጉዳይ 7፡ የጥራት ማረጋገጫ ሥርዓትን ማሻሻል የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት የጥራት ማረጋገጫ ሥርዓት ወጥነት፣ ተዓማኒነትና አግባብነት ያለው ሥልጠናን ከማረጋገጥ አኳያ ከፍተኛ ተግዳሮቶች ያሉበት ነው። በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ። ስትራቴጂዎች ውጫዊና ውስጣዊ አሠራሮችን ያጣመረ አጠቃላይ ሀገራዊ የጥራት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ማዘጋጀትና መተግበር፤ የሥልጠና ተቋማትን ደረጃና የሥልጠና ፕሮግራሞች ዕውቅና አሰጣጥ ሀገራዊ ስታንዳርድ ማዘጋጀት፤ በክልል የተደራጁ የብቃት ምዘና ማዕከልትን አሠራርና ተጠያቂነት የሚያረጋግጥ ማዕቀፍ ማዘጋጀትና መተግበር ናቸው። የሚጠበቁ ውጤቶች የተዘጋጀና የተተገበረ ውጫዊና ውስጣዊ አሠራሮችን ያጣመረ አጠቃላይ ሀገራዊ የጥራት ማረጋገጫ ማዕቀፍ፣ የተዘጋጀና የተተገበረ የሥልጠና ተቋማት ደረጃና የሥልጠና ፕሮግራሞች ዕውቅና አሰጣጥ ስታንዳርድ፣ ጥራታቸው ተረጋግጦ ዕውቅና የተሰጣቸው ተቋማትና የሥልጠና ፕሮግራሞች ቁጥር መጨመር፤ ጠንካራ የውስጥ የጥራት ማረጋገጫ ሥርዓት ያላቸው ተቋማት ቁጥር መጨመር ናቸው። 28 ቁልፍ ጉዳይ 8፡ ተደራሽነትን እና ፍትሓዊነትን ማሻሻል የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ተደራሽነትን ለማሳደግ ጥረቶች ቢደረጉም፣ በተለይም እንደ ገጠርና አርብቶ አደር ማኅበረሰቦች፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞችና ተፈናቃዮች ባሉ ልዩ ትኩረት ለሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ከፍተኛ ችግር መኖሩ ይስተዋላል። በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች የሥልጠና አማራጮችን በማስፋት ማንኛውም ሥልጠና ፈላጊ ቢያንስ አንድ የሙያ ሥልጠና ዕድል እንዲያገኝ ማድረግ፤ ዘመናዊና ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሥልጠና ዕድሎችን ማስፋት፤ ልዩ ትኩረት ለሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች ምቹ የሥልጠና ሥነ-ምኅዳር መፍጠር የሚያስችል ማዕቀፍ ማዘጋጀት፤ የተቀናጁ ልዩ የሥልጠና ፕሮግራሞችን የሚያቀርቡ የሥልጠና ተቋማትን ማቋቋም። የሚጠበቁ ውጤቶች የሰፋና ተግባራዊ የተደረገ ሁሉንም ሥልጠና ፈለጊዎችን ተጠቃሚ ያደረገ የሥልጠና አማራጭ፣ ዘመናዊና ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሰፋ ሥልጠና ዕድል፣ ልዩ ትኩረት ለሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች (አርብቶ አደር ማኅበረሰቦች፣ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፤ ስደተኞች ተፈናቃዮች፤ ከስደት ተመላሾች) ምቹ የሥልጠና ሥነ-ምኅዳር ለመፍጠር የሚያስችል የተዘጋጀና የተተገበረ ማዕቀፍ፤ የተቀናጁ ልዩ የሥልጠና ፕሮግራሞችን ለሚያቀርብ የተደራጁ የሥልጠና ተቋማት መጨመር፤ በቴ/ሙ/ሥ ተጠቃሚ የሆኑ ልዩ ትኩረት ለሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች መጨመር። ቁልፍ ጉዳይ 9፡ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ገጽታ ግንባታን ማሻሻል የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ፕሮግራም በኅብረተሰቡ ዘንድ የመጨረሻ አማራጭ ተደርጎ እየታየ የሚገኝ ነው። ይህም ኅበረተሰቡ ቴክኖሎጂንና ጉልበትን በመጠቀም ለሚሰሩ ምርትና አገልግሎት ሥራዎች የሚያገለግሉ ሙያዎች ላይ ያለው የሥልጠና ፍላጎት ማነስ ነው። ምክንያቱም በቀላሉ በቢሮ ውስጥ ለሚሠሩ ሥራዎች የሚሰጠው ሥልጠና ላይ ትኩረት የመስጠት ዝንባሌ፣ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዝቅተኛ የትምህርት ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች መግቢያ ተደርጎ መቀረጹ/ መወሰዱ ዝቅተኛ ክብር ያለው ተደርጎ እንዲታይ ተደርጓል። በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተፈላጊነት ለማጉላት ሀገር ዓቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎችን በተለያዩ አማራጮች ለማካሄድ የሚያስችል ስትራቴጂክ ማዕቀፍ ማዘጋጀትና መተግበር፤ በሀገራዊ ትምህርትና ሥልጠና የብቃት ማዕቀፍ ህግ መሠረት ለቴክኒክና ሙያ ሥልጠና አጠናቃቂዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት መሸጋገሪያ ሥርዓትን የሚያቀላጥፍ አሠራር ሥርዓት መዘርጋትና መተግበር፤ ተቋማትን ለዜጎች ምቹ፤ ሳቢ እና ለ21ኛ ክፍለ ዘመን ሥልጠና የተዘጋጁ እንድሆኑ ማድረግ፡ ከታችኛው የትምህርት እርከን ጀምሮ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ለዜጎች እንድሰጥ ማስቻል/Voca tionalization/ ናቸው። የሚጠበቁ ውጤቶች የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን ተፈላጊነት ለማጉላት የተዘጋጀና የተተገበረ ሀገር ዓቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስትራቴጂክ ማዕቀፍ፣ በሀገራዊ ትምህርትና ሥልጠና የብቃት ማዕቀፍ ሕግ መሠረት የተዘጋጀና የተተገበረ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና አጠናቃቂዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ሽግግር የሚያደርጉበት የተዘረጋ ሥርዓት፣ ሙያ ነክ የሆኑ ፕሮግራሞችን የሚሰጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መጨመር ነው። 29 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም ቁልፍ ጉዳይ 10፡ የመረጃ አያያዝ፣ ፍሰት እና አጠቃቀምን ማሻሻል የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና መረጃ ሥርዓት አስተዳደር (TMIS) ትግበራ የተቀናጀ አለመሆን፣ የመረጃ አሰባሰብ ሥርዓት ውስንነት ያለበት መሆኑ፣ የመረጃ አጠቃቀም ባህል ዝቅተኛ መሆኑ፣ የመረጃዎች ፍሰት ወጥነት የሌላቸውና ተአማኒነት የጎደላቸው በመሆኑ ውሳኔ ለመስጠት ችግሮችን ሲያስከትል ቆይቷል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና መረጃ ሥርዓት አስተዳደር (TMIS) እና የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አስተዳደርን (LMIS) ተቋማዊ ማድረግ፤ ሀገራዊ መረጃና የዕውቀት አስተዳደር ሥርዓት ማዘጋጀትና መተግበር፤ የመረጃ መጋራት አሠራር/ፕሮቶኮል/ እና ሀገራዊ የተጠያቂነት ማዕቀፍ ማዘጋጀትና መተግበር፣ የመረጃ አጠቃቀም ባህልን ለማሻሻል የአቅም ግንባታ ማዕቀፍ መንደፍና መተግበር ናቸው። የሚጠበቁ ውጤቶች ተቋማዊ የተደረገ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና መረጃ ሥርዓት አስተዳደር (TMIS) እና የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አስተዳደርን (LMIS)፤ የተዘጋጀና የተተገበረ ሀገራዊ መረጃና የዕውቀት አስተዳደር ሥርዓት ማድረግ፤ የተዘጋጀና የተተገበረ የመረጃ መጋራት አሠራር/ፕሮቶኮል/ እና ሀገራዊ የተጠያቂነት ማዕቀፍ፣ የመረጃ አጠቃቀም ባህልን ለማሻሻል የተነደፈ እና የተተገበረ የአቅም ግንባታ ማዕቀፍ ነው። ቁልፍ ጉዳይ 11፡ ክትትል፣ ግምገማ፣ ተጠያቂነት እና ልምድ ቅመራን (MEAL) ሥርዓትን ማሻሻል ጠንካራ የክትትል ድጋፍ፣ የግምገማ፣ የተጠያቂነትና የልምድ ቅመራ ማዕቀፍ መኖር ለቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት ወሳኝ ነው። ሆኖም ግን አፈጻጸሙን ውጤታማ በሆነ መንገድ ከመከታተልና ከመገምገም አንጻር ክፍተቶች ይሰተዋላሉ። ደካማ የክትትል ሥርዓት፣ ወጥነት የጎደለው ቁልፍ የአፈፃፀም አመልካቾች (KPIs)፣ ውስን ቅንጅትና ትብብር፣ ውጤታማ ያልሆነ የግብረ መልስ፣ በቂ የዓቅም እና የቴክኖሎጂ ውሕደት አለመኖር በዋናነት የሚጠቀሱ ተግዳሮቶች ናቸው። እነዚህን ተግዳሮቶቹን ከመፍታት አኴያ የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ተቀርጿል። ስትራቴጂዎች በውጤት ላይ የተመሠረተ ክትትል፣ ግምገማ፣ ተጠያቂነት እና ልምድ ቅመራ ሥርዓት ተቋማዊ ማድረግ፤ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመቀመር ዲጂታል ፕላትፎርም ማዘጋጀትና መጠቀም፤ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት ውስጥ በክትትል፣ ግምገማ፣ ተጠያቂነት እና ልምድ ቅመራ ሥርዓት ትግበራ ላይ የሚሳተፉ መሪዎችና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎችን ዓቅም ለመገንባት አጠቃላይ የዓቅም ግንባታ ፕሮግራም ማዘጋጀትና መተግበር ናቸው። የሚጠበቁ ውጤቶች ተቋማዊ የተደረገ እና በውጤት ላይ የተመሠረተ ክትትል፣ ግምገማ፣ ተጠያቂነት እና ልምድ ቅመራ ሥርዓት፤ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመቀመር የሚያስችል የተዘጋጀና ጥቅም ላይ የዋለ ዲጂታል ፕላትፎርም፣ በክትትል፣ ግምገማ፣ ተጠያቂነት እና ልምድ ቅመራ ሥርዓት ትግበራ ላይ ለሚሳተፉ አካላት የተዘጋጀና የተተገበረ የአቅም ግንባታ ፕሮግራም ዋነኞቹ ናቸው። 3.2. ትኩረት ሁለት፡ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና አግባብነት እና ጥራትን ማሻሻል ቁልፍ ጉዳይ 1፡ የሙያ ደረጃ ምደባ እና የሥርዓተ ሥልጠና ጥራትን ማሻሻል ሥርዓተ ሥልጠናው ለሠልጣኞች የሚፈልገውን የሙያ ብቃት በማስጨበጥ ረገድ የጥራት ደረጃው ውስንነት ያለበት በመሆኑ የኢንዱስትሪውን ፍላጎት ማሟላት አላስቻለም፡፡ እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ 30 ስትራቴጂዎች የሙያ ደረጃና የሥርዓተ ሥልጠና ዝግጅት ሀገራዊ እስታንዳርድ ማዘጋጀትና መተግበር፣ ሀገራዊ የሙያ ብቃት ደረጃዎችና ሥርዓተ ሥልጠናዎችን ከግሉ ዘርፍ ጋራ በመቀናጀት ማዘጋጀት፣ ማጽድቅ፣ መተግበርና ማሻሻል፣ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት የሙያ ደረጃ፣ የሙያ ብቃት ምዘና፣ በሥርዓተ ሥልጠና ዝግጅት እና ዕውቅና አሰጣጥ ሂደት ላይ ለተሠማሩ ባለሙያዎች የዓቅም ግንባታ ፕሮግራም ማዘጋጀትና መተግበር ነው። የሚጠበቁ ውጤቶች ከግሉ ዘርፍ ጋራ በመቀናጀት የተዘጋጁ፣ የጸደቁ የተተገበሩ እና የተሻሻሉ ሀገራዊ የሙያ ብቃት ደረጃዎችና ሥርዓተ ሥልጠናዎች፣ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት የሙያ ደረጃ፣ የሙያ ብቃት ምዘና፣ በሥርዓተ ሥልጠና ዝግጅት እና በዕውቅና አሰጣጥ ሂደት ላይ ሥልጠና አግኝተው የበቁ ባለሙያዎችን መጨመር። ቁልፍ ጉዳይ 2፡ የማኅበረሰብን የሥልጠና ፍላጎትና የክህሎት ክፍተቶችን የሚለይ እና ሥርዓተ ሥልጠና የሚያዘጋጅ ሥርዓት በጋራ መፍጠር የማኅበረሰብን የሥልጠና ፍላጎት፣ የክህሎት ክፍተቶችን መለየት እና ሥርዓተ ሥልጠና የማዘጋጀት ወቅታዊው አሠራር ከላይ ወደ ታች የተመሠረተ ነው። የኅብረተሰብ ክፍሎች የሆኑት ማኅበረሰቡ፣ መደበኛ ባልሆኑ ዘርፎች የሚሠሩ ሠራተኞች፣ የአካባቢ የኅብረት ሥራ ማኅበራት እና ሌሎችም ተሳትፎ ውስን ነው። ይህ አካሄድ የአካባቢ ማኅበረሰቡ ባለቤትነትን የሚቀንስ ሲሆን የሰዎችን ትክክለኛ የክህሎት ፍላጎትም አያሳይም። ስትራቴጂዎች በሁሉም ክልሎች በማኅበረሰብ የሚመራ የሥራ ገበያ ዳሰሳ ጥናትና የክህሎት ክፍተት ትንተና ማካሄድ፤ ዜጎችን፣ የእጅ ባለሙያዎችን፣ የኅብረት ሥራ ማኅበራትንና የአካባቢ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን የሚያካትቱ የጋራ ሥርዓተ ትምህርት በጋራ የማዘጋጀት አውደ ጥናቶችን መደበኛ ማድረግ፤ በማኅበረሰብ ላይ የተመሠረቱ አሠልጣኞችንና የእጅ ባለሙያዎችን እንደ መደበኛ የቴ/ ሙ/ሥ ሥነ-ምኅዳር አካል አድርጎ ዕውቅና መስጠትና የምስክር ወረቀት መስጠት። የሚጠበቁ ውጤቶች በሁሉም ክልሎች በማኅበረሰብ የሚመሩ የክህሎት ክፍተት ሪፖርቶች በየዓመቱ እየጨመሩ መሄድ፤ በቀጥታ በማኅበረሰብ አስተያየት ላይ ተመስርተው የተሻሻሉ ሥርዓተ ሥልጠናዎችት ቁጥር መጨመር ፤ የቴ/ሙ/ሥ አሠልጣኝ የምስክር ወረቀት ያላቸው እውቅና የተሰጣቸው የእጅ ባለሙያዎች/የማኅበረሰብ አሠልጣኞች ቁጥር መጨመር። ቁልፍ ጉዳይ 3፡ የሥልጠና አቅርቦትን ማሻሻል የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት በብቃት ላይ የተመሠረተና ዲጂታል መሣሪያዎችን በመጠቀም መሻሻሎች ቢኖሩትም፣ በሥራ ቦታ ሥልጠና ክትትልና ድጋፍ ዕጥረት፣ ወጥነት የጎደለው የማሠልጠኛ ዘዴ፣ ብቁ የሆኑ የኢንዱስትሪ አሠልጣኞች አለመኖር፣ በንድፈ ሐሳብና በተግባራዊ ክህሎቶች መካከል ክፍተት መኖሩ፣ የሥልጠና ቋንቋ ተግዳሮት መኖር፣ እና ደካማ ቅንጅት መኖር ዋንኛ ችግሮች ናቸው። እነዚህም የሥርዓቱን ብቃት ያላቸው የሥልጠና አጠናቃቂዎችን የማፍራት ዓቅም ገድበውታል። በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች በአፕረንትሽፕና በትብብር ሥልጠና ወቅት ለሠልጣኞች የሥራ ቦታ ሥልጠና ልምዶችን ጥራት ለማሻሻል የሚያስችል ሀገራዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት እና መተግበር ያስፈልጋል። የሥልጠና ቋንቋ አጠቃቀም፣ የማስተማሪያ መርጃ ዝግጅት እና ፕሮጀክት ተኮርና ችግር ፈቺ አቀራረቦችን ያካተተ የሥልጠና አሰጣጥ መመሪያ መንደፍና ተግባራዊ ማድረግ፣ ለሠልጣኞችና የሥልጠና ሠራተኞች 31 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም ደኅንነቱ የተጠበቀ የሥራና ሥልጠና አካባቢን ለመፍጠር የሚያስችል ሀገራዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀትና መተግበር። የሚጠበቁ ውጤቶች ለሠልጣኞች የሥራ ቦታ ሥልጠና ልምዶችን ጥራት ለማሻሻል የሚያስችል ተዘጋጅቶ የተተገበረ የአፕረንትሽፕና የትብብር ሥልጠና ማዕቀፍና ሀገራዊ የሥልጠና አሰጣጥ መምሪያ፣ በሠልጣኞች የርካታ የዳሰሳ ጥናት ውጤቶች በሚረጋገጥ መልኩ የሥራ ቦታ የሥልጠና ጥራት መሻሻልና፤ በሀገር ዓቀፍ የብቃት ምዘናዎች ብቁ የሚሆኑ ተመዛኞች ምጣኔ መጨመር ይጠበቃሉ። ቁልፍ ጉዳይ 4፡ የብቃት ምዘና እና የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ሥርዓትን ማዘመን የብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ሥርዓት በሥራ ገበያው ላይ ያለውን ውጤታማነትና ተጽዕኖ የሚገቱ በበርካታ ተግዳሮቶች ተተብትቦ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ተግዳሮቶች መካከል የምዘና ሥርዓቱ ወጥነት፣ አስተማማኝነት እና ተደራሽነት የጎደለው መሆኑ፣ ከሁኔታዎች ጋራ የማይጣጣም የምዘና አሠራር ሥርዓት፤ ለምዘና መሣሪያዎች ምስጢራዊነት በቂ የደኅንነት ማስጠበቂያ ሥርዓት አለመኖር ለስርቆት እና ለማጭበርበር ተጋላጭ መሆኑ፣ የዲጂታል መሣሪያዎች አጠቃቀም በቂ አለመሆን፤ የተሟላ ብቃት የተላበሱ መዛኞች እና ተቆጣጣሪዎች አለመኖር እና ደህንነታቸው ያልተረጋገጡ የማረጋገጫ ሂደቶች ጎልተው የሚታዩ ችግሮች ናቸው። በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች በምዝናና ብቃት ማረጋገጫ ሥርዓቱ ውስጥ ጥራትን እና እምነትን ለማሳደግ ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትን እና ደረጃውን የጠበቀ አሠራርን የሚያረጋግጥ ሀገራዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት እና መተግበር፣ የምዘናና የብቃት ማረጋገጫ ሥርዓቱን ዘመናዊነትን፣ ቅልጥፍናን፣ ትክክለኛነትንና ተደራሽነትን ለማሻሻል ዲጂታል መፍትሔዎችን መተግበር፣ በልምድ የተገኘን ዕውቀት (RPL) በምዘና በማረጋገጥ ዕውቅና ለመስጠት እና ተደራሽነትን ለማስፋት የሚያሰችል ሀገር ዓቀፍ ሥርዓት መዘርጋት እና መተግበር፣ የኢንዱስትሪ መዛኞችን ለመመልመልና ለማብቃት የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት እና መተግበር ይገባል። የሚጠበቁ ውጤቶች ጥራትን፣ ታዓማኒነትን፣ ግልጸኝነትን፣ ተጠያቂነትን እና ደረጃውን የጠበቀ አሠራርን ለማረጋገጥ የሚያስችል የተዘጋጀና የተተገበረ የምዘናና ብቃት ማረገገጫ ሥርዓት ማዕቀፍ፤ በኢንዱስትሪ ኩባንያዎች ውስጥ የተመሠረቱ የምዘና ማዕከላት ድርሻ መጨመር፤ የዲጂታል ምዘናዎች የሚካሄዱባቸው ሙያዎች ቁጥር መጨመር፣ ለቀደመ ብቃት ዕውቅና ለማግኘት ምዘናዎችን የሚወስዱ ተመዛኞች ቁጥር መጨመር፣ የመዛኝነት የብቃት ማረጋገጫ ከተሰጣቸው መዛኞች መካከል የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ድርሻ መጨመር፤ ከምዘና ጋራ በተያያዘ የማጭበርበርና ሌሎች ቅሬታዎችን ቁጥር መቀነስ ያካትታል። 32 33 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም ቁልፍ ጉዳይ 5፡ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና አሠልጣኞች እና አመራሮች ብቃት ማሻሻያ ሥርዓት ማጠናከር በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ የአሠልጣኝና አመራር ሚና ለጥራትና ብቁ የሰው ኃይል ልማት ወሳኝ ቢሆንም፣ በርካታ ተግዳሮቶች ገጥመውታል። ከእነዚህም መካከል በሥርዓተ ሥልጠናውና በአሠልጣኝ ልማት ፕሮግራሞች መካከል ያለው ተናባቢነት አነስተኛ መሆን፣ ከኢንዱስትሪ ፍላጎት ጋራ የማይጣጣሙ የማሠልጠኛ ዘዴዎች፣ ለባለሙያዎች ቀጣይነት ያለው የሙያ ማሻሻያ ፕሮግራም አለመኖር፣ ግልጽ የአመራር ብቃትና የተጠያቂነት ሥርዓት አለመኖር፣ ሙያዊ ሥነ-ምግባርንና ብቃትን መሠረት ያደረገ የአመራር ምደባ አለመኖር፣ ከፍተኛ አፈጻጸም ላላቸው ባለሙያዎች በቂ የማቆያ ስልት አለመኖር፣ ከኢንዱስትሪዎች ጋራ ያለው ደካማ ትስስር፣ እንዲሁም በተግባር ላይ የተመሠረተ ሥልጠናና የኢንዱስትሪ አሠልጣኞች ብቃት ማረጋገጥ የሚያስችል አሠራር አለመኖር ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች የአሠልጣኞች፣ አመራሮች፣ እና ሱፐርቫይዘሮች ምልመላ፣ ማብቃት፣ ማቆያና የብቃት ማረጋገጫ ሥርዓትን የሚያዘምን ሀገራዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀትና መተግበር፣ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና አሠልጣኞች፣ አመራሮች እና ሱፐርቫይዘሮች መካከል የሥርዓተ-ጾታ እኩልነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት እና መተግበር፣ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋምና ኢንዱስትሪ ውስጥ አሠልጣኞች እና ለተቋም አመራሮች የተከታታይ የሙያ ዕድገት የሚያረጋግጡ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት እና መተግበር ያስፈልጋል፡፡ የሚጠበቁ ውጤቶች የአሠልጣኞችን፣ የአመራሮችን፣ እና የሱፐርቫይዘሮችን ምልመላ፣ ማብቃት፣ ማቆያና የብቃት ማረጋገጫ ሥርዓትን ማዘመን የሚያስችል የተዘጋጀና የተተገበረ ሀገራዊ ማዕቀፍ፤ በአሠልጣኝነት የምስክር ወረቀት ያገኙ አሠልጣኞች ድርሻ መጨመር፣ በብቃት ላይ ተመሥርተው ምደባ ያገኙ አመራሮች ድርሻ መጨመር፣ በቴ/ሙያ አሠለጣኞችና በተቋም አመራሮች መካከል የሴቶች ድርሻ መጨመር የሚጠበቁ ናቸው። ቁልፍ ጉዳይ 6፡ በሠልጣኞ ዘንድ ጠንካራ የሥራ ሥነ-ምግባርና የሀገር ወዳድነት ስሜትን ማጎልበት በሠልጣኞች መካከል ጠንካራ የሥራ ሥነ-ምግባር ማሽቆልቆልና የሀገር ወዳድነት ስሜት ማጣት ለሀገራዊ ልማትና ለሠለጠነ የሰው ኃይል ዕድገት ከፍተኛ ሥጋት ነው። ይህ ክፍተት ምርታማነትን የሚገታ ከመሆኑም በላይ የሙያ ሥልጠና አጠናቃቂዎች የሚያደርጉትን አስተዋፅኦ ይገድባል። ስትራቴጂዎች ሁሉን ዓቀፍ ክህሎት እንዲዳብር ለማድረግ ስለ ሥራ ሥነ-ምግባርና ሀገራዊ ዕሴቶችን ለማዳበር የሚያስችሉ ሞጁሎችን በሁሉም የሥልጠና ፕሮግራሞች ውስጥ ማካተት፤ በሠልጣኞች ዘንድ የሙያዊ ሥነ-ምግባርን፣ ተጠያቂነትንና የሀገራዊ ልማት ኃላፊነትን ለማጎልበት ከኢንዱስትሪ መሪዎች ጋራ ህገራዊ የምክክር መድረኮችን ማቋቋም፣ የማኅበረሰብ አገልግሎትና የበጎ ፈቃድ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በሥርዓተ ሥልጠናው ውስጥ በማካተት የዜግነት ግዴታንና ሀገር ወዳድነትን ማዳበር፣ እንዲሁም ልዩ የሥራ ሥነ-ምግባርና ሐቀኝነትን የሚያሳዩ ሥልጠና አጠናቃቂዎች ዕውቅና መስጠት አስፈላጊ ነው። 34 የሚጠበቁ ውጤቶች ሁሉም የሥልጠና ፕሮግራሞች ስለ ሥራ ሥነ-ምግባር፣ ሥርዓትና ሀገራዊ ዕሴቶች የሚያስተምሩ ግዴታ የሆኑ ሞጁሎችን የሚያጠቃልሉ መሆንና ተመጣጣኝ ሥርዓተ ሥልጠና የግምገማ ማዕቀፍ መኖር፤ መደበኛ ሀገራዊ የአማካሪነት ፕሮግራም ተቋቁሞ በሥራ ላይ መዋል፣ በኢንዱስትሪ አጋሮች ሪፖርት መሠረትም በተማሪዎች ሙያዊ ብቃትና ተጠያቂነት ላይ የተመዘገበ ዕድገት መኖር፤ የማኅበረሰብ አገልግሎትና በበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይ የሚሳተፉ ሠልጣኞች መጨመር፤ እንዲሁም የዜግነት ግዴታን፣ ሐቀኝነትንና ሀገር ወዳድነትን አብነት መሆናቸው ዕውቅና የተሰጣቸው ሠልጣኞችን መጨመር። ቁልፍ ጉዳይ 7፡ ለሀገር ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የኢኮኖሚ ዘርፎች ልዩ የልህቀት ማዕከሎችን ለመመሥረት ስትራቴጂያዊ ዞን አከፋፈልና ልዩ ልዩነትን መተግበር በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት መካከል የስትራቴጂያዊ ልዩነት አለመኖር በቴ/ሙያ ሥርዓቱ ውስጥ መበታተንና መደጋገም እንዲፈጠር በማድረግ ተቋማት የየክልል ኢንዱስትሪዎችን የክህሎት ፍላጎት እንዳያሟሉ አግዷል። በዚህም በአንዳንድ ቦታ የሥልጠና ድግግሞሽና የሀብት ብክነትን እያስከተለ ከመሆኑም በላይ በሥልጠና አጠናቃቂዎች ክህሎትና በሥራ ገበያው ፍላጎት መካከል አለመጣጣምን በማምጣትና የኢኮኖሚ ዕድገትን በመግታት ያልተፈለገ ተጽዕኖ አምጥቷል። ስትራቴጂዎች በሁሉም ክልሎች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የኢኮኖሚ ዘርፎችና በእያንዳንዱ ዘርፍ ውስጥ የሚያስፈልጉ ክህሎቶችን ለመለየት ሀገራዊ የክህሎት ክፍተት ትንተና ማካሄድ፤ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ዘርፎችና ከየክልሉ የኢኮኖሚ ጥንካሬ ጋራ የተጣጣሙ የተወሰኑ የቴ/ሙ/ሥ ተቋማትን መርጦ ወደ ልዩ የልህቀት ማዕከላት ማሳደግና መሠየም፤ ሥርዓተ ሥልጠናዎችት፣ መሣሪያዎችና የሥልጠና ዘዴዎች የአሁንና የወደፊቱን የሥራ ገበያ ፍላጎቶች የሚያሟሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ለእያንዳንዱ የልህቀት ማዕከል ጠንካራ የኢንዱስትሪ አመራር ቦርዶችን ማቋቋም፤ ለልህቀት ማዕከላት በአፈጻጸማቸው፣ በኢንዱስትሪ ትብብርና በሥልጠና አጠናቃቂዎች የሥራ ቅጥር መጠን ላይ ተመስርቶ ልዩ ልዩ ድጋፍ የሚሰጥ ስትራቴጂያዊ የገንዘብ ድጋፍ ሞዴል መተግበር፤ የቴ/ሙ/ሥ ተቋማትን ከክልላዊ የኢኮኖሚ ቅድሚያዎችና ከተለያዩ ሠልጣኞች ፍላጎት ጋራ ለማጣጣም የሚያስችል ሀገራዊ ስትራቴጂካዊ የዞን አከፋፈልና የልየታ ማዕቀፍን መተግበር። የሚጠበቁ ውጤቶች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የኢኮኖሚ ዘርፎችና ለእያንዳንዱ ክልል የሚያስፈልጉ ክህሎቶችን የሚለይ ሀገራዊ ደረጃ የክህሎት ክፍተት ትንተና የሚያሳይ ሁሉን ዓቀፍና ለሕዝብ ክፍት የሆነ ሪፖርት ተዘጋጅቶ መጽደቅ፤ የተወሰኑ የቴ/ሙ/ሥ ተቋማት በይፋ እንደ ልዩ የልህቀት ማዕከላት መመደብና መሥራት፣ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ዘርፎች የተበጁ የተሻሻሉ መገልገያዎችና የሥልጠና ፕሮግራሞች መኖራቸው፤ ሁሉም የተመደቡ የልህቀት ማዕከላት ሥርዓተ ትምህርቶችን በመደበኛነት የሚገመግሙና የሚያጸድቁ የኢንዱስትሪ አመራር ቦርዶች መኖራቸው፣ ይህም ከሥራ ገበያ ፍላጎት ጋራ ቀጥተኛ መጣጣምን ያረጋግጣል፤ የፋይናንስ ድጋፍን ከተመሠረቱ ቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያዎች (KPIs) ጋራ የሚያገናኝ በአፈጻጸም ላይ የተመሠረተ የገንዘብ ድጋፍ ሞዴል መተግበር፣ ይህም በሥልጠና አጠናቃቂዎች የሥራ ቅጥር መጠንና በስኬታማ የኢንዱስትሪ ትብብሮች ላይ ያተኩራል፤ የቴ/ሙ/ሥ ተቋማትን ከክልላዊ የኢኮኖሚ ቅድሚያዎች ጋራ የሚጣጣም ልዩ ልዩነትን የሚመራ ሀገራዊ የስትራቴጂያዊ የዞን አከፋፈልና የልየታ ማዕቀፍ በይፋ መጽደቅና መተግበር ናቸው። 35 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም ቁልፍ ጉዳይ 8፡ በኢ-መደበኛ ዘርፍ የተሠማራውን የሰው ኃይል ብቃትን ማሳደግ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ፕሮግራም በኢ-መደበኛ ዘርፍ ለተሠማራው የሰው ኃይል ብቃት ማሳድግ፣ የሥራ ፈጠራንና እና የገበያ ተደራሽነትን የማሳደግ ዓቅም ቢኖረውም ለዚህ ዘርፍ አስፈላጊ የሆኑ ልዩ እና ተለማጭ ሥልጠና ፕሮግራሞችን መቅረጽና ማቅረብ አልቻለም። ይህ ደግሞ በፕሮግራሞቹ ውስን ተደራሽነት፣ ተለማጭ ያልሆነ የዘርፉ አወቃቀር ምክንያት በኢ-መደበኛ ዘርፉ የተሠማሩ ዜጎችን በሥልጠና ዕድሉ ተጠቃሚ እንዳይሆኑ አድርጓል። በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች በኢ-መደበኛ ዘርፍ ለተሠማሩ የሰው ኃይል ብቃትን ለማሳደግ ተለማጭ የሥልጠና ፕሮግራሞችን ማዘጋጀትና መተግበር፣ የኢ-መደበኛ ዘርፍ የሰው ኃይል ተወዳዳሪነትን ለማረጋገጥ የብቃት ምዘና ሥርዓት መዘርጋትና መተግበር፣ በኢ-መደበኛ ዘርፍ የተሠማሩ ሠራተኞችን የብቃት ደረጃ ለማሳደግ፣ አዳዲስ ክህሎቶችን ለማላበስ እና የክህሎት ክፍተቶችን ለማሻሻል የሚያስችሉ የተለያዩ የሥልጠና አማራጮችን እና ዕውቅና አሰጣጥ ሥርዓቶችን መዘርጋት፣ የኢ-መደበኛ ሠራተኞች የተለመደው የአኗኗር ዘይቤያቸው ሳይዛባ ብቃታቸውን ማሻሻል የሚያስችላቸውን የሥልጠና አማራጭ የሚያቀርብ የሥልጠና ፕሮግራም ማዘጋጀትና መተግበር ነው። የሚጠበቁ ውጤቶች ኢ-መደበኛ ዘርፍ ለተሠማሩ የክህሎት ክፍተቶቻቸውን ለመሙላት የተተገበሩ ሥልጠና አማራጮችና የዕውቅና አሰጣጥ ሥርዓቶች፣ የኢ-መደበኛ ሠራተኞች የዕለት ተዕለት ሕይወታቸው ሳይዛባ ብቃታቸውን ለማሻሻል የሚያስችላቸውን ከአኗኗር ዘይቤ ጋራ የተጣጣሙ ተለማጭ የሥልጠና አማራጮች፣ ለኢ-መደበኛ ዘርፍ የተበጁ የቴ/ሙ/ሥ ፕሮግራሞች ቁጥር መጨመር፣ የሠለጠኑና የምስክር ወረቀት ያገኙ በኢ-መደበኛ ዘርፍ የተሠማሩ ሰራተኞች ቁጥር መጨመር እና በኢ-መደበኛ ዘርፍ ባለሙያዎች ሥልጠና አግኝተው ለሥራ ብቁ የሆኑ የሥልጠና ተጠቃሚዎች መጨመር ናቸው። ቁልፍ ጉዳይ 9፡ የቴ/ሙ/ሥ/ ዓለም ዓቀፋዊነትን እና የክልላዊ ትስስር ማሳደግ የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት ዓለም ዓቀፋዊና ቀጣናዊ ማጣጣም ውስንነት አለበት። ይህ ደግሞ ከዓለም ዓቀፍ ደረጃዎች ጋራ ለመጣጣምና ዓለም ዓቀፍ ዕድል ለመጠቀም ያለውን አቅም ገድቦታል። የተደራጀ የሥራ ማዕቀፍ አለመኖር የዘርፉን ዓለም ዓቀፋዊነትና ቀጣናዊ ዘላቂ ትግበራ ላይ ከፍተኛ ችግር ፈጥሯል። በመሆኑም ከሥራ ገበያ ፍላጎት ጋራ ያልተጣጣሙ ብቃቶችና ለምሩቃን በቀጠናው ውስጥ የተገደበ እንቅስቃሴን እንዲኖር አድርጓል፡፡ እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች በአግባቡ የተቀመረ ከዓለም ዓቀፋዊ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ ጋራ ተናባቢ ሀገራዊ የቴ/ሙ/ሥ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ይተገበራል፣ ትብብርን ለማበረታታት ድንበር ተሻጋሪ የልምድ ልውውጥ ፕሮግራሞች እና የጋራ ሥልጠና ዕድሎችን መጠቀም የሚያስችል ቀጣናዊ የቴ/ሙ/ሥ የትስስር ማዕቀፍ ይዘጋጃል፣ በሀገር ውስጥ እና በውጭ በቴ/ሙ/ሥ ተቋማት መካከል የጋራ ምርምር፣ ፈጠራ እና የዕውቀት ሽግግር ማድረግ የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ መተግበር፣ ስደተኞች ከማኅበረሰቡ በአንድነት ሥልጠና እንዲያገኙ የሚያስችል የተቀናጀ የቴ/ሙ/ሥ ፕሮግራም ማቋቋም ናቸው። 36 የሚጠበቁ ውጤቶች በሀገር ውስጥ እና በውጭ በቴ/ሙ/ሥ ተቋማት መካከል የጋራ ምርምር፣ ፈጠራ እና የዕውቀት ሽግግር ለማሳለጥ ተዘጋጅቶ የተተገበረ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ፣ ስደተኞች ከማኅበረሰቡ በአንድነት ሥልጠና እንዲያገኙ የሚያስችል የተቀናጀ የቴ/ሙ/ሥ ፕሮግራም፤ በጋራ ፕሮግራሞች የሚሳተፉ ሠራተኞችና ሠልጣኞች ቁጥር መጨመር፣ ከዓለም ዓቀፍ ቴ/ሙ/ሥ ተቋማት በጋራ የሚደረጉ የልምድ ልውውጦች፤ የክህሎት ውድድሮችና የሚተገበሩ የምርምርና የፈጠራ ውጤቶች መጨመር፤ በመካከለኛ ጊዜ የሚጠበቁ ውጤቶች ናቸው። ቁልፍ ጉዳይ 10፡ ዲጂታላይዜሽንን በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ውስጥ ማሳደግ የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ለዲጂታል ለውጥ ያላቸው ዝግጁነት ውስንነት ያለበት ሲሆን የማያስተማምን የኢንተርኔት አገልግሎት፣ ወጥነት የሌለው የኃይል አቅርቦት፣ ውስንነት ያለበት የዲጂታል መሠረተ ልማት እና በአሠልጣኞች ዘንድ በቂ የሆነ የዲጂታል ክህሎት አለመኖር በሥልጠና አሰጣጡ ላይ እንቅፋት ሆኗል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማትን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ለማሻሻል የዲጂታል መሠረተ ልማት ደረጃዎችን ማዘጋጀት እና እንዲደራጁ ማድረግ፤ ዲጂታል ክህሎቶችን በሥርዓተ ሥልጠና ውስጥ ማካተት፣ አሠልጣኞች እና የሥራ ኃላፊዎችን በዲጂታል መሣሪያዎች አጠቃቀምና በኦንላይን አሠለጣጠን ዘዴዎች ላይ ማብቃት፣ የሥራ ሂደቶችን አውቶሜት (Automate) በማድረግ የሥራ ቅልጥፍናን ማሳደግ፣ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዙ የሥልጠና ፕሮግራሞችና የሥራ ላይ ሥልጠናዎችን በጋራ ተተግባሪ ለማድረግ የመንግሥትና የግል አጋርነትን ማጠናከር ነው። የሚጠበቁ ውጤቶች የተዘጋጀ የዲጂታል መሠረተ ልማት ደረጃዎች /standards/ እና ይህንን መሠረት ተደርጎ የተደራጁ ተቋማት፣ በሥርዓተ ሥልጠና ውስጥ የተካተቱ ዲጂታል ክህሎቶች፣ በዲጂታል መሣሪያዎች አጠቃቀምና በኦንላይን አሰለጣጠን ዘዴዎች የበቁ አሠልጣኞችና አመራሮች፣ አውቶሜት (Au tomate) የተደረጉ የሥራ ሂደቶች፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂን በተመለከተ በጋራ ለመሥራት የተደረገ የመንግሥትና የግል አጋርነቶች ናቸው። ቁልፍ ጉዳይ 11፡ አረንጓዴ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ፕሮግራምን ማሳደግ አሁን ያለው የቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት ዘላቂነት ባለው መልኩ የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋምን ቅድሚያ ሰጥቶ ገንቢ አስተዋፅኦ ማበርከት እንዲችል ከፍተኛ ለውጥ ያስፈልገዋል። በተለይም በፊት የነበረው ስርዓተ ሥልጠና የአረንጓዴ ክህሎትን ማዳበር የሚያስችል ሞጁል ያልያዘ ነበር። በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች በቴ/ሙ/ሥ ሥርዓተ ሥልጠና ፕሮግራሞች ውስጥ እንደ ታዳሽ ኃይል መልሶ ጥቅም ላይ ማዋልንና አረንጓዴ ክህሎቶችን ማካተትና መተግበር፣ የቴ/ሙ/ሥ ተቋማትን ከሥነ-ምኅዳር ጋራ ተስማሚ እንዲሆኑ የሚያደርግ መሠረተ ልማት ማሻሻያ ስትራቴጂካዊ ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት እና መተግበር፣ በሠልጣኞች፣ በሠራተኞችና በሰፊው የቴ/ሙ/ሥ ማኅበረሰብ ዘንድ በአረንጓዴ ቴ/ሙ/ሥ ልምዶች ላይ ግንዛቤን ማሳደግና ተሳትፎን ማበረታታት የሚያስችል አሠራሮችን መዘርጋትና መተግበር፣ በቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ውስጥ የሚፈጠሩና በግዥ የሚገቡ ቴክኖሎጂዎች አረንጓዴ ኢኮኖሚን ታሳቢ ያደረጉ እንዲሆኑ ማድረግ ናቸው። 37 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የሚጠበቁ ውጤቶች የቴ/ሙ/ሥ ተቋማትን ከሥነ-ምኅዳር ጋራ ተስማሚ እንዲሆኑ የሚያደርግ የተዘጋጀና የተተገበረ የመሠረተ ልማት ማሻሻያ ስትራቴጂካዊ ፍኖተ ካርታ፣ በሥርዓተ ሥልጠና እና በአሠልጣኝ ልማት ፕሮግራሞች ውስጥ የእንደ ታዳሽ ኃይል መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ያሉ የአረንጓዴ ክህሎቶችን ማካተታቸው የተረጋገጠ የቴ/ሙያ ፕሮግራሞች መጨመር፣ ከአረንጓዴ የቴ/ሙያ ጋራ ስምም መሆናቸው የተረጋገጠና የአረንጓዴ ካምፓስ ያላቸው የቴ/ሙያ ተቋማት ቁጥር መጨመር፤ በአርንጓዴ የቴ/ሙያ ላይ ግንዛቤ ያላቸው የተቋም ማህበረሰቦች መጨመር። ቁልፍ ጉዳይ 12፡ የሀገር-በቀል ዕውቀቶችንና ክህሎቶችን በቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት ውስጥ ማዋሓድና መጠቀም የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት ሀገር-በቀል ዕውቀቶችን ለመመዝገብና ለማዋሓድ የሚያስችል የተዋቀረ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ጉልሕ የሆነ ክፍተት ተፈጥሯል። ይህ ሁኔታ ጠቃሚ የሆኑ ባህላዊና ልማዳዊ ክህሎቶች እንዲጠፉና የባህል ቅርስ ጥበቃን የሚያደናቅፍ ከመሆኑም በላይ በባህላዊ ሙያዎች ላይ የሥልጠና ፕሮግራሞችን ለመፍጠር ባለመቻሉ ከዘርፉ የሚጠበቁ የኢኮኖሚ ዕድሎችን መጠቀም እንዳይቻል አድርጓል። ስትራቴጂዎች ለቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት ውሕደት እንዲመች ሀገር-በቀልና ባህላዊ ዕውቀቶችን በተለያዩ ዘርፎች ለመለየት፣ ለመመዝገብና ለማስቀመጥ የሚያስቸል ሀገራዊ ማዕቀፍ መቅረጽና መተገበር፤ የቴ/ ሙያ ሥልጠና ፕሮግራሞችን ከሀገር-በቀል ክህሎቶችና ዕውቀቶች ጋራ እንዲጣጣም ማሻሻል፤ ከእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ጋራ በሽርክናዎች የሚተገበሩ ልዩ የሥልጠና ፕሮግራሞችን መቅረጽና መተግበር፤ ሠልጣኞች ዘመናዊ መሣሪያዎችን ከባህላዊ ልምዶች ጋራ እንዲያዋሕዱ የሚያስችሉ መድረኮችን በመፍጠር የምርምርና ፈጠራ ሥርዓትን መተግበር፤ የቴ/ሙ/ሥ ሠራተኞች፣ ሠልጣኞችና ሰፊው ማኅበረሰብ ዘንድ ሀገር-በቀል ዕውቀቶች በኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጠቀሜታቸው ዕውቅና እንዲያገኙና እንዲከበሩ ለማድረግ ተነሣሽነቶችን ማስጀመር ናቸው። የሚጠበቁ ውጤቶች የቴ/ሙ/ሥ ሥርዓተ ሥልጠና ልማት ውስጥ እንደ መደበኛ መመዘኛ ሆኖ የሚያገለግል ሁሉን ዓቀፍ ሀገራዊ የሀገር-በቀል ዕውቀትና ባህላዊ ክህሎቶች የመረጃ ቋት (Database) መመሥረት፤ ሁሉም የቴ/ሙ/ሥ ሥርዓተ ሥልጠናዎች ሀገር-በቀል ክህሎቶችን በመደበኛነት እንዲያካትቱ መሻሻልና ባለሙያ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች እንደ አማካሪና አሠልጣኞች የሚያገለግሉበት አውታረ-መረብ መፈጠር፤ በሀገር-በቀልና ባህላዊ ሙያዎች የእጅ ጥበብ ላይ የሠለጠኑና የበቁ ባለሙያዎች ቁጥር መጨመር፣ ሠልጣኞችተ ሀገር-በቀል ዕውቀቶችን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋራ በማዋሓድ አዳዲስ ምርቶችንና አገልግሎቶችን በስኬት መፍጠርና ለገበያ ማቅረብ፣ ይህም የሥራ ፈጣሪነትን ማሳደግ፤ ከማኅበረሰብ ሽማግሌዎችና ባለሙያዎች ጋራ መደበኛ ሽርክናዎች መኖር፣ ይህም የባህል ኩራትን መልሶ ለማደስና ባህላዊ ሙያዎችን የሚያሳድዱ ሠልጣኞች ቁጥር እንዲጨምር መምራት ናቸው። ቁልፍ ጉዳይ 13፡ ተጽዕኖ መቋቋም የሚችል እና ተለማጭ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት መገንባት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ቀድሞ በመገመት ለመቆጣጠር እና ለመቀነስ የሚያስችል አጠቃላይ ስትራቴጂዊ ሥርዓት አልነበረውም። በዚህም የተነሣ ዘርፉን ላልተጠበቁ ክሥተቶች ተጋላጭ ሲያደርገው ቆይቷል። በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ 38 ስትራቴጂዎች የቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ከአደጋዎች እንዲያገግሙና ምላሽ እንዲሰጡ የሚያስችል አጠቃላይ ሀገራዊ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ስትራቴጂ ማዘጋጀትና መተግበር፣ በአስቸኳይ ጊዜያት ምቹ ሁኔታን የሚያረጋግጥ የቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት ላይ ኢንቨስት ለማድረግ የሚያስችል ስትራቴጂያዊ የድርጊት መርሓ ግብር ማዘጋጀት እና መተግበር፣ የቴ/ሙ/ሥ ዘርፍ የአስቸኳይ ጊዜ ዝግጁነት ዕቅዶችን፣ የሀብት ክፍፍልን እና ፈጣን ምላሽ የመስጠት ዓቅምን ለማሳደግና ለመደገፍ ከመንግሥት ተቋማት እና ከኢንዱስትሪ መሪዎች ጋራ ስትራቴጂያዊ ትብብር መፍጠር እና ተግባራዊ ማድረግ ናቸው። የሚጠበቁ ውጤቶች የቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ከአደጋዎች እንዲያገግሙና ምላሽ እንዲሰጡ የሚያስችል የተዘጋጀና የተተገበረ ሀገራዊ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ ስትራቴጂ፣ በድንገተኛ ሁኔታዎች አገልግሎታቸውን ማስቀጠል የሚያስችላቸውን ዝቅተኛ መሠረተ ልማትና ዓቅም ያሟሉ የቴ/ሙያ ተቋማት ቁጥር መጨመር፤ በአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ሥልጠናቸውን መቀጠል የቻሉ ተፈናቃይ ሠልጣኞች ቁጥር መጨመር፤ የቴ/ሙ/ሥ ዘርፍ የአስቸኳይ ጊዜ ዝግጁነት ዕቅዶችን፣ የሀብት ክፍፍልን እና ፈጣን ምላሽ የመስጠት ዓቅምን ለማሳደግና ለመደገፍ ከመንግስት ተቋማት እና ከኢንዱስትሪ መሪዎች ጋራ የተፈጠረና የተተገበረ ስትራቴጂያዊ ትብብር የሚጠበቁ ናቸው። 3.3. ትኩረት ሦስት፡ ለሥራ ዝግጁ የሚያደርጉ ክህሎቶችን ማሳደግ ቁልፍ ጉዳይ 1፡ ሥራ ፈጠራን እና የንግድ ሥራን ማጎልበት ሥራ ፈጣሪነትን በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓቱ ውስጥ ውጤታማ በሆነ መንገድ ማቀናጀት ተግዳሮት ሆኖ ቆይቷል። ሥርዓተ ሥልጠናው ለሥራ ፈጠራ፣ ለአዳዲስ የንግድ ሥራዎች ድጋፍ ማድረግ እና ገበያውን መሠረት ያደረገ ሥልጠና ማቅረብ ላይ ችግሮች ያሉበት ሲሆን ከሥራ ፈጠራ ይልቅ ለቴክኒካል ክህሎት ቅድሚያ የሰጠ ነው፡፡ አሠልጣኞችም ቢሆኑ የዕውቀት ክፍተት ያለባቸው ከመሆኑም ባሻገር ከገሃዱ ዓለም የተገኘ ነባራዊ ልምድ እና ለማሰልጠን በቂ ዝግጁነት የጎደላቸው ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች ሠልጣኞች ስለ ንግድ፣ ሥራ ፈጠራ እና የፈጠራ ክህሎቶችን የሚያስጨብጡ የኢንተርፕረነርሺፕ ቴክኒኮችን እና ክህሎቶችን እንዲጨብጡ ይደረጋል ፣ የቴ/ሙ/ሥ አሠልጣኞች የሥራ ፈጠራ ሥልጠናን በብቃት ማሠልጠን የሚያስችል ብቃት እንዲላበሱ ይደረጋል፣ ሠልጣኞች የሥራ ፈጠራና ሥምሪት ክህሎቶቻቸውን ለማዳበር የሚስችላቸው ልል ክህሎቶች (እንደ ኢንዱስትሪ ውስጥ የተግባር ልምምድ እና በሥራ ፈጠራ ስኬታማ የሆኑ አርአያዎችን ልምድ ማካፈል ያሉ) ዜዴዎች ታቅደው ይተገበራሉ፣ በቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ውስጥ የቢዝነስ ኢንኩቤሽን ፕሮግራሞችን በመፍጠር ሥልጠና አጠናቃቂዎች የራሳቸውን ንግድ እንዲጀምሩ እና እንዲያሳድጉ ድጋፍ ይደረጋል፡፡ የሚጠበቁ ውጤቶች የሥራ ፈጠራን በሥርዓተ ሥልጠናዎቻቸው ያካተቱ የቴ/ሙ/ሥ ፕሮግራሞች ቁጥር መጨመር፣ የሥራ ፈጠራ/ኢንተርፕረነርሺፕ/አሠልጣኞች ሥልጠና ያጠናቀቁ አሠልጣኞች ቁጥር መጨመር፣ የንግድ ሥራ የጀመሩ የቴ/ሙ/ሥ አጠናቃቂዎች ቁጥር መጨመር እና የመነሻ ድጋፍ ተደርጎላቸው የተጀመሩ የንግድ ሥራዎች ቁጥር መጨመር ናቸው። 39 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም ቁልፍ ጉዳይ 2፡ የሙያ ማማከር ድጋፍ እና አገልግሎቶችን ማሻሻል ብዙ ሠልጣኞችና የሥልጠና አጠናቃቂዎችም በደንብ የተዋቀረ የሙያ ምክርና ድጋፍ ሳይኖራቸው በያዙት የሙያ መስክ ለመግፋት ይታገላሉ። ይህም የሆነበት ምክንያት የተሟላ መረጃ ካለማግኘት የመነጨ ሲሆን ሠልጣኞች ከወደፊት የሥራ ሕይወት ትልማቸው ጋራ የሚጣጣሙ የሥልጠና መርሓ ግብሮችን በተመለከተ በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዳይወስኑ አድርጓል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች ዝርዝር የሥራ መረጃን፣ ወቅታዊ ክፍት የሥራ ቦታዎችን የሚያሳይ እና የሥልጠና አጠናቃቂዎችን ፕሮፋይል አቀናጅቶ የሚያቀርብ የኦንላይን ፕላትፎርም ይዘጋጃል። ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች የተደራጁ ጠንካራ የሙያ ማማከርና ድጋፍ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ይቋቋማሉ። የሥልጠና አጠናቃቂዎች ኔትወርክና የኢንዱስትሪ አጋርነትን በመጠቀም አጠናቃቂዎች ከአሠሪዎች ጋራ ይገናኛሉ፤ የሥልጠና አጠናቃቂዎች የሥራ ሥምሪትና የሥልጠና ጥራት መከታተያ ሥርዓት ይዘረጋል። የሚጠበቁ ውጤቶች ዝርዝር የሥራ መረጃን፣ ወቅታዊ ክፍት የሥራ ቦታዎችን የሚያሳይ እና የሥልጠና አጠናቃቂዎችን ፕሮፋይል አቀናጅቶ የሚያቀርብ የተዘጋጀ የኦንላይን ፕላትፎርሞች፣ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች የተደራጁ ጠንካራ የሙያ ማማክርና ድጋፍ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት መጨመር፣ በሠልጣኙ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ የሙያ ምክር አገልግሎት ያገኙ ሠልጣኞች፣ የሥልጠና አጠናቃቂዎች ኔትወርክና የኢንዱስትሪ አጋርነትን በመጠቀም ከአሠሪዎች የተገናኙ የሥልጠና አጠናቃቂዎች የሥራ ሥምሪትና የሥልጠና ጥራት መከታተያ የዘረጉ የቴ/ሙያ ተቋማት ናቸው። ቁልፍ ጉዳይ 3፡ ማኅበረሰቡን መሠረት የደረጉ የሥራ ልምምድ (Apprenticeships) እና የትብብር ሥልጠና (Cooperative Training) ማስፋፋት ኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና አብዛኛው ትኩረቱን የሚያደርገው በመደበኛ ሥልጠና ላይ ነው። በዚህም ሳቢያ፣ መደበኛ ያልሆነውን ኢኮኖሚ የሚያግዙ በማኅበረሰብ ላይ የተመሠረቱ ኢ-መደበኛ የሆኑ የሙያ ሥልጠና ሞዴሎችን በበቂ ሁኔታ አይጠቀምም። ይህ ደግሞ የዘርፉን ተደራሽነት በእጅጉ ጎድቶታል። ስትራቴጂዎች ሠልጣኞችን ከሀገር ውስጥ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ከኅብረት ሥራ ማኅበራት እና ከሴቶች/ ወጣቶች ማኅበራት ጋራ በማገናኘት የማኅበረሰብ የሙያ ሥልጠና ሞዴሎችን ማስፋፋት ፤ ባህላዊ የሙያ ሥልጠና ሥርዓቶችን በቀደመ ትምህርት የተገኘን ክህሎትት ዕውቅና መስጠት (RPL) ማዕቀፎች አማካይነት ዕውቅናና የምስክር ወረቀት መስጠት፤ የሀገር ውስጥ ሥራ ፈጣሪነትን ለማስተዋወቅና የድርጅቶችን ዕድገት ለማሳደግ የቴ/ሙ/ሥ ማኅበረሰብ የኅብረት ሥራ ሽርክናዎችን ማቋቋም። የሚጠበቁ ውጤቶች በማኅበረሰብ ላይ በተመሠረቱ የሙያ ሥልጠናዎች ላይ የተመዘገቡ ሠልጣኞች ቁጥር መጨመር፤ የRPL ማዕቀፍን በመጠቀም መደበኛ ያልሆኑ የሙያ ሥልጠናዎችት በይፋ ዕውቅና ማግኘት፤ እንደ ሥልጠና አጋር ሆነው የሚያገለግሉ የኅብረት ሥራ ማኅበራትና የማኅበረሰብ ድርጅቶች ቁጥር መጨመር። 40 ቁልፍ ጉዳይ 4፡ ሀገራዊ የክህሎት ባንክ በማቋቋም የክህሎት ክምችትና ዝውውር ማጎልበት በሀገራችን ያሉ በርካታ ዜጎች ተጨባጭ የሆኑ ክህሎቶች ቢኖሯቸውም እነዚህን ክህሎቶች በይፋዊነት ለማስመዝገብና ለመጠቀም የሚያስችል ሥርዓት የለም። ይህም ዜጎች በያዙት ክህሎት ተጠቃሚ እንዳይሆኑ፣ የሥራ ዕድል እንዲያጡ፣ እንዲሁም ሀገሪቷም ያሏትን የሰው ኃይል ዓቅም በአግባቡ እንዳትጠቀም ያግዳታል። በመሆኑም፣ ሀገራዊ የክህሎት ባንክ በማቋቋም፣ የዜጎችን ክህሎቶች በይፋዊነት የመመዝገብና የማስተላለፍ ሂደቱን ማጎልበት፣ የክህሎት ክምችትና ዝውውርን በማሳደግ ዜጎች በክህሎታቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑና ለሀገራዊ ልማት አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ያስችላል። ስትራቴጂዎች የክህሎት መረጃ መሰብሰቢያና ምዝገባ ሥርዓት መዘርጋት፤ በተለያዩ ዘርፎች ያሉ ዜጎች ያላቸውን ክህሎት እንዲመዘግቡ የሚያስችል ዘመናዊና ተደራሽ የሆነ የመረጃ ቋት መፍጠር፤ የክህሎት ዕውቅናና ምዘና ማዕቀፍ ማዘጋጀት: የዜጎችን ክህሎት በይፋ ዕውቅና እንዲያገኙ የሚያስችል ግልጽና ተጨባጭ የሆነ የመመዘኛ መመሪያዎችን ማውጣት፤ የሥራ ዕድልና የክህሎት ፍላጎት ጋራ ማጣጣም፤ በክህሎት ባንኩ የተመዘገቡ ክህሎቶችን ከገበያው የሥራ ዕድል ፍላጎት ጋራ በማገናኘት የሥራ ቅጥር ሂደትን ማመቻቸት፤ የክህሎት ልውውጥና ቀጣይነትን ለማበረታታት፤ የተመዘገቡ ክህሎቶች እንዲሻሻሉና አዳዲስ ክህሎቶች እንዲጨመሩ የሚያስችሉ የሥልጠናና የልምድ ልውውጥ መድረኮችን ማዘጋጀት። የሚጠበቁ ውጤቶች በሀገር ዓቀፍ ደረጃ በዜጎች የተያዙት ክህሎቶች በግልጽ ተለይተውና ተመዝግበው የሚገኙበት የተሟላ የክህሎት መረጃ ቋት መኖር፤ የተሻሻለ የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት፤ ዜጎች ያላቸውን ክህሎት በሥራ ገበያው ተፈላጊነት መሠረት የሥራ ዕድል የሚያገኙበት ዕድልና ተጠቃሚነት መጨመር፤ ክህሎቶች ከአንድ ዘርፍ ወደ ሌላ በቀላሉ የሚተላለፉበትና የሚከማቹበት ምቹ ሁኔታ መፈጠር፤ የተመዘገቡ ክህሎቶች እንዲሻሻሉና አዳዲስ ክህሎቶች እንዲጨመሩ የሚያስችሉ የሥልጠናና የልምድ ልውውጥ መድረኮች ማዘጋጀት ናቸው። ቁልፍ ጉዳይ 5፡ ለቀደመ ትምህርት ዕውቅና መስጠት (RPL) ለቀደመ ትምህርት ዕውቅና በመስጠት (RPL) ረገድ ብዙ ርቀት መጓዝ ያለበት መሆኑ ወቅቱ የሚጠይቅ ቢሆንም ወጥ የሆነ አገልግሎት ሰጪ መዋቅር ባለመኖሩ በልምድ ለተገኘ ዕውቀት ዕውቅና የመስጠት ተግባር ተግዳሮት ያለበት እንዲሆን አድርጓል። በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች በሁሉም ዘርፎች እና ክልሎች ለቀደመ ትምህርት ዕውቅና የመስጠት ሂደቶችን ለማቀላጠፍ ዕውቅና የመስጫ ማዕቀፍ ማዘጋጀት እና መተግበር፣ አጠቃላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስትራቴጂ በማዘጋጀት ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ለቀደመ ትምህርት ዕውቅና ግንዛቤ ማስጨበጥ፣ በቀደመ ትምህርት ዕውቅና ሰርተፊኬት የያዙ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎችን መዛኞች አድርጎ ለመጠቀም የሚያስችል ሀገራዊ መርሓ ግብር ማዘጋጀት እና በሥራ ላይ ማዋል ናቸው። የሚጠበቁ ውጤቶች በሁሉም ዘርፎች እና ክልሎች ለቀደመ ትምህርት ዕውቅና የመስጠት ሂደቶችን ለማቀላጠፍ የተዘጋጀ እና የተተገበረ ዕውቅና የመስጫ ማዕቀፍ፣ የቀደመ ትምህርት ዕውቅና የሚያስገኙ ምዘናዎችን የሚወስዱ ሰዎች ቁጥር መጨመር፣ የቀደመ ትምህርት ዕውቅና መዛኝነት የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ቁጥር መጨመር ናቸው። 41 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም ቁልፍ ጉዳይ 6፡ በሀገር ውስጥ እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የሚገኙ የሥራ ገበያ ዕድሎችን ማሳደግ በኢትዮጵያ የሚፈለገውን መስፈርት የሚያሟላ የሰው ኃይል ለዓለም ዓቀፍ ገበያ የማቅረብ ፍላጎት ቢኖርም ሥርዓተ ሥልጠናው ከዓለም ዓቀፍ የሥራ ፍላጎት ጋራ ተስማሚ ባለመሆኑ በሚፈለገው ልክ ውጤት ማምጣት አልተቻለም። በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች የቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ሥልጠና አጠናቃቂዎችን ለውጭ ሀገር የሥራ ቅጥር በልዩ ሥልጠናዎች ለማዘጋጀት ሥርዓተ ሥልጠናዎች እንዲዘምኑ ይደረጋል። ከመዳረሻ ሀገራት ጋራ የጋራ የብቃት ዕውቅና ስምምነቶች ይደረጋል፣ የቴ/ሙ/ሥ አጠናቃቂዎች ለዓለም ዓቀፍ የሥራ ገበያ ያላቸውን ዝግጁነት የሚያሳድጉና በመዳረሻ ሀገራት ዕውቅና ባገኙ ክህሎቶች ላይ የሚያተኩር ሥልጠና እንዲያገኙ ይደረጋል፤ እንደ አስፈላጊነቱ በውጪ የሥራ ገበያ ላይ ትኩረት አድርገው የሚያሰለጥኑ ተቋማት ማደራጀት ናቸው። የሚጠበቁ ውጤቶች የቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ሥልጠና አጠናቃቂዎችን ለውጭ ሀገር የሥራ ቅጥር በልዩ ሥልጠናዎች ለማዘጋጀት የዘመኑ ሥርዓተ ሥልጠናዎች፣ ከመዳረሻ ሀገራት ጋራ የጋራ የብቃት ዕውቅና የተደረገ ስምምነት፣ የቴ/ሙ/ሥ ሥልጠና አጠናቃቂዎች ለዓለም ዓቀፍ የሥራ ገበያ ያላቸውን ዝግጁነት የሚያሳድጉና በመዳረሻ ሀገራት ዕውቅና ባገኙ ክህሎቶች ላይ ያተኮረ የሥልጠና ፕሮግራሞች መጨመር፣ በውጪ የሥራ ገበያ ላይ ትኩረት አድርገው የሚያሠለጥኑ ተቋማት መጨመር፤ ለውጪ ሀገር የሥራ ሥምሪት ብቃታቸው የተረጋገጠ ባለሙያዎች ቁጥር መጨመር። 42 43 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም 3.4 ትኩረት አራት፡ የምርምር እና ፈጠራን ሥነ-ምኅዳር ማበልጸግ ቁልፍ ጉዳይ 1፡ የቴ/ሙ/ሥ ጥናትና ምርምር ምኅዳርን ማበልጸግ በቴክኖሎጂ የታገዘ የምርምርና ፈጠራ ሥነ-ምኅዳሮች ወጥ የሆነ የተቀናጀ የትብብር ማዕቀፍ ባለመኖሩ የቴ/ሙ/ሥ ሥርዓቱ ያለውን እምቅ ዓቅም ማሳደግ ሳይችል ቆይቷል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች ፈጠራን የሚያጎለብት ጠንካራ የቴ/ሙ/ሥ የምርምር ሥነ-ምኅዳር መገንባት የሚያስችል ሀገራዊ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ ይደረጋል። በኢንዱስትሪ፣ በአካዳሚክ እና በምርምር ተቋማት መካከል ያለውን አጋርነት ለማጠናከር ስትራቴጂካዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀትና መተግበር፤ ለቴ/ሙ/ሥ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች በምርምር ዘዴዎች፣ በመረጃ ትንተና እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ምርጥ ተሞክሮዎች ቅመራ ላይ ያላቸውን ብቃት ማሳደግ የሚያስችሉ ልዩ የሥልጠና ፕሮግራሞችን ማዘጋጀትና መተግበር፤ የፋይናንስ ምንጭ ከማስፋት አኳያ የመንግሥት፣ የግሉ ዘርፍ እና ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶችን ቀልብ ለመሳብ የሚያስችል ማዕቀፍ ማዘጋጀት፤ በቴ/ሙ/ሥ ሥነ-ምኅዳር ውስጥ ያሉ የምርምር ሥራዎችን ለመከታተልና ለመገምገም የሚያስችል ጠንካራ ሥርዓት ይዘረጋል። የሚጠበቁ ውጤቶች ፈጠራን የሚያጎለብት ጠንካራ የቴ/ሙ/ሥ የምርምር ሥነ-ምኅዳር መገንባት የሚያስችል የተዘጋጀ ሀገራዊ ስትራቴጂ፤ በኢንዱስትሪ፣ በአካዳሚክና በምርምር ተቋማት መካከል የተጠናከረ አጋርነት ለመፍጠር የተዘጋጀ ማዕቀፍ፤በቴ/ሙ/ሥ ዘርፍ ውስጥ በምርምር ዘዴዎች የበቃ ባለሙያና ተመራማሪ፤ ምርምሮችን ለመደገፍ የተዘጋጀ አማራጭ ፋይናንስ ምንጭ ማዕቀፍ፤ የምርምር ሥራዎችን ለመከታተልና ለመገምገም የተዘረጋ ጠንካራ ሥርዓት፤ በምርምርና የፈጠራ ሥራ ላይ የሚሳተፉ የተቋማት አሠልጣኞች ቁጥር መጨመር፣ በምርምር የዳበሩ ቴክኖሎጂዎችና ፈጠራዎች መጨመር፣ ለምርምርና ፈጠራ የዋለ ሀብት መጨመር፣ የአእምሯዊ ሀብት ባለቤትነት መብት የተጠበቀላቸው የፈጠራ ውጤቶች መጨመር፤ ከእንዱስትሪና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋራ በትብብር የተሠሩ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች መጨመር። ቁልፍ ጉዳይ 2፡ በዜጎች የሚመራ ፈጠራ እና ማኅበራዊ የፈጠራ ማዕከሎች (Social Inno vation Labs) በቴ/ሙያ ዘርፉ በአሁኑ ጊዜ ያሉ የፈጠራ ተነሣሽነቶች በአብዛኛው የሚያተኩሩት በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ሲሆን፣ ከሕዝብ የሚመነጩ ማኅበራዊ ፈጠራዎችንና ችግር ፈቺ መፍትሔዎችን ችላ ይላሉ። ይህም ማኅበረሰቦችና ዜጎች አካባቢያቸውን በሚመጥን መልኩ በጋራ መፍትሔዎችን የመፍጠር ከፍተኛ አቅማቸው ጥቅም ላይ እንዳይውል አድርጓል። በመሆኑም፣ የፈጠራ ሥርዓታችን የቴክኖሎጂ ሽግግርን ብቻ ሳይሆን፣ ከማኅበረሰብ የሚመጡ ሐሳቦችን በማካተት የፈጠራ ባህል እንዲዳብር መሥራት ይኖርበታል። ስትራቴጂዎች በማኅበረሰብ ላይ የተመሠረቱ መፍትሔዎችን ለማመንጨት በቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ውስጥ የዜጎች የፈጠራ ማዕከላት ማቋቋም፤ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊና ማኅበራዊ ችግሮችን የሚፈቱ የማኅበረሰብ ፈጠራ ፈተናዎችና ውድድሮች ማካሄድ፤ በማኅበረሰብ ላይ በተመሠረተ ልማት ላይ ትኩረት በማድረግ ማኅበራዊ ፈጠራ ምርምሮችን በቴ/ሙ/ሥ የምርምር ቅድሚያዎች ውስጥ ማካተት። የሚጠበቁ ውጤቶች በዜጎች የሚመሩ የፈጠራ ማዕከላትን የሚያስተናግዱ የቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ቁጥር መጨመር፤ በየዓመቱ የሚካሄዱ የማኅበረሰብ ፈጠራ ፕሮጀክቶችና ውድድሮች ቁጥር መጨመር፤ የቴ/ ሙ/ሥ ፖሊሲና አሠራር ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የማኅበራዊ ፈጠራ ምርምሮች ውጤቶች ቁጥር መጨመር። ቁልፍ ጉዳይ 3፡ የቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደቱን ለመጠቀም ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ መተግበር የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት ዋነኛ ችግር ለቴክኖሎጂ ሽግግር የሚያገለግል ስትራቴጂካዊ ማዕቀፍ አለመኖሩ ነው። ይህም በሥልጠናው ውስጥ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ልማት ተሳትፎ ደካማ እንዲሆን አድርጓል። በተጨማሪም የአሠልጣኞች የባለሙያ ብቃት ማነስ፣ በቂ ያልሆነ የገንዘብ ድጋፍ፣ ደካማ የኢንዱስትሪ ትብብርና የጥናትና ምርምር ባህል አለመኖር ቴክኖሎጂን ለጅምላ ምርትና ለንግድ ትስስር (commercialization) በማዋል ሂደት ላይ እንቅፋት ሆነውበታል። በዚህም ምክንያት ሥርዓቱ ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ውስን ሆኗል። ስትራቴጂዎች ግልጽ መመሪያዎች፣ ማበረታቻዎችና የአእምሯዊ ንብረት መብቶችን የሚመሩ ፖሊሲዎች ያሉት ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕቀፍ ማዘጋጀት፤ በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ላይ ያለውን የቴክኒክ ባለሙያ ዕውቀት ክፍተት ለመሙላት ለቴ/ሙ/ሥ አሠልጣኞችና ሠራተኞች ሁሉን ዓቀፍ የብቃት ማጎልበቻ ፕሮግራም ማዘጋጀትና መተግበር፤ ትብብርንና ምርምርን ለማጎልበት በቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ውስጥ ሀገራዊ የፈጠራ ማዕከላትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕከላትን ማቋቋም እና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፤ ፕሮግራሞች ከዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ጋራ መጣጣማቸውን ለማረጋገጥ የቴክኖሎጂ ሽግግር መርሖዎችን በቴ/ሙ/ሥ ሥርዓተ ሥልጠና ውስጥ ማዋሓድ፤ የቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት የረጅም ጊዜ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ ለአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ግዥ፣ ጥገናና መጠገኛ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት። የሚጠበቁ ውጤቶች በቴ/ሙ/ሥ የተገነቡ ፈጠራዎች ጋራ የተያያዙ የአእምሯዊ ንብረት መብቶች ቁጥር መጨመር ፤ የቴ/ሙ/ሥ ሠራተኞች የሚወስዱት የውጭ የሥራ ልምምድ ፕሮግራሞች ቁጥር መጨመር፣ በቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ውስጥ የተቋቋሙ መደበኛ የፈጠራ ማዕከላት ቁጥር መጨመር፤ በቴ/ ሙ/ሥ ተቋማትና በአካባቢ ኢንዱስትሪዎች መካከል በጋራ የሚሠሩ የፈጠራ ፕሮጀክቶች ቁጥር መጨመር፤ ፕሮግራሞች ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋራ መጣጣማቸውን ለማረጋገጥ የቴክኖሎጂ ሽግግር ማዕቀፍ በቴ/ሙ/ሥ ሥርዓተ ትምህርት ውስጥ መዋሓድ። ቁልፍ ጉዳይ 4፡ የማኅበረሰብ አገልግሎትን ማሳደግ የቴ/ሙ/ሥ/ ተቋማት የሚሰጡት የማኅበረሰብ አገልግሎቶች በአመራር ብቃት ማነስ፣ የአሠልጣኞች ፈቃደኛነት ማነስና ውስን የሀብት አቅርቦት ምክንያት ውጤታማ አይደሉም። በመሆኑም እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታት የሚከተሉት ስትራቴጂዎች ይተገበራሉ፡፡ ስትራቴጂዎች የሁሉንም ባለድርሻ አካላት እና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተጠቃሚዎችን ሚና የሚያጎለብት ስትራቴጅክ ፕሮግራም ማዘጋጀት እና መተግበር፤ ጠንካራ የማኅበረሰብ አገልግሎት ማዕቀፍ ማዘጋጀት እና መተግበር፤ በማኅበረሰብ አገልግሎቱ በባለድርሻ አካላት መካከል የመረጃ ፍሰትን የሚያሳልጥ የግንኙነት ማዕቀፍ ማዘጋጀት እና መተግበር፤ የአካባቢ ማኅበረሰብን ልዩ ፍላጎት ለመለየት እና የማኅበረሰብ አገልግሎት ፋይዳዎችን ለመገምገም የሚያስችሉ ስትራቴጂያዊ የምርምር ሥራዎችን ማዘጋጀት እና መተግበር፤ በቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ማኅበረሰብ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ለማስፋፋት የሚያስችል ግልጽ የሆነ ፕሮግራም ማዘጋጀትና መተግበር፡፡ 44 45 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የሚጠበቁ ውጤቶች ውጤታማ የማኅበረሰብ አገለግሎትን እውን ለማድርግ ተዘጋጅተው የተተገበሩ ማዕቀፎች፤ ውጤታማ የማኅበረሰብና የኢንዱስትሪ አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት የገነቡ ተቋማት ቁጥር መጨመር፣ በኢንዱስትሪና በማኅበረሰብ አገልግሎት ተደራሽ የሆኑ አካላት ቁጥር መጨመር፣ ከኢንዱስትሪዎችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በጋራ የተሰጡ የማኅበረሰብ አገልግሎቶች መጨመር፣ ከኢንዱስትሪዎች፣ ከማኅበረሰቦች እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ለማኅበረሰብ አገልግሎት የሚሰበሰብ ሀብት መጨመር። ቁልፍ ጉዳይ 5፡ በተሰጥኦ ላይ የተመሠረተ ሥልጠናና ምደባ ሥርዓት በመተግበር ተሰጥኦን መፈለግና ማዳበር የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት ተሰጥኦን ለመለየትና ለማጎልበት የተዋቀረ አቀራረብ ስለሌለው ለሁሉም ሰው የሚሆን አንድ ወጥ ሞዴል እንዲፈጠር አድርጓል። ይህ ደግሞ ከፍተኛ የሠልጣኞች ሥልጠናን ማቋረጥና፣ በሥልጠና አጠናቃቂዎች ክህሎትና በሥራ ገበያ ፍላጎት መካከል ከፍተኛ የሆነ አለመጣጣም እንዲኖር በማድረግ ልዩና በከፍተኛ ደረጃ የሠለጠነ የሰው ኃይል እንዳይዳብር ይገድባል። ስትራቴጂዎች መደበኛ የችሎታ መለያ ምዘናዎችንና ጠንካራ የሙያ ማማክርና ድጋፍ አገልግሎትን በመጠቀም በተሰጥኦ ላይ የተመሠረተ ምዘናና ለግል የተበጀ የሙያ መስመር የሚያስችል ሁሉን ዓቀፍ ማዕቀፍ ማዘጋጀት፤ ልዩ የልህቀት ማዕከሎችን በማቋቋም፣ የክህሎት ውድድሮችንና የተሰጥኦ ማሳያዎችን በመተግበር የተሰጥኦ ልማትን በቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት ውስጥ ማካተት፤ የላቀ ውጤት ላመጡ ሠልጣኞችና ተቋማት ሀገራዊ የዕውቅና ፕሮግራምና የማበረታቻ ዘዴዎችን በመፍጠር የልህቀትና ከፍተኛ ስኬት ባህልን ማዳበር፤ የሥልጠና አጠናቃቂዎችን ክህሎት ከአሠሪዎች ፍላጎት ጋራ ቀጥተኛ ተዛማጅነት እንዳለው ለማረጋገጥ በአፈጻጸም ላይ የተመሠረተ ምደባን መደበኛ ማድረግ፣ ይህም ለሥልጠና አጠናቃቂዎችና ለኢኮኖሚው የተሻለ ውጤት ማምጣትን ያረጋግጣል። የሚጠበቁ ውጤቶች ተሰጥኦን ለመለየት፣ ለማሳደግና ለመመዘን የሚያስችል አጠቃላይ ማዕቀፍ በሁሉም ክልሎችና የቴ/ሙያ ተቋማት ሙሉ በሙሉ መተግበር፣ ተቋማዊ፣ ክልላዊና ሀገር ዓቀፍ ውድድሮች በተሳካ ሁኔታ መካሄድ፤ በልዩ የሙያ ተሰጥኦ ውድድር አማካይነት ተለይተው ከትትል የሚደረግባቸውና ዕውቅና የሚሰጣቸው ግለሰቦች ቁጥር መጨመር፤ ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ዜጎች የሚያስተናግዱ የቴ/ሙ/ሥ የልህቀት ማዕከላት ቁጥር መጨመር፤ በአፈጻጸም ላይ የተመሠረተ የሥራ ምደባ ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ተግባባራዊ መሆን ይህም ከሥልጠና አጠናቃቂዎች ክህሎትና ከአሠሪዎች ፍላጎት ጋራ ቀጥተኛ ተዛማጅነት ባላቸው ሥራዎች የሚቀጠሩ ሥልጠና አጠናቃቂዎች ቁጥር እንዲጨምር ያደርጋል። 46 ክፍል አራት 47 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም ክፍል አራት የስትራቴጂው ትግበራ ስትራቴጂካዊ ማዕቀፎች ይህ ክፍል ሀገራዊ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ትግበራ የሚመራበትን አስፈላጊ መርሖች እና ዘዴዎች ያብራራል። ከቴ/ሙ/ሥ ጋራ በተያያዘ የሀብት ማሰባሰብ፣ የአደጋ ቅነሳ፣ ክትትል፣ ግምገማ እና ልምድ ቅመራን፣ ተቋማዊ የአሠራር ሞዴል፣ የአፈጻጸም ልህቀት፣ ተቋሟዊ ዓላማን ማስተማርና ማስተዋወቅ፣ የማኅበረሰብን ግንዛቤን ማሳደግ እና ተደራሽነት የማረጋገጥ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ እና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ ትግበራ የኃላፊነት፣ ተጠያቂነት፣ ምክር የሚሰጥ እና እንዲያውቀው መረጃ የሚሰጠው አካል ማትሪክስ (ኃተምእ)- በእንግሊዝኛው አጠራር RACI/Responsible, Accountable, Consulted and Informed/ ስሆን የማዕቀፎቹን መሠረታዊ መርሖችን የያዘ ጭምር ነው። በአጠቃላይ የትግበራ ማዕቀፎቹ የቴ/ሙ/ሥ ስትራቴጂያዊ ሪዕይን ወደ ተጨባጭ እና ሊለካ ወደሚችል ውጤት ለመቀየር የሚያስችል የትግበራ ፍኖተ ካርታ ነው። 4.1. የሀብት ማሰባሰብ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ የሀብት ማሰባሰብ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ ሀገራዊ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ፕሮግራምን ከሀገሪቱ የልማት ዓላማዎች ጋራ በማጣጣም ለትግበራው የሚያስፈልገውን ሀብት ለማሰባሰብ ያለመ ሲሆን የትግበራ ዕቅዱ በደረጃ የተከፋፈለ፤ ማለትም የአጭር ጊዜ ግቡ (2018-2020ዓ.ም.) የፖሊሲ ማጣጣም ሲሆን፣ የረጅም ጊዜ ግቡ (2021-2023ዓ.ም.) ደግሞ በአፈጻጸም ላይ የተመሠረተ የፋይናንስ ምደባን መተግበር ነው። ማዕቀፉ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማሻሻል የክህሎት ልማት ክፍያን በማስተዋወቅ የኢንዱስትሪ ተሳትፎን ለማሳደግ እና ለማበረታታት፣ እንዲሁም የመንግሥት እና የግል አጋርነትን በማጎልበት የጋራ ተጠያቂነትን ባህል ያረጋግጣል። ማዕቀፉ ተቋማት ከመንግሥት እና ከሌሎች የውጪ የፋይናንስ ምንጮች ላይ ያላቸውን ጥገኝነት ለመቀነስ ትኩረት ይሰጣል። ይህንን ለማሳካት የቴ/ሙ/ሥ ተቋማት በፋሲሊቲ ኪራይ፣ በማማከር አገልግሎት እና ከሥልጠና በሚገኝ ክፍያ ገቢ እንዲያፈሩ በማድረግ ለውስጥ ገቢ ማስገኛ ዘዴዎች ትኩረት እንዲሰጡ ይደረጋል። በተጨማሪም፣ ዓለም ዓቀፍ የፋይናንስ ድጋፎችን ለማሰባሰብ፣ የለጋሾችን ድጋፍ ለማብዛት፣ እና የዘርፉን የሪፎርም ትኩረት (እንደ ዲጂታላይዜሽን፣ ሥርዓተ-ፆታ እኩልነት እና አረንጓዴ ክህሎቶች) ከዓለም ዓቀፍ ቅድሚያ እይታዎች ጋራ ለማጣጣም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና የጋራ ፈንድ እንዲቋቋም በመፍትሔነት ያቀርባል። ተጨማሪ የፋይናንስ ምንጮች የማኅበረሰብ ልገሳዎች፣ የኮርፖሬት ማኅበራዊ ኃላፊነት ኢንቨስትመንቶች፣ በእርዳታ የተደገፈ ለዚህ ዓላማ ብቻ የሚውል የቴ/ሙ/ሥ መሠረተ ልማት ፈንድ፣ የዝቅተኛ ወለድ ብድሮች፣ እና የመንግሥት እና የግሉ ዘርፍ ትብብሮችን ያካትታል። ስትራቴጂው ዓለም ዓቀፋዊ ትስስርን ለማሳደግ ከኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች ጋራ በትብብር መሥራት እና ዲጂታል መድረኮችን በመጠቀም ሥልጠና አጠናቃቂዎችን ከዓለም ዓቀፍ ቀጣሪዎች ጋራ ማገናኘት ላይ ያተኩራል። የቴ/ሙ ሥርዓተ ሥልጠና ለአረንጓዴ ክህሎት ትኩረት እንዲሰጥ በማድረግ ሠልጣኞች ለወደ ፊቱ ዘላቂ የሥራ ገበያ እንዲዘጋጁ በማድረግ ኢትዮጵያ ለአካባቢ ጥበቃ ያላትን ቁርጠኝነት ያጠናክራል። ይህ ማዕቀፍ በፈጻሚ አካላት የበለጠ ተዘጋጅቶ ማለትም የሀብት ማሰባሰብ ስትራቴጂያዊ አካሄድ፣ የጊዜ ሰሌዳ፣ ሚናዎችን እና ኃላፊነቶችን ጨምሮ በዕቅድና መርሓ-ግብር ዳብሮ ተግባራዊ ይሆናል። 4.2. የስትራቴጂ ትግበራ ሥጋት እና የሥጋት ቅነሳ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ ማጠቃለያ ይህ የ2017ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ ትግበራ ሥጋትና የሥጋት ቅነሳ ማዕቀፍ፣ ሥርዓታዊ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የሀገሪቱን የቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት ለማሻሻል የሚድረገውን ጥረት ለመደገፍ የተነደፈ ነው። ማዕቀፉ በአራት ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች ውስጥ ቁልፍ ተጋላጭነቶችን በመለየት፣ ሊከሠቱ የሚችሉበትን ዕድልና ተጽዕኖ በመገምገም፣ እንዲሁም ተግባራዊ የማቃለያ ስትራቴጂዎችን ያስቀመጠ ነው። ማዕቀፉ ከትግበራ ጋራ የተያያዙ ወሳኝ ሥጋቶችን በመለየት ተግባራዊ የማቃለያ እርምጃዎችን ያቀርባል። ለምሳሌ የተበጣጠሰ አሠራር፣ ያልተረጋጋ የፋይናንስ ድጋፍ፣ ደካማ የመረጃ አስተዳደር፣ ከጊዜው ጋራ የማይሄድ ሥርዓተ ሥልጠና፣ የአሠልጣኞች ብቃት ማነስ፣ የሥልጠና መሠረተ ልማት እጥረት፣ ከፍተኛ የወጣቶች የሥራ አጥነት፣ ዝቅተኛ የኢንተርፕረነርሺፕ ተነሣሽነት፣ ደካማ የቅድመ ትምህርት ዕውቅና (RPL) ትግበራ፣ ውስን የምርምር ባህል፣ እና ቴክኖሎጂን የማላመድ ክፍተቶች ያሉ ጉዳዮችን ያጠቃለለ ነው። ሥጋትን ለመቀነስ የሚከተሏቸው መርሖዎች የባለድርሻ አካላት ትብብርን (ለምሳሌ የዘርፍ ክህሎት ምክር ቤቶች)፣ ቀጣይነት ያለው ክትትልና ግምገማን ማዕቀፍ (MEAL Framework)፣ የሀብት ማሰባሰብን እና የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎችን ቅድሚያ መስጠትን ያካትታሉ። ይህ ማዕቀፍ ከMEAL ሥርዓት ጋራ በመዋሃድ፣ ለእያንዳንዱ የሥጋት ቅነሳ እርምጃ ባለቤት በመመደብ፣ እና በየሁለት ዓመቱ ሥጋቶችን በመገምገም ይተገበራል። እነዚህን ሥጋቶች ስልታዊ በሆነ መንገድ በመቅረፍ፣ የ2017ዓ.ም የቴ/ሙ/ሥ ስትራቴጂ ሀገራዊ ልማትን የሚመራ የሠለጠነ፣ ፈጠራን የተላበሰ እና ችግርን የመቋቋም ዓቅም ያለው የሰው ኃይል ለመፍጠር ያለውን ሪዕይ ማሳካት የሚያስችል ሲሆን፣ በዚህ ሂደት ልያጋጥም የሚችል አደጋ መለያ አካሄድ፣ የጊዜ ሰሌዳ፣ ሚናዎችን እና ኃላፊነቶችን ጨምሮ በፈጻሚ አካላት በቀጣይ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል። 4.3. የክትትል፣ ግምገማ፣ ተጠያቂነት እና ተሞክሮ ቅመራ (MEAL) ማዕቀፍ ማጠቃለያ ይህ ማዕቀፉ የቴ/ሙ/ሥ ፕሮግራሞችን ውጤታማ ትግበራ፣ ቀጣይነት ያለው መሻሻል እና ከሴክተር ግቦች ጋራ መጣጣምን ከሥር ከሥሩ በሚሰጥ ግብረ መልስ እና ሊለካ በሚችል ውጤት አማካይነት ያረጋግጣል። በተጨማሪም የቴ/ሙ/ሥ ፕሮግራሞችን ጥራትና ተጽዕኖ ከፍ በማድረግ የሥልጠና አጠናቃቂዎችን የሥራ ዕድል ያሻሽላል። እንዲሁም በተጨባጭ ማስረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ አሰጣጥን የሚያረጋግጥ ስሆን በንዑስ ማዕቀፎች ማለትም የክትትል ማዕቀፍ፣ የግምገማ ማዕቀፍ፣ የተሞክሮ ቅመራ ማዕቀፍ እና የተጠያቂነት ማዕቀፎች መርሕ የሚመራ ይሆናል። የክትትል ማዕቀፉ ዓላማ የእያንዳንዱን የቴ/ሙ/ሥ ሪፎርም ስትራቴጂካዊ ንዑስ ክፍል አፈጻጸም ደረጃ በደረጃ በመከታተል ማናቸውም መዛባት በፍጥነት እንዲታወቅና መፍትሄ እንዲሰጥበት ማድረግ ነው። ይህም የቁጥጥርና የሕግ ማዕቀፎችን ማጣጣም፣ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ቅንጅት፣ የቴ/ሙ/ሥ የፋይናንስ ምንጭን ማስፋት፣ የተሻሻለ መሠረተ ልማት፣ የጥራት ማረጋገጫ ሥርዓት ማሻሻል፣ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ፣ ተደራሽነትን እና ፍትሓዊነትን ማሻሻል፣ ሕዝቡ ለቴ/ሙ/ሥ ያለውን አመለካከት ማሻሻል፣ የቴ/ሙ/ሥ የሥራ ገበያ መረጃ አያያዝን ማሻሻል፣ እና የMEAL ማዕቀፉን ማሻሻልን ያጠቃልላል። 48 49 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የግምገማ ማዕቀፉ ዓላማ ደግሞ የእያንዳንዱን ስትራቴጂካዊ አካል ተጽዕኖ፣ ውጤታማነት እና አጠቃላይ አፈጻጸምን በመገምገም፣ የቴ/ሙ/ሥ ማሻሻያ በ2023ዓ.ም. የሚፈለገውን ውጤት እንደሚያስገኝ ማረጋገጥ ነው። ይህ የሙያ ደረጃዎችንና ሥርዓተ ሥልጠናን ማሻሻል፣ የቴ/ሙ/ሥ አሰጣጥን ማሻሻል፣ የብቃት ምዘናና የማረጋገጫ ሰርተፊኬት አሰጣጥን ማሻሻል፣ የአሠልጣኝ መምህራንንና የአመራሩን ልማት፣ መደበኛ ያልሆነውን ዘርፍ ክህሎት ማሻሻል፣ የኢንተርፕረነርሺፕ እና የንግድ ልማትን ማሻሻል፣ የሙያ ዕድገት መሰላል መመሪያና አገልግሎቶችን ማሻሻል፣ ለቀደመ ሥልጠና ዕውቅና መስጠት፣ ዓለም ዓቀፍ የሥራ ገበያ እድሎችን ማሳደግ፣ የምርምርና ፈጠራ ምኅዳርን ማበልጸግ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር ሂደትን ጠቀሜታ ማሳደግ፣ ዲጂታላይዜሽንና አረንጓዴ ቴ/ሙ/ሥን ማሻሻል፣ የሀገር-በቀል ዕውቀት አጠቃቀምን ማሳደግ፣ እና ለሥጋት ጊዜ ምላሽ የሚሰጥ የቴ/ሙ/ሥ ሥርዓት መዘርጋትን ይገመግማል። የተሞክሮ ቅመራ ማዕቀፉ ዓላማ ምርጥ ተሞክሮዎችን መያዝ፣ የተቀሠሙ ልምዶችንና ትምህርቶችን መሰነድ እና የቴ/ሙ/ሥ ስትራቴጂን ቀጣይነት ባለው መልኩ በሁሉም ባለድርሻ አካላት በሚሰጥ ምላሽና ነባራዊ ልምድ ላይ ተመሥርቶ ከሁኔታዎች ጋራ እያላመደ እንዲሄድ ማድረግ ነው። የተጠያቂነት ማዕቀፉ ዓላማ ሁሉም ባለድርሻ አካላት – መንግሥት፣ ተቋማት፣ ኢንዱስትሪ አጋሮች እና ማህበረሰቦች – የቴ/ሙ/ሥ ማሻሻያ ተግባራት በግልጽ መተግበራቸውን በማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ ግቦችን በ2023ዓ.ም. የማሳካት ኃላፊነት እንዲሸከሙ ማድረግ ነው። ይህ የቁጥጥርና የሕግ ተገዢነት፣ የባለድርሻ አካላት ኃላፊነት፣ የፋይናንስ፣ የመሠረተ ልማት፣ የጥራት ማረጋገጫ፣ የግል ዘርፍ ተሳትፎ ፣ የፍትሓዊነትና አካታችነት፣ የመረጃ አስተዳደር፣ የMEAL ሥርዓት፣ የሥልጠና አሰጣጥ፣ ምዘናና የምስክር ወረቀት አሰጣጥ፣ የመምህራንና አመራር ልማት፣ የኢ-መደበኛ ዘርፍ ሥልጠናና ዕውቅና፣ የኢንተርፕረነርሺፕ፣ የሥራ ማማከር፣ ዓለም ዓቀፍ የሥራ ገበያ፣ ምርምር ሥነ-ምኅዳር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ዲጂታላይዜሽንና አረንጓዴ፣ ሀገር-በቀል እውቀት፣ እና ለአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጪነት ተጠያቂነትን የሚያረገግጥ ሲሆን ዝርዝር ስትራቴጂክ አካሄድ፣ የጊዜ ሰሌዳ፣ ሚናዎችን እና ኃላፊነቶችን ጨምሮ በየደረጃው ባሉ ፈጻሚ አካላት በቀጣይ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል። 4.4. ተቋማዊ የአሠራር ሞዴል፣ የአፈጻጸም ልህቀት፣ ተቋሟዊ ዓላማን ማስተማርና ማስተዋወቅ፣ የማኅበረሰብን ግንዛቤን ማሳደግ እና ተደራሽነት የማረጋገጥ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ ማጠቃለያ እነዚህ ሦስት የተቀናጁ ስትራቴጂካዊ ማዕቀፎች፣ የኢትዮጵያን የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ መሠረት በማድረግ፣ የመንግሥት የቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ተቋማትን ወደ ንቁ፣ ሁሉን ዓቀፍ እና ዘላቂ የክህሎት ማጎልበቻ ማዕከላት ለመቀየር የሚያስችል አጠቃላይ መርሕ ቀርቧል። ። እነዚህ ማዕቀፎች የሥራ ገበያ ፍላጎቶችን ማሟላት፣ የሁሉም ሰው ፍትሓዊ ተጠቃሚነትን ማበረታታት፣ ባለድርሻ አካላትን ማቀናጀት፣ የፋይናንስ መረጋጋትን ማረጋገጥ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው ሥልጠና መስጠትን ቅድሚያ የሚሰጥ ነው። ከዚህም በተጨማሪ፣ የተሳሳቱ አመለካከቶችን ለመለወጥ እና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን እንደ ተከበረ የሙያ መስክ ለመሣል ይጥራሉ። የእነዚህ ሦስት የተቀናጁ ስትራቴጂካዊ ማዕቀፎች ዝርዝር ዕቅድ፣ አካሄድ፣ የጊዜ ሰሌዳ፣ ሚናዎችን እና ኃላፊነቶችን ጨምሮ በፈጻሚ አካላት በቀጣይ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ስለማዕቀፎቹ መርሕ ውጥን እንደምከተልው ቀርቧል። 50 4.4.1. ተቋማዊ የአሠራር ሞዴል እና የአፈጻጸም ልህቀት ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ የተቋማዊ የአሠራር ሞዴል ንዑስ ክፍል እንደ አጓጊ የዕሴት አቅርቦት (በዲጂታል እና አረንጓዴ ክህሎቶች የተደገፈ ብቃት ላይ የተመሠረተ ሥልጠና)፣ የታለመ የተቋሙ አገልግሎት የተለያዩ ተገልጋዮች (ወጣቶች፣ የኢ-መደበኛ ዘርፍ ሰራተኞች፣ የአካባቢ ኢንዱስትሪዎች፣ ገጠራማ ማህበረሰቦች እና ልዩ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች)፣ ቁልፍ ተግባራት (የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት፣ የሥልጠና አሰጣጥ እና ምርምር)፣ ጠንካራ ግብዓቶች (መሠረተ ልማት፣ የመረጃ ሥርዓቶች እና የመምህራን አቅም) ፣ ስትራቴጂካዊ ሽርክናዎች (ከመንግሥት፣ ከኢንዱስትሪ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋራ) ፣ የተለያዩ የገቢ ምንጮች (የተማሪ ክፍያ፣ የክህሎት ቀረጥ፣ የውስጥ ገቢ ሞዴሎች) እና የወጪ ቅነሳ የመሳሰሉ ቁልፍ ነገሮችን ያካትታል። የአፈጻጸም ልህቀት ንዑስ ክፍል የአሠራር ሥርዓት እና አመራርን ማጠናከር፣ ጥብቅ የጥራት ማረጋገጫ እና ተከታታይ ማሻሻያ ሂደቶችን ተግባራዊ ማድረግ፣ እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማሳደግ ላይ ያተኩራል። እንዲሁም ትብብርን ለማጎልበት ሁሉን ዓቀፍ የሥጋት አስተዳደር፣ የዘላቂነት ተግባራት እና የባለድርሻ አካላት ቀዳሚ ተሳትፎ ላይ አጽንዖት ይሰጣል። ይህ የተቀናጀ ማዕቀፍ የተለምዶውን ተቋማዊ የአሠራር ሞዴል ወደ ተለዋዋጭና ከመረጃ ጋራ የተጣጣመ ሥርዓት በመቀየር፣ ተቋማቱ ጥራት ያላቸው፣ ቀልጣፋ እና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ሞተሮች መሆናቸውን ያረጋግጣል። 4.4.2. የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ዘርፍ ማርኬቲንግ እና ማስተዋወቅ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ ይህ ማዕቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማትን በሀገራዊ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ ከተገለጸው ሪዕይ ጋራ ያጣጥማል። ዓላማው ኅብረተሰቡ ስለ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ያለውን ግንዛቤ ከፍ ማድረግ፣ የሙያ ሥልጠናን የተከበረ እና አዋጭ የሙያ መስክ መሆኑን ሁሉም ማኅበረሰብ ክፍል እንዲያውቅ ማድረግ፣ እና ዲጂታል መሣሪያዎች ሰፊ ታዳሚ ዘንድ እንዲደርሱ ማድረግ ነው። የማዕቀፉ ቁልፍ ትኩረት የሕዝብ ግንዛቤን ማሳደግ እና ጥራት ያለው ሥልጠና በመስጠት መልካም ስም መገንባት፣ የዕደ ጥበብ ሙያዎችን ማሳደግ፣ ዲጂታል ተሳትፎን ማሳደግ እና የባለድርሻ አካላትንና የኢንዱስትሪ ትብብርን ማጠናከር ናቸው። ይህ ማዕቀፍ የሕዝብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና ጥራት ያለው ሥልጠና በመስጠት መልካም ስም ለመገንባት የሚያስችሉ ተግባራትን ይዘረዝራል። ይህም የስኬት ታሪኮችን እና ምስክርነቶችን በመጠቀም የሕዝብ ግንዛቤ ማሳደግ ዘመቻዎችን (በቴሌቪዥን፣ ራዲዮ፣ ኅትመት እና ማህበራዊ ሚዲያ) ማስጀመርን ያካትታል። በተጨማሪም፣ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን እንደ ተከበረ እና ለወደፊት የሚያዘጋጅ የዕውቀት መንገድ አድርጎ ለመሳል ወጥ የሆነ የምርት ስም እና መልዕክት ማበልጸግን (ለምሳሌ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ልህቀት ክህሎቶች ለኢትዮጵያ መጪ ዘመን፤ ወዘተ) ያካትታል። 4.4.3. የማኅበረሰብ ግንዛቤን ማሳደግ እና ተደራሽነትን የማረጋገጥ ስትራቴጂካዊ ማዕቀፍ ይህ ማዕቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ተቋማትን ህዝባዊ ገጽታ ከፍ ለማድረግ እና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋራ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር የተነደፈ ሁሉን ዓቀፍ ስትራቴጂ ነው። ከሀገራዊ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ ጋራ በተጣጣመ መልኩ ግልጽ ዓላማዎችን እና የታለሙ ተግባራትን በማስቀመጥ ወጥ የሆነ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና የምርት ስም ለመፍጠር፣ የሥራ ዘርፎችን ለማስተዋወቅ እና ሁሉን ዓቀፍ የማኅበረሰብ ተደራሽነትን ለማሳደግ ይጥራል። 51 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም ማዕቀፉ ከተለመዱት ሚዲያዎች እስከ ዲጂታል መድረኮች ድረስ ባሉ በርካታ የማሠራጫ መንገዶች ላይ በማተኮር፣ የአካባቢ መሪዎችን፣ ባለድርሻ አካላትን እና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ቡድኖች በማሳተፍ ማኅበረሰብ-ተኮር ዝግጅቶችን ለማቅረብ ትኩረት ያደርጋል። እንዲሁም ሊለኩ የሚችሉ ቁልፍ የአፈጻጸም አመልካቾች (KPIs) እና ለትግበራ የተወሰነ የጊዜ ሰሌዳ በማስቀመጥ፣ ማዕቀፉ ቀጣይነት ያለው ክትትልና መሻሻልን ያረጋግጣል፣ ይህም የቅበላ መጨመር እና ጠንካራ የማኅበረሰብ አጋርነት እንዲኖር ያደርጋል። 4.5. የቲክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ ትግበራ የኃላፊነት፣ ተጠያቂነት፣ ምክር የሚሰጥ እና እንዲያውቀው መረጃ የሚሰጠው አካል ማትሪክስ (ኃተምእ) ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ ማጠቃለያ የ2017ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ ትግበራን ለመምራት፣ የኃላፊነት፣ ተጠያቂነት፣ ምክር የሚሰጥ አካል እና እንዲያውቀው መረጃ የሚሰጠው አካል ማትሪክስ (ኃተምእ/ RACI Matrix) ስትራቴጂካዊ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል። ይህ ማትሪክስ በሥርዓት የለውጥ ሂደት ውስጥ የሚያጋጥሙ ውስብስብ ጉዳዮችን ለመፍታት፣ የአሠራር ሥርዓቶችን፣ የትግበራ እና የአፈጻጸም ቁጥጥርና ክትትል ኃላፊነቶችን በግልጽ ይለያል። ማትሪክሱ በቴክኒክና ሙያ ሥልጠና የአሠራር ሥርአት ማጎልበት፣ አግባብነትና ጥራትን ማሻሻል፣ የሥራ ፈጣሪነትና ዝግጁነትን ማጎልበት፣ እና የምርምርና ኢኖቬሽን ምኅዳርን ማበልጸግ በሚሉ አራት ስትራቴጂካዊ ትኩረቶች ላይ ያተኩራል። ዋና አላማውም የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ሥርዓት ውስጥ ያሉ ቁልፍ ተዋናዮችን በማሳተፍ ውጤታማ ግንኙነትና ቅንጅትን በማረጋገጥ ሥርዓቱን ምላሽ ሰጪ፣ ከፍተኛ ጥራት ያለው እና ለሀገራዊ ልማት ሁሉን ዓቀፍ አንቀሳቃሽ ሞተር እንዲሆን ማድረግ ነው። ይህ የኃላፊነት፣ ተጠያቂነት፣ ምክር የሚሰጥ አካል እና እንዲያውቀው መረጃ የተሰጠው አካል ማትሪክስ (RACI Matrix) የፕሮጀክት ማኔጅመንት መሣሪያ ሲሆን የቡድን ሚናዎችን እና ኃላፊነቶችን በግልጽ ያብራራል። “ኃ (ኃላፊ)” ማለት ተግባሩን የሚያከናውን አካል ሲሆን፣ “ተ (ተጠያቂ)” ደግሞ በመጨረሻ ስለ ተግባሩ መጠናቀቅ መልስ የሚሰጥና ውሰኔ ሰጭ አካል ነው። “ም (ምክር የሚሰጥ አካል)” ማለትም ግብዓት የሚያቀርብ (ባለሁለት ወገን መረጃ ልውውጥ) ሲሆን፣ “እ (እንዲያውቀው መረጃ የሚሰጠው አካል)” እንዲሁም ስለሂደቱ ወቅታዊ መረጃ የሚያገኝ (የአንድ ወገን መረጃ ልውውጥ) ነው። ይህ ማትሪክስ ስትራቴጂው ወደ ክልሎች እና ተቋማት የድርጊት መርሓ ግብር ሲወርድ፣ የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ለመወሰን፣ የድርጊት መርሓ ግብሮችን ለማውጣት እና ዝርዝር ጉዳዮችን ለመወሰን በሚደረጉ የባለድርሻ አካላት ውይይቶች ይበልጥ እንዲዳብር ተደርጎ ይጠናከራል። 52 የባለድርሻ አካላት ኃላፊነቶች ክፍፍል የኃተምእ ማትሪክስ ዘዴን በመጠቀም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር (ሥ/ክ/ሚ) ጨምሮ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት የሚከተሉት ኃላፊነቶች ተሰጥቷቸዋል። ሥ/ክ/ሚኒስቴር፡ ለጠቅላላው ስትራቴጂ እና ፖሊሲ አቅጣጫ አጠቃላይ ተጠያቂነት (ተ) አለበት። (ሀገር ዓቀፍ) የቴ/ሙ/ሥ አስተባባሪ አካል፡ ለፖሊሲ ቀረጻ፣ ሀገር ዓቀፍ ማስተባበር እና ስትራቴጂካዊ መመሪያዎችን የመስጠት ኃላፊነት (ኃ) አለበት፣ እንዲሁም የሙያ እገዛ በሚያስፈልግበት ጊዜ ምክር (ም) ይሰጣል። ክልሎች፡ ሀገራዊ ስትራቴጂው ከክልላዊ ፍላጎቶች ጋራ መጣጣሙን በማረጋገጥ የክልሉን ፖሊሲ አፈፃፀም ይመራሉ እና ይከታተላሉ (ኃ)። የዘርፍ ክህሎት አስፈጻሚ አካላት፡ የኢንዱስትሪ ፍላጎቶችን ከሥልጠና ዓላማዎች ጋራ ለማጣጣም በዘርፉ ላይ ያተኮሩ ሙያዊ ዕውቀትና ክህሎቶችን ያማክራሉ (ም) ወይም ኃላፊነት ይጋራሉ (ኃ)። የቴ/ሙ/ሥ ተቋማት፡ እንደ ፈጻሚ ማዕከላት፣ የዕለት ተዕለት የሥልጠና እንቅስቃሴዎችን እና ፕሮግራሞችን ይቆጣጠራሉ (ኃ)። የተቋም ቦርድ፡ በቴ/ሙ/ሥ ተቋማት የውስጥ የበላይ አካል ሲሆን፣ የቴ/ሙ/ሥ ተቋማት ተግባራቶቻቸውን ከስትራቴጂዎች ጋራ የተጣጣሙና በአግባቡ መሬት የወረዱ መሆናቸውን ይከታተላል (ም)። የቴ/ሙ/ሥ መምህራን፡ ከፍተኛ ጥራት ያለው ሥልጠና የመስጠትና የትምህርት ደረጃዎችን የማስጠበቅ ኃላፊነት (ኃ) አለባቸው። የቴ/ሙ/ሥ ሠልጣኞች፡ በግብረ መልስ ቀዳሚ ተጠቃሚ ሲሆኑ፣ በአጠቃላይ በሂደቱ ውስጥ ሲያልፉ መረጃውን ያገኛሉ (እ)። ኢንዱስትሪ/የግል ዘርፍ፡ የሥልጠና መርሓ ግብሮች ከሥራ ገበያ ፍላጎቶች ጋራ መጣጣማቸውን ለማረጋገጥ በንቃት አስተዋጽዖ ያደርጋሉ (ም/ኃ)። የጥራት ማረጋገጫ አካል፡ የሥልጠና ጥራትን ለማረጋገጥ ደረጃውን የማስጠበቅ፣ የዕውቅና አሰጣጥ እና ጠንካራ የምዘና ሥራዎችን የመተግበር ኃላፊነት (ኃ) አለበት። የልማት አጋሮች፡ በተለይ የቴክኒክ ምክር (ም) እንዲለግሱ እና የፋይናንስ ድጋፍ (ም) እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ። አዲስ የተቋቋሙ ፎረሞች፡ በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ልዩ ችግሮችን ለመፍታት በሚሰጣቸው ኃላፊነት መሠረት ሚናቸውን ይወስዳሉ (ኃ)። በተመሳሳይ ይህ ኃተምእ ስትራቴጂያዊ ማዕቀፍ በፈጻሚ አካላት የበለጠ ተዘጋጅቶ ማለትም ዝርዝር የኃላፊነት፣ ተጠያቂነት፣ ምክር የሚሰጥ አካል እና እንዲያውቀው መረጃ የሚሰጠው አካል (ኃተምእ) ተለይቶ ማትሪክስ ማዘጋጀት፣ የጊዜ ሰሌዳ፣ ሚናዎችን እና ኃላፊነቶችን ጨምሮ በመርሓ ግብር ዳብሮ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል። 53 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም © የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር 2017 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አገራዊ ሪፎርሙን ተከትሎ የሥራ ፈጠራ፣ ክህሎት ማበልጸግና የሥራ ሁኔታ ምቹነት ጉዳዮችን ለመተግበር በአዋጅ ቁጥር 1263/2014 የተቋቋመ ተቋም ነው። ስልክ ቁጥር፡ +251 116 671792 ፖስታ ሳ/ቁ፡ 25534 ፋክስ: +251 116 671568 አድራሻ፡ ላምበረት መነኻሪያ አካባቢ ኢሜይል: This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it ተጨማሪ መረጃዎችን እነዚህ ኮድ ስካን በማድረግ በዌብሳይትና ማህበራዊ ሚድያ ይከታተሉን። ዌብሳይት ፌስቡክ ሊንክድኢን 54 55 የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ስትራቴጂ 2017 ዓ.ም 56

Last Updated (Thursday, 08 October 2026 12:25)